የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g20 ቁጥር 2 ገጽ 8-9
  • 2. ለሚደርስብን መከራ ተጠያቂዎቹ እኛው ነን?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • 2. ለሚደርስብን መከራ ተጠያቂዎቹ እኛው ነን?
  • ንቁ!—2020
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ይህን ማወቅ ለምን አስፈለገ?
  • ሊታሰብባቸው የሚገቡ ነጥቦች
  • መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?
  • መጽሐፍ ቅዱስ ምን ያስተምራል?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2017
  • የርዕስ ማውጫ
    ንቁ!—2020
  • ጥያቄ 3፦ አምላክ መከራ እንዲደርስብኝ የሚፈቅደው ለምንድን ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2012
  • መከራ ይህን ያህል የበዛው ለምንድን ነው?
    ንቁ!—2011
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—2020
g20 ቁጥር 2 ገጽ 8-9
አንድ ሰው በአንድ እጁ ሲጋራ፣ በሌላኛው እጁ ደግሞ የተከፈተ የቢራ ጠርሙስ ይዞ ሳሎን ውስጥ ተቀምጦ።

2. ለሚደርስብን መከራ ተጠያቂዎቹ እኛው ነን?

ይህን ማወቅ ለምን አስፈለገ?

በራሳችን ላይ መከራ የምናመጣው እኛው ከሆንን መከራውን መቀነስ የምንችልበት መንገድ ሊኖር ይችላል።

ሊታሰብባቸው የሚገቡ ነጥቦች

ከዚህ በታች ለተጠቀሱት መከራዎች መድረስ የሰዎች አስተዋጽኦ ምን ያህል ነው?

  • ቡጢ ለመሰንዘር የተጨበጠ እጅ ምልክት፣ ጥቃትን ያመለክታል።

    ጥቃት

    የዓለም የጤና ድርጅት እንደገለጸው ከ4 አዋቂዎች መካከል 1ዱ በልጅነቱ አካላዊ ጥቃት ደርሶበታል፤ ከ3 ሴቶች መካከል 1ዷ ደግሞ በሕይወቷ ውስጥ በሆነ ወቅት ላይ አካላዊ ወይም ፆታዊ ጥቃት (አሊያም ሁለቱም) ይደርስባታል።

  • የመቃብር ድንጋይ ምልክት፣ የመቃብር ቦታን ያመለክታል።

    ሞት

    የዓለም የጤና ድርጅት ያሳተመው ዎርልድ ኸልዝ ስታትስቲክስ 2018 የተባለ ጽሑፍ እንደገለጸው “በ2016 በዓለም ዙሪያ 477,000 ገደማ የሚሆኑ ሰዎች ተገድለዋል።” ይህ አኃዝ በዚያው ዓመት በጦርነት ወይም በእርስ በርስ ግጭት ምክንያት እንደሞቱ የሚገመቱትን 180,000 ገደማ የሚሆኑ ሰዎች አይጨምርም።

  • የልብ ምልክት፣ የጤና ችግሮችን ያመለክታል።

    የጤና እክል

    ናሽናል ጂኦግራፊክ በተሰኘው መጽሔት ላይ በወጣ አንድ ርዕስ ላይ ፍራን ስሚዝ የተባለች ጸሐፊ እንዲህ ብላለች፦ “ከአንድ ቢሊዮን የሚበልጡ ሰዎች ትንባሆ ያጨሳሉ፤ ትንባሆ ደግሞ ለሚከተሉት ቀንደኛ የሞት መንስኤ የሆኑ አምስት የጤና እክሎች ያጋልጣል፦ የልብ በሽታ፣ አንጎል ውስጥ ደም መፍሰስ፣ የመተንፈሻ አካላት ኢንፌክሽን፣ የአየር ቧንቧ መደፈንና የሳንባ ካንሰር።”

  • የሚዛን ምልክት፣ ኢፍትሐዊነትን ያመለክታል።

    ኢፍትሐዊነት

    የሥነ ልቦና ባለሙያ የሆኑት ጄ ዋትስ እንዲህ ብለዋል፦ “ድህነት፣ መድልዎ፣ ዘረኝነት፣ ፆታዊ አድልዎ፣ ስደትና ማኅበራዊ ፉክክር ለአእምሮ ጤና መታወክ ያጋልጣሉ።”

    ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት

    jw.org ላይ የሚገኘውን አምላክ ምድርን የፈጠረው ለምንድን ነው? የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት።

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

ያው ሰው የሆስፒታል አልጋ ላይ ተኝቶ። ሐኪሙ ለሰውየው ሚስት ስለ ባለቤቷ ጤንነት አሳዛኝ ዜና ሲነግራት ሴትየዋ ፊቷን አዙራ።

በዓለም ላይ ለሚደርሰው አብዛኛው መከራ ተጠያቂዎቹ ሰዎች ናቸው።

አብዛኛው መከራ የሚደርሰው ጨቋኝ የሆኑ መንግሥታት፣ ሊያገለግሉት የሚገባውን ሕዝብ በመበደላቸው ምክንያት ነው።

“ሰው ሰውን የገዛው ለጉዳቱ ነው።”—መክብብ 8:9

የሚደርስብንን መከራ መቀነስ እንችላለን።

የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያ ጤንነታችንን ለማሻሻልና ከሌሎች ጋር በሰላም ለመኖር ይረዳናል።

“የሰከነ ልብ ለሰውነት ሕይወት ይሰጣል፤ ቅናት ግን አጥንትን ያነቅዛል።”—ምሳሌ 14:30

“የመረረ ጥላቻ፣ ቁጣ፣ ንዴት፣ ጩኸትና ስድብ ሁሉ እንዲሁም ክፋት ሁሉ ከእናንተ መካከል ይወገድ።”—ኤፌሶን 4:31

ለሚደርስብን መከራ ተጠያቂዎቹ እኛው ነን?

መጽሐፍ ቅዱስ “አንድ ሰው ምንም ዘራ ምን ያንኑ መልሶ ያጭዳል” ይላል። (ገላትያ 6:7) አንዳንድ ጊዜ መከራ የሚደርስብን በምናደርጋቸው ምርጫዎች የተነሳ ነው። ሐኪሞች የተመጣጠነ ምግብ እንድንመገብ፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እንድናደርግ እንዲሁም እንደ ማጨስ ያሉ ጎጂ ልማዶችን እንድናስወግድ የሚመክሩን ለዚህ ነው። ያም ቢሆን የሁሉም መከራ መንስኤ ሰዎች ናቸው ሊባል አይችልም። ብዙ ሰዎች ድንገተኛ አደጋ፣ የተፈጥሮ አደጋ እና ሌሎች አሳዛኝ ነገሮች የሚደርሱባቸው ያለጥፋታቸው ነው።

ታዲያ ጥሩ ሰዎች መከራ የሚደርስባቸው ለምንድን ነው?

ጥያቄ 3⁠ን ተመልከት።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ