የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g 8/10 ገጽ 25
  • የውኃ ተርብ ክንፍ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የውኃ ተርብ ክንፍ
  • ንቁ!—2010
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የጉጉት ክንፍ
    ንድፍ አውጪ አለው?
  • አስገራሚ የሆነው የቢራቢሮ ክንፍ
    ንቁ!—2012
  • የርዕስ ማውጫ
    ንቁ!—2010
  • የቢራቢሮ ክንፍ
    ንቁ!—2014
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—2010
g 8/10 ገጽ 25

ንድፍ አውጪ አለው?

የውኃ ተርብ ክንፍ

● አንዳንድ የውኃ ተርቦች ያሉበትን ከፍታ ብዙም ሳይለቁ ለ30 ሴኮንዶች ያህል ማንዣበብ ይችላሉ። ለዚህ ሚስጥሩ ምንድን ነው? የክንፋቸው ንድፍ በአውሮፕላን ኢንዱስትሪ ከተሠሩት ክንፎች ሁሉ እጅግ በተለየ ሁኔታ አየርን ሰንጥቀው ለማለፍ ስለሚያስችላቸው ነው!

እስቲ የሚከተለውን አስብ፦ በጣም ስስ የሆነው የውኃ ተርብ ክንፍ የተሸበሸበ መሆኑ ክንፉ በቀላሉ እንዳይታጠፍ ይረዳዋል። ከዚህም ባሻገር ክንፉ የተሸበሸበ መሆኑ የውኃ ተርቡን ወደ ላይ በመግፋት አየር ላይ እንዲንሳፈፍ የሚያደርገው ግፊት እንዲጨምር እንደሚረዳው የሳይንስ ሊቃውንት ደርሰውበታል። ኒው ሳይንቲስት የተባለው መጽሔት እንደገለጸው ከሆነ “ይህ የሚሆነው አየር በተሸበሸቡት ክንፎች መካከል በሚገኙት ክፍት ቦታዎች ስለሚዘዋወርና ተርቡን ወደኋላ የሚጎትተው የአየር ግፊት በእነዚህ ክፍት ቦታዎች ላይ ያለውን አየር እምብዛም ስለማያገኘው ነው፤ ይህ ደግሞ ተርቡን ከሥር ወደላይ የሚገፋው ኃይል እንዲፈጠር የሚያደርገውን በክንፉ ላይ የሚያልፈውን ነፋስ ያግዘዋል።”

የበረራ ቴክኖሎጂ መሐንዲስ የሆኑት አቤል ቫርጋስ እና ባልደረቦቻቸው የውኃ ተርብን ክንፍ ካጠኑ በኋላ “የተፈጥሮን ንድፍ በመቅዳት የሚሠሩ ክንፎች አነስተኛ የሆኑ በራሪ መሣሪያዎችን ንድፍ ለማውጣት ትልቅ አስተዋጽኦ ያበረክታሉ” የሚል መደምደሚያ ላይ ደርሰዋል። ካሜራ ወይም ሌላ መሣሪያ የተገጠሙባቸው እንዲህ ያሉ የእጅ መዳፍ መጠን ያላቸው ሮቦቶች አደጋ ከተከሰተባቸው ቦታዎች መረጃዎችን መሰብሰብንና የብክለት መጠንን መመዝገብን ጨምሮ የተለያዩ ጠቃሚ አገልግሎቶችን ይሰጣሉ።

ታዲያ ምን ይመስልሃል? በጣም ስስ የሆነውና የተሸበሸበው የውኃ ተርብ ክንፍ እንዲሁ በአጋጣሚ የተገኘ ነው? ወይስ ንድፍ አውጪ አለው?

[በገጽ 25 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

በውኃ ተርብ ንድፍ የተሠራው ይህ እጅግ አነስተኛ በራሪ መሣሪያ 120 ሚሊ ግራም ክብደትና ስድስት ሴንቲ ሜትር ስፋት ያለው ሲሆን በኤሌክትሪክ አማካኝነት የሚርገበገቡ በጣም ስስና ጠፍጣፋ የሲልከን ክንፎች ተገጥመውለታል

[ምንጭ]

© Philippe Psaila/Photo Researchers, Inc.

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ