የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g24 ቁጥር 1 ገጽ 10-12
  • ለቤተሰብ አክብሮት ማሳየት ቀረ እንዴ?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ለቤተሰብ አክብሮት ማሳየት ቀረ እንዴ?
  • ንቁ!—2024
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ለቤተሰብ አክብሮት ማሳየት አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?
  • ምን ማድረግ ትችላለህ?
  • ምን ጥረት እያደረግን ነው?
  • እርዳታ ማግኘት ትችላለህ
    ንቁ!—2020
  • ለቤተሰቦች የሚሆን ተጨማሪ እርዳታ
    ንቁ!—2018
  • ለዕለት ተዕለት ሕይወት የሚጠቅም ምክር JW.ORG ላይ መፈለግ
    ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2022
  • ለጥናት የሚረዱ ሐሳቦች
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2023
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—2024
g24 ቁጥር 1 ገጽ 10-12
አንድ ባል ሚስቱ ልታነጋግረው ስትሞክር ተበሳጭቶ ስልኩን ሲነካካ። ትንሽ ልጃቸው እያያቸው ነው።

ለቤተሰብ አክብሮት ማሳየት ቀረ እንዴ?

ለቤተሰብ አክብሮት ማሳየት አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?

ለቤተሰብ አባላት አክብሮት ማሳየት ባሎች፣ ሚስቶችም ሆኑ ልጆች ሰላም በሰፈነበት ቤተሰብ ውስጥ እንዲኖሩ ያስችላል።

  • ዘ ሰቨን ፕሪንሲፕልስ ፎር ሜኪንግ ሜሬጅ ወርክ የተባለው መጽሐፍ እንደሚገልጸው ባለትዳሮች እርስ በርስ የሚከባበሩ ከሆነ “በትላልቅ መንገዶች ብቻ ሳይሆን በየዕለቱ በትናንሽ መንገዶችም” ፍቅራቸውን ይገላለጻሉ።

  • አንዳንድ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ለሌሎች አክብሮት ማሳየትን የተማሩ ልጆች ለራሳቸው ጥሩ ግምት ያዳብራሉ፤ ከወላጆቻቸው ጋር መልካም ግንኙነት ይኖራቸዋል፤ እንዲሁም ለሥነ ልቦናዊ ችግሮች የመዳረጋቸው አጋጣሚ ጠባብ ይሆናል።

ምን ማድረግ ትችላለህ?

ከቤተሰብህ ጋር ሆነህ ዕቅድ አውጣ። በመጀመሪያ “የአክብሮትን” ምንነት በተመለከተ ከትዳር ጓደኛህ ጋር የጋራ አቋም ይኑራችሁ። ከዚያም ሁሉም የቤተሰቡ አባላት አክብሮት ለማሳየት የትኞቹን ነገሮች ማድረግ፣ ከየትኞቹ ነገሮች ደግሞ መቆጠብ እንዳለባቸው በዝርዝር ጻፉ። በመጨረሻም ከሁሉም የቤተሰቡ አባላት ስለሚጠበቀው ነገር የጋራ መግባባት ላይ እንድትደርሱ ልጆቻችሁ ባሉበት በቤተሰብ ደረጃ ተወያዩ።

“የትጉ ሰው ዕቅድ ለስኬት ያበቃዋል።”—ምሳሌ 21:5

ጥሩ ምሳሌ ሁን። የቤተሰብህ አባላት ስህተት ሲሠሩ ትተቻቸዋለህ? አመለካከታቸውን ሲገልጹ ታሾፍባቸዋለህ? አሊያም ደግሞ ሲያነጋግሩህ ችላ ትላቸዋለህ? ወይም ጣልቃ ገብተህ ታቋርጣቸዋለህ?

ጠቃሚ ምክር፦ የትዳር አጋርህና ልጆችህ የአንተን አክብሮት ማትረፍ እንዳለባቸው ከማሰብ ይልቅ ለእነሱ አክብሮት የማሳየት ግዴታ እንዳለብህ አስብ።

“አንዳችሁ ሌላውን ለማክበር ቀዳሚ ሁኑ።”—ሮም 12:10

አለመግባባቶችን በአክብሮት አስተናግድ። ሐሳብህን በምትገልጽበት ጊዜ “አንተ ሁሌም እንደዚህ ነህ” ወይም “አንቺ ሁሌም እንደዚህ ነሽ” እንደሚሉት ያሉ አባባሎችን አትጠቀም። እንዲህ ያለው የሰላ ትችት የቤተሰብህን አባላት ስሜት ሊጎዳና ትንሹን አለመግባባት ወደ ከባድ ግጭት ሊያሳድገው ይችላል።

“የለዘበ መልስ ቁጣን ያበርዳል፤ ክፉ ቃል ግን ቁጣን ያነሳሳል።”—ምሳሌ 15:1

አንዲት ወጣት jw.org ላይ ቪዲዮ ስትመለከት።

ምን ጥረት እያደረግን ነው?

የይሖዋ ምሥክሮች፣ የቤተሰብ አባላት አንዳቸው ሌላውን በአክብሮት እንዲይዙ ያበረታታሉ። ስለዚህ ጉዳይ የሚያብራሩ በርካታ ርዕሶችን፣ መጽሐፎችን፣ ብሮሹሮችንና ቪዲዮዎችን አውጥተናል። ሁሉንም በነፃ ማግኘት ይቻላል።

ለባለትዳሮች፦ ለቤተሰብ የሚለው ዓምድ ከሚከተሉት ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ለባሎችና ለሚስቶች ግሩም ምክር ይዟል፦

  • ጥሩ አድማጭ መሆን

  • ኩርፊያን ማስወገድ

  • መጨቃጨቅ ማቆም

(jw.org ላይ “ለቤተሰብ” ብለህ ፈልግ።)

ለወላጆች፦ ለቤተሰብ የሚለው ዓምድ ወላጆች በሚከተሉት አቅጣጫዎች ረገድ ልጆቻቸውን እንዲያሠለጥኑ የሚረዳ ጠቃሚ ምክር ይዟል፦

  • ታዛዥ መሆን

  • የቤት ውስጥ ሥራዎችን መሥራት

  • “እባክህ” እና “አመሰግናለሁ” ማለት

(jw.org ላይ “ልጆች ማሳደግ” እና “በአሥራዎቹ ዕድሜ ላይ የሚገኙ ልጆችን ማሳደግ” ብለህ ፈልግ።)

ወጣቶች የሚጠይቋቸው ጥያቄዎችና ተግባራዊ መሆን የሚችሉ መልሶች፣ ጥራዝ 1 ላይ የሚገኘውን “ወላጆች የሚጠይቋቸው ጥያቄዎች” የሚለውን ተጨማሪ ክፍልም ተመልከት። (jw.org ላይ “ወላጆች የሚጠይቋቸው ጥያቄዎች” ብለህ ፈልግ።)

ለወጣቶች፦ jw.org ላይ የሚገኘው ታዳጊዎች እና ወጣቶች የሚለው ዓምድ በሚከተሉት ጉዳዮች ረገድ ወጣቶችን የሚረዱ ርዕሶችን፣ ቪዲዮዎችንና መልመጃዎችን ይዟል፦

  • ከወላጆቻቸው እንዲሁም ከወንድሞቻቸውና ከእህቶቻቸው ጋር ተስማምቶ መኖር

  • ወላጆቻቸው ያወጧቸውን ሕጎች በተመለከተ እነሱን በአክብሮት ማነጋገር

  • የወላጆቻቸውን አመኔታ ማትረፍ

(jw.org ላይ “ታዳጊዎች እና ወጣቶች” ብለህ ፈልግ።)

jw.org የተባለውን ድረ ገጽ በነፃ መጠቀም ይቻላል። ምንም ዓይነት ክፍያ ወይም የአባልነት ምዝገባ የለም፤ የግል መረጃ ማስገባትም አያስፈልግም።

ጆሴፍ ኢሬንቦጌን።

ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት

ጆሴፍ ኢሬንቦጌን ትዳር በመሠረተበት ወቅት ዓመፀኛና የዕፅ ሱሰኛ ነበር። ከይሖዋ ምሥክሮች ጋር መጽሐፍ ቅዱስን ማጥናቱ የቤተሰብ ሕይወቱን ያሻሻለለት እንዴት እንደሆነ ለማወቅ “ለራሴም ሆነ ለሴቶች አክብሮት ማሳየትን ተማርኩ” የሚለውን ርዕስ jw.org ላይ ፈልግ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ