ክርስቲያናዊ ሕይወት
ለዕለት ተዕለት ሕይወት የሚጠቅም ምክር Jw.org ላይ መፈለግ
አስቸጋሪ በሆኑት በእነዚህ የመጨረሻዎቹ ቀናት የተለያዩ ተፈታታኝ ሁኔታዎች ያጋጥሙናል፤ የአምላክ ቃል እነዚህን ተፈታታኝ ሁኔታዎች ለመወጣት ያስታጥቀናል። (2ጢሞ 3:1, 16, 17) ያም ቢሆን አንዳንድ ጊዜ፣ ላለንበት ሁኔታ የሚሠራ የመጽሐፍ ቅዱስ መሠረታዊ ሥርዓት ለማግኘት እገዛ ሊያስፈልገን ይችላል። ለምሳሌ ልጆችን ለማሳደግ የሚረዳ ምክር እየፈለግህ ይሆን? የእምነት ፈተና ያጋጠመህ ወጣት ነህ? የትዳር ጓደኛህን በሞት በማጣትህ በሐዘን ተደቁሰሃል? ታዲያ ለምን jw.orgን አትቃኝም? እነዚህንም ሆነ ሌሎች በርካታ ተፈታታኝ ሁኔታዎችን ለመወጣት የሚረዱ የመጽሐፍ ቅዱስ መሠረታዊ ሥርዓቶችን የት እንደምታገኝ ይመራሃል።—ምሳሌ 2:3-6
ከjw.org መነሻ ገጽ ላይ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቶች የሚለውን ዓምድ ጠቅ አድርግ። (ምስል 1ን ተመልከት።) ከተከፈተልህ ዝርዝር ላይ የምትፈልገውን ዓምድ ምረጥ። ወይም ላይብረሪ > ተከታታይ ርዕሶች የሚለው ውስጥ ገብተህ የምትፈልገውን ዓምድ ምረጥ። (ምስል 2ን ተመልከት።) JW ላይብረሪ ላይም እነዚህኑ ዓምዶች ማግኘት ትችላለህ።a በሁለቱም ቦታዎች ላይ ርዕሶቹን በመቃኘት የምትፈልገውን ርዕስ መምረጥ ትችላለህ። ሌላው አማራጭ ደግሞ jw.org ላይ በሚገኘው “ፈልግ” በሚለው ሣጥን ውስጥ የምትፈልገውን ርዕሰ ጉዳይ ማስገባት ነው።
“ፈልግ” በሚለው ሣጥን ውስጥ የሚከተሉትን ርዕሰ ጉዳዮች ጻፍ፤ ከዚያም ማንበብ የምትፈልጋቸውን ርዕሶች ለይተህ አስቀምጥ።
ልጆች ማሳደግ
የወጣቶች ጭንቀት
የትዳር ጓደኛ ሞት
a የአንዳንዶቹን ዓምዶች የተሟላ ይዘት ማግኘት የሚቻለው jw.org ላይ ብቻ ነው።