የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g 2/11 ገጽ 29
  • ከዓለም አካባቢ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ከዓለም አካባቢ
  • ንቁ!—2011
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ጥቂት እውነተኛ ወዳጆች
  • ዕፅ አዘዋዋሪ ከፊል ባሕር ሰርጓጅ መርከቦች
  • በቤተሰብ አንድ ላይ ሆኖ መመገብ የሚያስገኘው ጥቅም
  • አብሮ መመገብ የቤተሰባችሁን አንድነት ሊያጠናክረው ይችላል?
    ንቁ!—2010
  • ከዓለም አካባቢ
    ንቁ!—2012
  • የታሸገ ምግብ ምሥክርነት ሰጠ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1995
  • የተከለከሉ ዕፆች ሕይወትህን የሚነኩትእንዴት ነው?
    ንቁ!—1999
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—2011
g 2/11 ገጽ 29

ከዓለም አካባቢ

ዕድሜያቸው ከ40 ዓመት በታች ከሆነ ጀርመናውያን መካከል በየቀኑ ከልጆች ጋር መጸለይ ጠቃሚ እንደሆነ የሚያስቡት ከአንድ አራተኛ ያነሱ ሲሆኑ ከቤተ ክርስቲያን ተሳላሚዎች መካከል ጸሎት አስፈላጊ እንደሆነ የሚሰማቸው ደግሞ ከአሥሩ አራቱ ብቻ ናቸው።—አፖቴከን ኡምሻው፣ ጀርመን

አንድ የወንዴ ዘር ለጋሽ በጂኑ ላይ ከልብ ሕመም ጋር የተያያዘ በምርመራ ያልተደረሰበት እክል ስለነበረበት ይህንኑ እክል የእሱ ልጆች እንደሆኑ ከሚታወቁ 24 ሕፃናት መካከል ለ9ኙ አስተላልፏል። ከእነዚህ መካከል አንዱ በሁለት ዓመቱ በልብ ሕመም ምክንያት ሞቷል።—ጃማ፣ ዩናይትድ ስቴትስ

“ከ50 በመቶ በላይ የሚሆኑ ሩስያውያን ሙስና ሊወገድ የማይችል የሕይወት ክፍል እንደሆነ ያምናሉ።”—ሪያ ኖቮስቲ፣ ሩስያ

ጥቂት እውነተኛ ወዳጆች

የለንደኑ ዴይሊ ቴሌግራፍ እንደሚለው ከሆነ “አንድ ብሪታንያዊ ያሉት የሚተማመንባቸውና እውነተኛ ወዳጆች ሦስት ብቻ ናቸው።” አንድ ጥናት እንዳመለከተው አንድ ሰው “በሕይወቱ ውስጥ በአማካይ ከሚኖሩት 36 የሚያህሉ ጓደኞች” ጋር ያለው ግንኙነት እንዲቋረጥ ከሚያደርጉት ምክንያቶች መካከል “ጊዜ ማጣት” እና ‘ቀስ በቀስ እየተራራቁ መሄድ’ የሚገኙበት ሲሆን ጥናት ከተደረገባቸው ሰዎች መካከል 43 በመቶ የሚሆኑት ከወዳጆቻቸው ጋር የተቆራረጡት “በመቀያየማቸው . . . እና ተኮራርፈው በመቅረታቸው” ምክንያት ነው። አንድ አምስተኛ የሚሆኑት “የሚያማክሩት ሰው ስለሌላቸው” የልባቸውን አውጥተው የሚናገሩት ለሥራ ባልደረቦቻቸው ነው። የጥናቱ ቃል አቀባይ “የሌላን ሰው እምነት ለማትረፍና እምነት የሚጣልበት ዓይነት ሰው ለመሆን ልዩ ነገር ያስፈልጋል” ብለዋል።

ዕፅ አዘዋዋሪ ከፊል ባሕር ሰርጓጅ መርከቦች

የኮሎምቢያ ዕፅ አዘዋዋሪዎች ወደ ማዕከላዊ አሜሪካ፣ ሜክሲኮና ዩናይትድ ስቴትስ ኮኬይን ለማስገባት የሚጠቀሙበት ዘዴ ይበልጥ እየተራቀቀ መጥቷል። ከ1993 ወዲህ ቢያንስ 42 የሚያህሉ ዕፅ አዘዋዋሪ ከፊል ባሕር ሰርጓጅ መርከቦች በኮሎምቢያ ባለሥልጣናት ተይዘዋል። እነዚህ መርከቦች የሚሠሩባቸው በርካታ የማምረቻ ቦታዎች ተገኝተዋል። በናፍጣ የሚሠራ ሞተር ያላቸው እነዚህ መርከቦች ባሕር ውስጥ ጠልቀው መግባት ባይችሉም በራዳር ተጠቅሞ ለመያዝ በጣም ያስቸግራሉ። አንዳንዶቹ እስከ 3,200 ኪሎ ሜትር መጓዝና ከስልሳ እስከ መቶ ኩንታል መጫን ይችላሉ፤ እነዚህን መርከቦች ለመሥራት በግምት እስከ አንድ ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ይፈጃል።

በቤተሰብ አንድ ላይ ሆኖ መመገብ የሚያስገኘው ጥቅም

በቅርብ በተደረገ አንድ ጥናት ላይ ቃለ መጠይቅ ከተደረገላቸው ከ14 እስከ 16 ዓመት ባለው የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ፊንላንዳውያን ልጆች መካከል ከቤተሰባቸው ጋር የሚመገቡት ከግማሽ በታች ናቸው። እንዲያውም በብዙ ቤቶች ምግብ በሥነ ሥርዓት ተዘጋጅቶ እንደማይቀርብ ጥናቱ አመልክቷል። ይሁን እንጂ ልጆች ዘና ባለ ሁኔታ ከቤተሰባቸው ጋር አዘውትረው ጊዜ ለማሳለፍ በጣም ይፈልጋሉ። ከወላጆቻቸው ምን እንደሚፈልጉ ሲጠየቁ የሰጡት መልስ ግልጽ መልእክት ያስተላልፋል፦ “ትኩስ ምግብ፣ በቤተሰብ አንድ ላይ ሆኖ መመገብና ጊዜ ሰጥቶ የሚያዳምጠን ሰው” ብለው እንደመለሱ ሄልሲንጂን ሳኖማት የተባለው ጋዜጣ ዘግቧል። በቤተሰብ አንድ ላይ ሆኖ መመገብ ለአንድ ወጣት የአእምሮ ጤንነት ትልቅ አስተዋጽኦ አለው። ይኸው ጋዜጣ እንዳለው “ከቤተሰባቸው ጋር አብረው የሚመገቡ ወጣቶች አብዛኛውን ጊዜ በትምህርታቸው ጎበዝ ሲሆኑ አያጨሱም፣ አይጠጡም ወይም ዕፅ አይወስዱም፤ እንዲሁም የመንፈስ ጭንቀት እምብዛም አያጠቃቸውም።”

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ