የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g 1/11 ገጽ 19
  • ትልቅ ቋሚ ሰዓት

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ትልቅ ቋሚ ሰዓት
  • ንቁ!—2011
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ‘የሰዓቶችን ንጉሥ’ ማየትና መስማት
    ንቁ!—2010
  • ዓለማችን ምንም ተስፋ የለውም?
    ንቁ!—2017
  • ሰዓት ስንት ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2018
  • የመካከለኛው ዘመን የሜካኒክስ ሊቃውንት
    ንቁ!—2012
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—2011
g 1/11 ገጽ 19

ትልቅ ቋሚ ሰዓት

● አውቶማቲክ ሰዓት ከ900 ዓመታት በፊት ቻይና ውስጥ እንደተፈለሰፈ ይገመታል። ከዚያ ጊዜ ጀምሮ በሰዓቶች ሞዴል ላይ ብዙ ማሻሻያ ተደርጓል። ጉልህ መሻሻል የተደረገው በ1600 አጋማሽ ላይ አውቶማቲክ ሰዓቶች ፔንዱለም በገባላቸው ጊዜ ነበር። ለዚህ ጉልህ የፈጠራ ውጤት ምስጋና ይግባውና ሰዓቶች በትክክል መቁጠር የሚያስችላቸው አንድ አዲስ ነገር ይኸውም ደቂቃ ቆጣሪ ተጨመረላቸው! ፔንዱለምና ክብደት የገባለት እንዲሁም በአንፃራዊ ሁኔታ ሲታይ ከባድ በሆኑ ዕቃዎች የተሠራው አዲሱ ሞዴል ጠንካራና ቀጥ ያለ ማስቀመጫ አስፈልጎት ነበር። ከዚህ ሁሉ ማሻሻያ በኋላ በዓለም ዙሪያ በሚገኙ ሰዎች ዘንድ ግራንድፋዘር ክሎክa ወይም ትልቅ ቋሚ ሰዓት በመባል የሚታወቀው ሰዓት ተሠራ፤ አንድ የሰዓት ባለሙያ ይህን ሰዓት “አስቸጋሪ የአየር ሁኔታዎችን እንኳን ሳይቀር ተቋቁሞ በትክክል የሚሠራ አስተማማኝ የሰዓት መቁጠሪያ” በማለት ገልጸውታል።

ተወዳጅነት ያተረፈው ይህ ሰዓት መጀመሪያ ላይ ይፈበረክ የነበረው እንደ ለንደንና ፓሪስ ባሉ ትላልቅ የአውሮፓ ከተሞች ነበር። ቀስ በቀስ ግን አውሮፓ ውስጥ በየጓዳ ጎድጓዳው መሠራት ጀመረ። ሞዴሉ እንደየአካባቢው ዕደ ጥበባዊ ስልት ይሠራ ስለነበር ይበልጥ እያማረ መጣ። የሰዓቱ ቅርጽ ቀጥ ወይም ጎበጥ ያለ መሆን ይችል ነበር፤ መጠኑም ቀጠን ያለ ወይም ግዙፍ ሆኖ ሊሠራ ይችል ነበር። የሰዓቱ ቀፎ ወይም ሣጥን ከጥድ፣ ከባሉጥ እንዲሁም ኢቦኒ፣ ማሆጋኒ ወይም ዋልነት ከሚባሉ ዛፎች እንጨት ሊሠራ ይችል የነበረ ሲሆን ቀፎው ልሙጥ ሆኖ ወይም በጌጣጌጥ ተንቆጥቁጦ ይሠራ ነበር። ስለዚህ ይህ ትልቅ ቋሚ ሰዓት በትክክል ስለሚቆጥር ብቻ ሳይሆን የተቀመጠበትን ክፍል ውበትና ግርማ ሞገስ ያጎናጽፍ ስለነበር ይበልጥ ተወዳጅነትን እያገኘ ሄደ።

ይህን ሰዓት ለብዙዎች ዓይን ውብና ማራኪ ሆኖ እንዲታይ ያደረገው ሌላም ምክንያት አለ። በድንገት ሲታይ፣ የቆመ ሰው ይመስላል። ዶክተር ሲኒካ ማንቱኤላ የተባሉ ፊንላንዳዊ ተመራማሪ “መጠኑ መካከለኛ ቁመት ያለው ሰው የሚያህል ሲሆን ፊቱ ላይ ትርጉም ያለው ስሜት ይነበብበታል” በማለት ገልጸዋል። እንዲሁም ቲክ ቲክ የሚለው የሰዓቱ ድምፅ የልብ ምት ይመስላል። በዛሬው ጊዜ ዝንፍ የማይሉትና እምብዛም ውድ ያልሆኑት የሚሞሉ ሰዓቶች እነዚህን ድንቅ የፈጠራ ውጤቶች ተክተዋቸዋል። ይሁን እንጂ በዚህ በጥድፊያ በተሞላው ጊዜያችንም እንኳን ሳይቀር ይህ ትልቅ ቋሚ ሰዓት መኖሩ በውስጣችን የመረጋጋት ስሜት ይፈጥራል። ኪፒንግ ታይም—ኮሌክቲንግ ኤንድ ኬሪንግ ፎር ክሎክስ የተሰኘው መጽሐፍ “ይህ ትልቅ ቋሚ ሰዓት ያለው ምንጊዜም የማይለዋወጥና ረጋ ያለ ምት እንዴት እንደሆነ ባናውቅም መንፈስን ሊያረጋጋ የሚችል ከመሆኑም በላይ ይበልጥ ሰላማዊ ነው ብለን በምናስበው ዘመን ውስጥ የምንኖር እንዲመስለን ያደርጋል” በማለት አስተያየቱን ሰጥቷል።

[የግርጌ ማስታወሻ]

a በአንዳንድ አገሮች ሎንግኬዝ ክሎክ ተብሎ የሚጠራው ግራንድፋዘር ክሎክ ስያሜውን ያገኘው በ1876 “ማይ ግራንድፋዘርስ ክሎክ” በሚል ርዕስ ከተዘፈነ ተወዳጅ ዘፈን እንደሆነ ይነገራል።

[በገጽ 19 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

በ1800ዎቹ መጀመሪያ ላይ እንደተሠራ የሚገመት ሰዓት

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ