የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g 5/10 ገጽ 31
  • ቤተሰብ የሚወያይበት

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ቤተሰብ የሚወያይበት
  • ንቁ!—2010
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ጥሩ ውሳኔ ነበር?
  • ስለ ንጉሥ ኢዮሣፍጥ ምን የምታውቀው ነገር አለ?
  • ለልጆች የቀረበ የሥዕል ጥያቄ
  • ከዚህ እትም
  • በገጽ 31 ላይ ለቀረቡት ጥያቄዎች የተሰጡ መልሶች
  • ቤተሰብ የሚወያይበት
    ንቁ!—2010
  • መልስህ ምንድን ነው?
    ንቁ!—2008
  • ቤተሰብ የሚወያይበት
    ንቁ!—2010
  • ቤተሰብ የሚወያይበት
    ንቁ!—2010
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—2010
g 5/10 ገጽ 31

ቤተሰብ የሚወያይበት

ጥሩ ውሳኔ ነበር?

ማርቆስ 14:66-72ን አንብብ። ከዚያም ሥዕሉን ተመልከት። መልስህን ከታች ባሉት ክፍት ቦታዎች ላይ ጻፍ።

1. በሥዕሉ ላይ ያለው ሁኔታ የተከናወነው የት ነበር?

ፍንጭ፦ ማርቆስ 14:53, 54ን አንብብ።

․․․․․

2. ጴጥሮስ፣ ሰዎች የኢየሱስ ተከታይ እንደሆነ ሲነግሩት ምን አደረገ?

․․․․․

3. ለሁለተኛ ጊዜ ዶሮ ሲጮህ ምን ሆነ?

․․․․․

ለውይይት፦

ጴጥሮስ እንዲህ ዓይነት እርምጃ የወሰደው ለምን ይመስልሃል? አንተስ እንዲህ ያለ ስህተት እንዳትፈጽም ምን ማድረግ ትችላለህ?

ስለ ንጉሥ ኢዮሣፍጥ ምን የምታውቀው ነገር አለ?

4. ኢዮሣፍጥ በይሁዳ የነበረውን የፍርድ ሁኔታ ያስተካከለው እንዴት ነው?

ፍንጭ፦ 2 ዜና መዋዕል 19:5-11ን አንብብ።

․․․․․

5. ኢዮሣፍጥ ምን ስህተት ሠራ?

ፍንጭ፦ 2 ዜና መዋዕል 18:1-3ን እና 19:1-3ን አንብብ።

․․․․․

ለውይይት፦

ጓደኛን በመምረጥ ረገድ ከኢዮሣፍጥ ምን ትምህርት ማግኘት ትችላለህ?

ፍንጭ፦ 1 ቆሮንቶስ 15:33ን አንብብ።

ለልጆች የቀረበ የሥዕል ጥያቄ

ከዚህ መጽሔት ውስጥ እነዚህን ሥዕሎች ማግኘት ትችላለህ? እያንዳንዱ ሥዕል ምን እንደሚያሳይ በራስህ አባባል ግለጽ።

ከዚህ እትም

የሚከተሉትን ጥያቄዎች መልስ፤ እንዲሁም የጎደለውን ቁጥር አሟላ።

ገጽ 4 ራሳችንን ከምን ነገር ማንጻት ይገባናል? 2 ቆሮንቶስ 7:․․․

ገጽ 5 ሁለት ሰዎች አብረው ምን ማድረግ ይችላሉ? መክብብ 4:․․․

ገጽ 19 ጥበበኞች በምን ላይ ተስፋቸውን አይጥሉም? 1 ጢሞቴዎስ 6:․․․

ገጽ 27 የበለጠ ደስታ የምታገኘው ምን ስታደርግ ነው? የሐዋርያት ሥራ 20:․․․

● መልሱ በገጽ 24 ላይ ይገኛል

በገጽ 31 ላይ ለቀረቡት ጥያቄዎች የተሰጡ መልሶች

1. በሊቀ ካህናቱ ግቢ ውስጥ።

2. ጴጥሮስ ኢየሱስን እንደማያውቀው በመናገር ካደ።

3. ጴጥሮስ ስቅስቅ ብሎ አለቀሰ።

4. ኢዮሣፍጥ አምላክን የሚፈሩ ዳኞች በከተሞች እንዲሁም ሌዋውያንንና ካህናትን በኢየሩሳሌም በመሾም።

5. ክፉ ከነበረው ንጉሥ ከአክዓብ ጋር ወዳጅነት መሠረተ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ