የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g 7/11 ገጽ 3
  • መከራ አብቅቶ ለማየት እንጓጓለን!

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • መከራ አብቅቶ ለማየት እንጓጓለን!
  • ንቁ!—2011
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • መከራ ይህን ያህል የበዛው ለምንድን ነው?
    ንቁ!—2011
  • መጽሐፍ ቅዱስ ምን ያስተምራል?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2017
  • ጥያቄ 3፦ አምላክ መከራ እንዲደርስብኝ የሚፈቅደው ለምንድን ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2012
  • መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ተፈጥሮ አደጋዎች ምን ይላል?
    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—2011
g 7/11 ገጽ 3

መከራ አብቅቶ ለማየት እንጓጓለን!

የኪዮ መከራ የጀመረው አባቱ ላሞቹን በአቅራቢያው ባለ የበቆሎ ማሳ ውስጥ በመልቀቁ ምክንያት በተገደለ ጊዜ ነበር። በኋላም እናቱና ሁለት እህቶቹ በካምቦዲያ በሚገኙት የከሜር ሩዥ ኃይሎች ተገደሉ። ከዚያም ኪዮ መሬት ውስጥ በተቀበረ ፈንጂ ጉዳት ደረሰበት። እርዳታ እስኪያገኝ ድረስ በጫካ ውስጥ 16 ቀን ቆየ። በደረሰበት ጉዳት ሳቢያ እግሩ መቆረጥ ነበረበት። ኪዮ “መኖር አስጠልቶኝ ነበር” በማለት ተናግሯል።

መከራ በማንም ሰው ላይ እንደሚደርስ ሳታስተውል አትቀርም። የተፈጥሮ አደጋዎች፣ ሕመም፣ የአካል ጉዳት፣ የወንጀል ጥቃት እንዲሁም ሌሎች አሳዛኝ ነገሮች በማንም ሰው ላይ፣ በየትኛውም ቦታና በማንኛውም ጊዜ ሊደርሱ ይችላሉ። ግብረ ሰናይ ድርጅቶች በሰው ልጆች ላይ የሚደርሰውን መከራ ለማስወገድ ካልሆነም ደግሞ ለመቀነስ የቻሉትን ያህል ጥረት አድርገዋል። ይሁንና ጥረታቸው ምን ውጤት አስገኝቷል?

ረሃብን ለማስወገድ የተደረገውን ዘመቻ እንደ ምሳሌ እንውሰድ። ቶሮንቶ ስታር የተሰኘ አንድ ጋዜጣ እንደዘገበው ከሆነ ብዙዎች በተፈጥሮ አደጋዎች ሳቢያ ቤት አልባ ከመሆናቸውም ሌላ ለምግብ እጦት ተዳርገዋል። ይሁን እንጂ ጋዜጣው “በረሃብ የተጠቁ ሰዎችን የሚረዱ የተለያዩ ድርጅቶች የሚያደርጉት ጥረት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ በመጣ ዓመፅ ምክንያት ተስተጓጉሏል” ብሏል።

ከፖለቲካ፣ ከማኅበራዊ ሕይወትና ከሕክምና ጋር በተያያዘ አመራር የሚሰጡ አካላት በሰዎች ላይ የሚደርሰውን መከራ ለመቀነስ የተቻላቸውን ሁሉ ጥረት ቢያደርጉም የተገኘው ውጤት ግን የተጠበቀውን ያህል አይደለም። የኢኮኖሚውን እድገት ለማፋጠን የተቀረጹ ፕሮግራሞች ድህነትን ለማስወገድ የፈየዱት ነገር የለም። ክትባቶች፣ መድኃኒቶችና የተራቀቁ የቀዶ ሕክምና ዘዴዎች በሽታን ሙሉ በሙሉ ማጥፋት አልቻሉም። ፖሊሶችና ሰላም አስከባሪ ኃይሎች የወንጀል ድርጊቶችን ማስቆምም ሆነ እየተባባሱ እንዳይሄዱ ማድረግ ባለመቻላቸው የሚያደርጉት ጠፍቷቸዋል።

ለመሆኑ መከራ ይህን ያህል የበዛው ለምንድን ነው? አምላክ በሰው ልጆች ላይ እየደረሰ ያለው መከራ ያሳስበዋል? በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ለእነዚህ ጥያቄዎች ከመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የሚያጽናኑ መልሶችን ማግኘት ችለዋል፤ በቀጣዮቹ ርዕሶች ላይ ይህን እንመለከታለን።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ