የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g21 ቁጥር 1 ገጽ 15
  • አንተም ጥበብ ማግኘት ትችላለህ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • አንተም ጥበብ ማግኘት ትችላለህ
  • ንቁ!—2021
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • አምላክ እሱ የሚሰጠውን ጥበብ በማወቅ ጥቅም እንድታገኝ ጋብዞሃል
  • አምላክ የሚሰጠውን ጥበብ አንተም መማር ትችላለህ
  • አምላክን መስማት የምንችለው እንዴት ነው?
    አምላክን ስማ የዘላለም ሕይወት ታገኛለህ
  • አምላክ አለ? ይህን ማወቅ ምን ለውጥ ያመጣል?
    ንቁ!—2015
  • ትክክል ወይስ ስህተት? ለእያንዳንዳችን የተተወ ምርጫ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2024
  • አምላክን የሚያስደስቱ እውነተኛ ትምህርቶች
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2005
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—2021
g21 ቁጥር 1 ገጽ 15

አንተም ጥበብ ማግኘት ትችላለህ

“ቅዱሳን መጻሕፍት ሁሉ በአምላክ መንፈስ መሪነት የተጻፉ ናቸው።” (2 ጢሞቴዎስ 3:16) ጥቅሱ ላይ “በአምላክ መንፈስ መሪነት” ሲል ሁሉን ቻይ የሆነው አምላክ ሐሳቡን በመጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፊዎች አእምሮ ውስጥ እንዳስቀመጠ መናገሩ ነው።

አጭር መረጃ ስለ መጽሐፍ ቅዱስ

  • የመጽሐፍ የተወሰኑ ገጾች።

    66

    መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያሉት ንዑሳን መጻሕፍት ወይም ክፍሎች ብዛት

  • እየጻፈ ያለ እጅ፤ ከላይ ብርሃን በርቶበታል።

    40

    አምላክ መጽሐፍ ቅዱስን ለማስጻፍ የተጠቀመባቸው ሰዎች ብዛት

  • ጊዜ መቁጠሪያ።

    1513 ዓ.ዓ.

    መጽሐፍ ቅዱስ መጻፍ የጀመረበት ዓመት፤ ከ3,500 ከሚበልጡ ዓመታት በፊት ማለት ነው!

  • የተለያዩ ቋንቋዎች ፊደላት።

    3,000+

    ሙሉው መጽሐፍ ቅዱስ ወይም በከፊል የሚገኝባቸው ቋንቋዎች ብዛት

አምላክ እሱ የሚሰጠውን ጥበብ በማወቅ ጥቅም እንድታገኝ ጋብዞሃል

“የሚጠቅምህን ነገር የማስተምርህ፣ ልትሄድበትም በሚገባህ መንገድ የምመራህ እኔ ይሖዋ . . . ነኝ። ትእዛዛቴን ብትሰማ ምንኛ መልካም ነው! እንዲህ ብታደርግ ሰላምህ እንደ ወንዝ፣ ጽድቅህም እንደ ባሕር ሞገድ ይሆናል።”—ኢሳይያስ 48:17, 18

እነዚህን ቃላት አምላክ ለአንተ በግልህ ያቀረበልህ ግብዣ አድርገህ ተመልከታቸው። አምላክ ውስጣዊ ሰላም እንድታገኝና ሁልጊዜ ደስተኛ እንድትሆን ይፈልጋል፤ ሰላምና ደስታ እንድታገኝ ሊረዳህም ይችላል።

አምላክ የሚሰጠውን ጥበብ አንተም መማር ትችላለህ

“ምሥራቹ ለብሔራት ሁሉ መሰበክ አለበት።”—ማርቆስ 13:10

እዚህ ላይ የተጠቀሰው ‘ምሥራች’ ይሖዋ መከራን እንደሚያስወግድ፣ ምድርን ገነት እንደሚያደርግና በሞት የተለዩንን ሰዎች እንደሚያስነሳ የሰጠውን ተስፋ ያካትታል። የይሖዋ ምሥክሮች ይህን የመጽሐፍ ቅዱስ መልእክት በዓለም ዙሪያ እየሰበኩ ነው።

መጽሐፍ ቅዱስን ሳነብ ግራ ላጋባኝ ጥያቄ መልስ አገኘሁ

“ከትንሽነቴ ጀምሮ የፈጣሪ ማንነት ግራ ያጋባኝ ነበር። ‘እያንዳንዱ አገር የራሱ አምላክ ወይም ፈጣሪ ሊኖረው የሚችለው እንዴት ነው?’ ብዬ አስብ ነበር። ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ሮም 3:29⁠ን ሳነብ በጣም ተደሰትኩ፤ ጥቅሱ፣ እውነተኛው አምላክ የሕዝቦች ሁሉ አምላክ እንደሆነ ይናገራል። በተጨማሪም ፈጣሪያችን ይሖዋ የተባለ ስም አለው፤ ወዳጆቹ እንድንሆንም ይፈልጋል።”—ራኬሽ

ራኬሽ።
    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ