የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g20 ቁጥር 1 ገጽ 3
  • ውጥረት አለብህ?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ውጥረት አለብህ?
  • ንቁ!—2020
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ጥሩና መጥፎ ውጥረት
    ንቁ!—1998
  • ውጥረትን መቆጣጠር የምንችልበት መንገድ
    ንቁ!—2010
  • በትምህርት ቤት የሚያጋጥመኝን ውጥረት እንዴት ልቋቋመው?
    ወጣቶች የሚጠይቋቸው ጥያቄዎችና ተግባራዊ መሆን የሚችሉ መልሶች፣ ጥራዝ 1
  • ውጥረት—መንስኤዎቹና የሚያስከትላቸው ችግሮች
    ንቁ!—2005
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—2020
g20 ቁጥር 1 ገጽ 3
በሥራ ቦታ ያለች ሴት በውጥረት በመዋጧ ምክንያት አንገቷን አቀርቅራ።

ከውጥረት እፎይታ ማግኘት

ውጥረት አለብህ?

“ሁሉም ሰው በተወሰነ ደረጃ ውጥረት አለበት፤ እኔ ግን ውጥረት ከአቅሜ በላይ ሆኖብኛል። ውጥረት ያስከተለብኝ፣ አንድ ትልቅ ችግር ሳይሆን የየዕለቱ ውጣ ውረድ እንዲሁም አካላዊና አእምሯዊ ሕመም ያለበትን ባለቤቴን ለብዙ ዓመታት ማስታመሜ የፈጠረብኝ ጫና ነው።”—ጂልa

“ባለቤቴ ጥላኝ ስለሄደች ሁለት ልጆች ያሳደግኩት ብቻዬን ነው። ልጆችን ያለእናት ማሳደግ በጣም ከባድ ነው። በዚያ ላይ ደግሞ ከሥራ ተባረርኩ፤ መኪናዬን የማሠራበት ገንዘብ እንኳ አልነበረኝም። ምን ማድረግ እንዳለብኝ ግራ ገባኝ። ውጥረቱ ከአቅሜ በላይ ሆኖብኝ ነበር። ራስን ማጥፋት ትክክል እንዳልሆነ ስለተሰማኝ አምላክ ሕይወቴን እንዲወስድና ከዚህ መከራ እንዲገላግለኝ ለመንኩት።”—ባሪ

አንተስ እንደ ጂልና እንደ ባሪ፣ ውጥረት ከአቅምህ በላይ እንደሆነብህ ይሰማሃል? ከሆነ ቀጣዮቹ ርዕሶች እንደሚያጽናኑህና እንደሚረዱህ ተስፋ እናደርጋለን። በርዕሶቹ ውስጥ የውጥረት መንስኤ ምን እንደሆነ፣ ውጥረት ምን ጉዳት እንደሚያስከትል እንዲሁም በተወሰነ መጠንም ቢሆን ከውጥረት እፎይታ ማግኘት የምንችለው እንዴት እንደሆነ እንመለከታለን።

a ስሞቹ ተቀይረዋል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ