የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g 9/12 ገጽ 25-26
  • ያለ ደም የሚሰጡ አማራጭ ሕክምናዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ያለ ደም የሚሰጡ አማራጭ ሕክምናዎች
  • ንቁ!—2012
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ተፈላጊነቱ እየጨመረ የመጣው ያለ ደም የሚሰጥ ሕክምና
    ንቁ!—2000
  • የይሖዋ ምሥክሮች ደም የማይወስዱት ለምንድን ነው?
    ስለ ይሖዋ ምሥክሮች ብዙ ጊዜ የሚነሱ ጥያቄዎች
  • ከፍተኛ ጥራት ያለው ሕክምና የትኛው ነው?
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2007
  • የሐኪም ሙያ
    ንቁ!—1993
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—2012
g 9/12 ገጽ 25-26

ያለ ደም የሚሰጡ አማራጭ ሕክምናዎች

ከአርባ ከሚበልጡ አገሮች የተውጣጡ እውቅ ባለሙያዎች ከግንቦት 20-22, 2011 በተካሄደው የአውሮፓ የልብና የደም ሥር ቀዶ ጥገና ማኅበር 60ኛ ኢዮቤልዩ ዓለም አቀፍ ጉባኤ ላይ ለመገኘት በሞስኮ ተሰብስበው ነበር። አንድ የሩስያ ቴሌቪዥን ጋዜጠኛ “ሐኪሞች ለእንዲህ ዓይነቱ ጉባኤ የሚሰጡት ግምት አትሌቶች ለኦሎምፒክ ከሚሰጡት አይተናነስም” ብሏል።

ስብሰባው በተደረገባቸው በሦስቱም ቀናት የብዙ ሰዎችን ትኩረት የሳበው ያለ ደም የሚሰጡ አማራጭ ሕክምናዎችን አስመልክቶ መረጃ የሚሰጠው ዴስክ ነበር። ይህን ዴስክ ያዘጋጀው የይሖዋ ምሥክሮች የሆስፒታል መረጃ አገልግሎት ነው። ሐኪሞች ወደዚህ ዴስክ በመምጣት በዚህ ወሳኝ ርዕስ ዙሪያ የተዘጋጁ በመቶ የሚቆጠሩ መጻሕፍትን፣ ዲቪዲዎችን፣ የሕክምና ጽሑፎችንና ልዩ ልዩ መረጃዎች የያዙ ፋይሎችን ወስደዋል። በተለይ ያለ ደም የሚሰጡ አማራጭ የሕክምና ዘዴዎች—ቀላል፣ አስተማማኝና ውጤታማa የተባለው የቪዲዮ ፊልም ያለበት ዲቪዲ በብዙዎች ዘንድ ተፈላጊነት ነበረው።

ዴስኩን የጎበኙ በርካታ ሐኪሞች በቀዶ ሕክምና ወቅት ብዙ ደም እንዳይፈስ ማድረግ እጅግ አስፈላጊ እንደሆነ ተስማምተዋል። በስብሰባው ላይ ንግግር ያቀረቡ ከጣሊያን የመጡ አንድ የልብ ቀዶ ሕክምና ባለሙያ፣ የይሖዋ ምሥክሮችን በደንብ እንደሚያውቋቸውና 70 ለሚሆኑ የይሖዋ ምሥክሮች ሕሙማን በተሳካ ሁኔታ ያለ ደም የልብ ቀዶ ሕክምና እንዳደረጉ ተናግረዋል። በተጨማሪም በክሊኒካቸው ውስጥ ያለ ደም ቀዶ ሕክምና ማድረግ በጣም የተለመደ ነገር መሆኑን ጠቅሰዋል። በጀርመን የበርሊን የልብ ተቋም ፕሮፌሰር የሆኑ አንድ ሐኪም ለራሳቸውና ለሥራ ባልደረባቸው አንድ አንድ ዲቪዲ ወስደዋል። ሐኪሙ፣ 2.5 ኪሎ ግራም ለሚመዝን ሕፃን በቅርቡ ያለ ደም ቀዶ ጥገና እንዳደረጉና ክሊኒካቸው ከዚያ ያነሰ ክብደት ላላቸው ሕፃናት ሳይቀር ያለ ደም የልብ ቀዶ ጥገና እንዳደረገ በስብሰባው ላይ ለተገኙት ሰዎች ተናግረዋል።

የሞስኮው ስብሰባ ከተደረገ ከአንድ ወር በኋላ በሩሲያ ሰሜን ምዕራብ አካባቢ የሚገኙ ማደንዘዣ የሚሰጡ ባለሙያዎች (አኒስቲዚዮሎጂስት) እና ልዩ ክትትል የሚያስፈልጋቸውን ሕሙማንን የሚረዱ ሐኪሞች (ኢንቴንሲቭ ኬር ፊዚሽያን) አራተኛውን የቤሎሞርስክ ሲምፖዚየም አካሂደው ነበር፤ ከተለያዩ አገሮች የተውጣጡ ሐኪሞች በአርካንጊልስክ ከተማ ውስጥ በተካሄደው በዚህ ስብሰባ ላይ ተገኝተዋል። የሆስፒታል መረጃ አገልግሎት በዚህ ቦታም ተመሳሳይ ዴስክ ከፍቶ የነበረ ሲሆን ዴስኩ የብዙዎችን ትኩረት ስቦ ነበር። አንድ ሐኪም ዴስኩ ያቀረባቸውን መረጃዎች ሲመለከቱ “እኛ የሚያስፈልገን እንዲህ ዓይነት ነገር ነው!” ብለዋል። እኛ ሐኪም፣ አንዳንድ የሥራ ባልደረቦቻቸው ልማድ ስለሆነባቸው ብቻ በቃጠሎ ለተጎዱ ታካሚዎች ደም መስጠት መቀጠላቸው የሚያሳዝን እንደሆነ ተናግረዋል። አክለውም “እናንተ ያዘጋጃችኋቸው መረጃዎች በቃጠሎ ለተጎዱ ሰዎች የሚሰጠውን ሕክምና አስመልክቶ በሴይንት ፒተርስበርግ ሊደረግ ለታሰበው ጉባኤ በጣም ጠቃሚ ይሆናሉ” በማለት ተናግረዋል።

በመላው ዓለም፣ ቀዶ ጥገናን ጨምሮ ያለ ደም የሚሰጡ ሕክምናዎች ያላቸውን ጠቀሜታ የተረዱ ሐኪሞች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ነው። ይህ ዓይነቱ ሕክምና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ያለው የሕክምና ዘዴ እስከመሆን ይደርስ እንደሆነ ወደፊት የምናየው ነገር ይሆናል።

a በይሖዋ ምሥክሮች የተዘጋጀ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ