የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g20 ቁጥር 3 ገጽ 12-13
  • ፍቅር ለማሳየት ጥረት አድርግ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ፍቅር ለማሳየት ጥረት አድርግ
  • ንቁ!—2020
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • እንዲህ አለማድረግ ምን ችግር አለው?
  • የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያ
  • ምን ማድረግ ትችላለህ?
  • የጭፍን ጥላቻን ግድግዳ ማፍረስ ችለዋል
    ንቁ!—2020
  • ጭፍን ጥላቻ—አንተንም አጥቅቶህ ይሆን?
    ንቁ!—2020
  • የፍትሕ መዛባትን መታገል እፈልግ ነበር
    መጽሐፍ ቅዱስ የሰዎችን ሕይወት ይለውጣል
  • ከጭፍን ጥላቻ የጸዳ ዓለም ይመጣ ይሆን?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2013
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—2020
g20 ቁጥር 3 ገጽ 12-13
አንዲት ሕንዳዊ የአንዲትን በዕድሜ የገፉ ነጭ ሴት ዕቃ ተሸክማ ደረጃ እንዲወጡ ስትረዳቸው።

ፍቅር ለማሳየት ጥረት አድርግ

እንዲህ አለማድረግ ምን ችግር አለው?

ጭፍን ጥላቻ በአንዴ ከውስጣችን አይወገድም። አንድን ቫይረስ ለማጥፋት ጊዜና ጥረት እንደሚጠይቅ ሁሉ ጭፍን ጥላቻን ለማጥፋትም ጊዜና ጥረት ይጠይቃል። ታዲያ ጭፍን ጥላቻን ለማስወገድ ምን ማድረግ ትችላለህ?

የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያ

1. የእስያ ተወላጅ የሆነ አንድ ሰው የቡና ኩባያዎች ለያዘ አንድ ጥቁር ሰው በር ከፍቶ ሲይዝለት። 2. ያ ጥቁር ሰው ደግሞ የያዘውን ቡና በቅድሙ ሥዕል ላይ ላለችው ሕንዳዊት ጨምሮ ለሥራ ባልደረቦቹ ሲያካፍል።

“ፍቅርን ልበሱ፤ ፍቅር ፍጹም የሆነ የአንድነት ማሰሪያ ነውና።”—ቆላስይስ 3:14

ከዚህ ጥቅስ ምን ትምህርት እናገኛለን? የደግነት ተግባር ሰዎችን እርስ በርስ ያቀራርባል። ለሌሎች ፍቅር ባሳየህ መጠን በውስጥህ ያለው ጭፍን ጥላቻም የዚያኑ ያህል ይቀንሳል። ለሰዎች ያለህ ፍቅር እየጨመረ ከሄደ ጥላቻ ወይም ንቀት በልብህ ውስጥ ቦታ አያገኙም።

ምን ማድረግ ትችላለህ?

1. አንዲት ሕንዳዊ የአንዲትን በዕድሜ የገፉ ነጭ ሴት ዕቃ ተሸክማ ደረጃ እንዲወጡ ስትረዳቸው። 2. በዕድሜ የገፉት ነጭ ሴት ለጎረቤታቸው ማለትም በቅድሙ ሥዕል ላይ ላለው እስያዊ ሰው ኩኪስ ሲሰጡት።

በጭፍን ለምትጠላቸው ሰዎች ፍቅር ማሳየት የምትችልባቸውን አንዳንድ መንገዶች አስብ። ትልቅ ነገር ማድረግ እንዳለብህ ሊሰማህ አይገባም። ከሚከተሉት ነገሮች መካከል ቢያንስ አንዱን ለማድረግ ሞክር፦

ፍቅር ለማሳየት ስትል የምታደርገው ትንሹ ነገር ጭፍን ጥላቻን በማስወገድ ረገድ ትልቅ አስተዋጽኦ ያበረክታል

  • በር ከፍተህ በመያዝ ወይም በሕዝብ መጓጓዣ ላይ ወንበርህን በመልቀቅ ጥሩ ምግባር አሳይ።

  • የአንተን ቋንቋ ጥርት አድርገው መናገር ባይችሉም እንኳ ከእነሱ ጋር ለመጨዋወት ጥረት አድርግ።

  • ግራ የሚገባህ ነገር በሚያደርጉበት ጊዜ በትዕግሥት ለማለፍ ሞክር።

  • ስላስጨነቋቸው ነገሮች ሲነግሩህ በአዘኔታ ስሜት አዳምጣቸው።

እውነተኛ ታሪክ፦ ናዛሬ (ጊኒ ቢሳው)

“በአንድ ወቅት ለስደተኞች ጭፍን ጥላቻ ነበረኝ። አብዛኞቹ ስደተኞች አላግባብ የመንግሥትን ድጎማ ለማግኘት እንደሚሞክሩና ወንጀለኞች እንደሆኑ ሲነገር እሰማ ነበር። ይህም ለእነሱ ጥሩ አመለካከት እንዳይኖረኝ አድርጓል። ሆኖም ጭፍን ጥላቻ እንዳለብኝ አይሰማኝም ነበር። ምክንያቱም አብዛኞቹ ሰዎች ለስደተኞች እንደ እኔ ዓይነት አመለካከት አላቸው።

“ከጊዜ በኋላ ግን ለስደተኞች ያለኝ አሉታዊ አመለካከት ጭፍን ጥላቻ እንደሆነ ተገነዘብኩ። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኘው ጠቃሚ ምክር ለእነሱ ፍቅር እንዳሳይ ረድቶኛል። አሁን እንደ ድሮው አልርቃቸውም። ከዚህ ይልቅ ሰላም እላቸዋለሁ እንዲሁም አነጋግራቸዋለሁ። እያንዳንዳቸውን በግለሰብ ደረጃ ለማወቅ ጥረት አደርጋለሁ። አሁን ለእነሱ ጥሩ አመለካከት አለኝ። ከእነሱ ጋር መሆን ያስደስተኛል።”

“የፍትሕ መዛባትን መታገል እፈልግ ነበር”

ራፊካ ሞሪስ

ራፊካ የዘር መድልዎን ለመዋጋት አንድን አብዮታዊ ቡድን ተቀላቅላ ነበር። የይሖዋ ምሥክሮች በሚያደርጉት አንድ ትልቅ ስብሰባ ላይ ከተገኘች በኋላ ግን ትፈልገው የነበረውን አንድነት እንዳገኘች ተሰማት።

ራፊካ ሞሪስ፦ የፍትሕ መዛባትን መታገል እፈልግ ነበር የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት። የቪዲዮውን ርዕስ jw.org/am ላይ ፈልግ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ