የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g20 ቁጥር 2 ገጽ 4-5
  • አንዳንዶች ምን ብለው ያምናሉ?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • አንዳንዶች ምን ብለው ያምናሉ?
  • ንቁ!—2020
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ሂንዱዎች
  • ሙስሊሞች
  • የአይሁድ እምነት
  • ቡድሂስቶች
  • የኮንፊሽየስ ተከታዮች
  • የተለያዩ ባዕድ አምልኮዎች
  • ክርስቲያኖች
  • መጽሐፍ ቅዱስ ምን ያስተምራል?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2017
  • ጥያቄ 3፦ አምላክ መከራ እንዲደርስብኝ የሚፈቅደው ለምንድን ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2012
  • መከራ ይህን ያህል የበዛው ለምንድን ነው?
    ንቁ!—2011
  • 4. የተፈጠርነው በመከራ የተሞላ ሕይወት እንድንኖር ነው?
    ንቁ!—2020
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—2020
g20 ቁጥር 2 ገጽ 4-5
የቡድሂዝም፣ የሂንዱይዝም፣ የባዕድ አምልኮዎች፣ የአይሁድ እምነት፣ የክርስትና፣ የእስልምና እና የኮንፊሽየስ ተከታዮች ሃይማኖታዊ ዓርማዎች።

አንዳንዶች ምን ብለው ያምናሉ?

ሂንዱዎች

የሂንዱይዝም ዓርማ።

ሂንዱዎች አንድ ሰው መከራ የሚደርስበት በአሁኑ ሕይወቱ ወይም በቀድሞ ሕይወቱ በፈጸመው ድርጊት የተነሳ እንደሆነ ያምናሉ። አንድ ሰው አእምሮውን ከዓለማዊ ምኞቶች ሙሉ በሙሉ ማላቀቅ ከቻለ ሞክሻ የሚባል ደረጃ ላይ እንደሚደርስ ማለትም ሌላ ፍጥረት ሆኖ ዳግመኛ መወለዱን እንደሚያቆም ያስተምራሉ።

ሙስሊሞች

የእስልምና ዓርማ።

ሙስሊሞች መከራ የሚደርሰው ሰዎችን ለመቅጣት ወይም እምነታቸውን ለመፈተን እንደሆነ ያምናሉ። የሰሜን አሜሪካ እስላማዊ ማኅበር ፕሬዚዳንት የሆኑት ዶክተር ሳይድ ሰኢድ “መከራ ላገኘናቸው በረከቶች አምላክን ምንጊዜም ማመስገንና የተቸገሩትን መርዳት እንዳለብን” እንደሚያስታውሰን ገልጸዋል።

የአይሁድ እምነት

የአይሁድ እምነት ዓርማ።

የአይሁድ እምነት ሰዎች መከራ የሚደርስባቸው በራሳቸው ጥፋት እንደሆነ ያስተምራል። አንዳንድ አይሁዳውያን፣ ምንም ሳያጠፉ መከራ የደረሰባቸው ሰዎች ከትንሣኤ በኋላ ፍትሕ እንደሚያገኙ ያምናሉ። የካባላ አይሁድ እምነት ደግሞ ሪኢንካርኔሽንን ያስተምራል፤ በዚህ ትምህርት መሠረት አንድ ሰው ለኃጢአቱ ስርየት ማግኘት የሚችልበት ተደጋጋሚ አጋጣሚ ያገኛል።

ቡድሂስቶች

የቡድሂዝም ዓርማ።

ቡድሂስቶች አንድ ሰው አሉታዊ ድርጊቶቹን፣ ስሜቶቹንና ምኞቶቹን ማስወገድ እስኪችል ድረስ በተደጋጋሚ እየተወለደ መከራ እንደሚደርስበት ያምናሉ። አንድ ሰው ጥበብ በማዳበር፣ የጽድቅ ሥራ በማከናወንና አእምሮውን በመገሠጽ ኒርቫና ላይ እንደሚደርስ ማለትም ከየትኛውም ዓይነት መከራ ነፃ እንደሚሆን ያስተምራሉ።

የኮንፊሽየስ ተከታዮች

የኮንፊሽየስ ዓርማ።

የኮንፊሽየስ ተከታዮች መከራ በአብዛኛው የሚደርሰው “በሰዎች ድክመትና ስህተት የተነሳ ነው” ብለው እንደሚያምኑ ኤ ዲክሽነሪ ኦቭ ኮምፓራቲቭ ሪሊጅን ገልጿል። በኮንፊሽየስ ትምህርት መሠረት፣ መልካም አኗኗር በመከተል መከራን መቀነስ ቢቻልም ‘መከራ ከሰው የሚበልጥ አቅም ባላቸው መንፈሳዊ ኃይሎች ምክንያትም ሊመጣ ይችላል። በዚህ ወቅት ሰዎች ዕጣ ፈንታቸውን ከመቀበል ውጭ ምንም ማድረግ አይችሉም።’

የተለያዩ ባዕድ አምልኮዎች

የባዕድ አምልኮዎች ዓርማ።

የተለያዩ ባዕድ አምልኮዎች መከራ የሚደርሰው በመናፍስት ምክንያት እንደሆነ ያስተምራሉ። እንዲህ ያሉ እምነቶች፣ መናፍስት መልካም ዕድል ሊያመጡ ወይም ጉዳት ሊያስከትሉ እንደሚችሉ እንዲሁም አንዳንድ የአምልኮ ሥርዓቶችን በመፈጸም ጉዳቱን መከላከል እንደሚቻል ይገልጻሉ። በመሆኑም አንድ ሰው በሚታመምበት ጊዜ “አዋቂዎች” የሚሰጡት መድኃኒትና የሚፈጽሙት የአምልኮ ሥርዓት የመናፍስቱን ሥራ ለማፍረስ እንደሚያስችል ይታመናል።

ክርስቲያኖች

የክርስትና ዓርማ።

ክርስቲያኖች የዘፍጥረት መጽሐፍ በሚገልጸው መሠረት መከራ የመጣው የመጀመሪያዎቹ ባልና ሚስት በሠሩት ኃጢአት ምክንያት እንደሆነ ያምናሉ። ሆኖም በርካታ የክርስትና ሃይማኖቶች ይህን ትምህርት በርዘውታል። ለምሳሌ አንዳንድ ካቶሊኮች አንድ ሰው መከራ ሲደርስበት መከራውን ‘ለአምላክ እንደ መባ አድርጎ በማቅረብ’ አምላክ ቤተ ክርስቲያኒቱን እንዲባርክ ወይም የእሱ መከራ ለሌላ ሰው መዳን እንዲያስገኝ መጠየቅ እንደሚችል ያስተምራሉ።

ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት

jw.org ላይ የሚገኘውን አምላክ ሁሉንም ሃይማኖቶች ይቀበላል? የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ