የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • my ታሪክ 69
  • አንዲት ልጅ አንድ ኃያል ሰው ረዳች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • አንዲት ልጅ አንድ ኃያል ሰው ረዳች
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች መማሪያ መጽሐፌ
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የመርዳት ፍላጎት ነበራት
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2008
  • የሠራዊቱ አለቃና ትንሿ ልጅ
    ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ምን ትማራለህ?
  • እምቢተኛ የነበረ ቢሆንም በኋላ ላይ ታዛዥ ሆኗል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2012
  • ስግብግብነት ግያዝን ለውድቀት ዳረገው
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2012
ለተጨማሪ መረጃ
የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች መማሪያ መጽሐፌ
my ታሪክ 69

ምዕራፍ 69

አንዲት ልጅ አንድ ኃያል ሰው ረዳች

ይቺ ትንሽ ልጅ ምን እያለች እንደሆነ ታውቃለህ? ስለ ይሖዋ ነቢይ ስለ ኤልሳዕና እርሱ በይሖዋ እርዳታ ስለፈጸማቸው አስደናቂ ነገሮች ለሴትዮዋ እየነገረቻት ነው። ሴትዮዋ እስራኤላዊት ስላልሆነች ስለ ይሖዋ ምንም አታውቅም። እንግዲያው ልጅቷ እዚህች ሴትዮ ቤት ምን እንደምትሠራ እንመልከት።

ሴትዮዋ ሶርያዊት ናት። ባልዋ የሶርያ ሠራዊት አለቃ ንዕማን ነው። ሶርያውያን ይቺን ትንሽ እስራኤላዊት ልጅ ማርከው አገልጋይዋ እንድትሆን ወደ ንዕማን ሚስት አምጥተዋት ነበር።

ንዕማን የሥጋ ደዌ የተባለ ከባድ በሽታ ይዞት ነበር። ይህ በሽታ የአንድ ሰው ሥጋ ከሰውነቱ ላይ እየተቀረፈ እንዲወድቅ ሊያደርግ ይችላል። ስለዚህ ልጅቷ የንዕማንን ሚስት ‘ጌታዬ በእስራኤል ወደሚገኘው የይሖዋ ነቢይ ቢሄድ ጥሩ ይመስለኛል። ከያዘው የሥጋ ደዌ ያድነው ነበር’ አለቻት። በኋላ ይህን ነገር ለሴትዮዋ ባል ነገሩት።

ንዕማን ከበሽታው ለመዳን በጣም ፈልጎ ነበር፤ ስለዚህ ወደ እስራኤል ለመሄድ ወሰነ። እዚያ ሲደርስ ወደ ኤልሳዕ ቤት ሄደ። ኤልሳዕ ሂድና በዮርዳኖስ ወንዝ ውስጥ ሰባት ጊዜ ታጠብ ብለህ ንዕማንን ንገረው ብሎ አገልጋዩን ላከው። ንዕማን በጣም ተናደደ። ‘በአገራችን ያሉት ወንዞች በእስራኤል ውስጥ ከሚገኘው ከማንኛውም ወንዝ የተሻሉ ናቸው!’ ሲል ተናገረ። ንዕማን ይህን ከተናገረ በኋላ ተመልሶ ሄደ።

ይሁን እንጂ ከአገልጋዮቹ አንዱ ‘ጌታዬ፣ ኤልሳዕ ከዚህ የበለጠ ከባድ ነገር እንድታደርግ ቢነግርህ ኖሮ እንኳ ታደርገው ነበር። እሱ እንዳለህ ሄደህ ብትታጠብ ምን አለበት?’ አለው። ንዕማን አገልጋዩ ያለውን ተቀብሎ ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ ሄደና ወንዙ ውስጥ ሰባት ጊዜ ተነከረ። ይህን ካደረገ በኋላ ሰውነቱ ታደሰና ጤናማ ሆነ!

ንዕማን በጣም ተደሰተ። ወደ ኤልሳዕ ተመለሰና ‘በምድር ሁሉ ላይ ብቸኛው እውነተኛ አምላክ የእስራኤል አምላክ እንደሆነ ተገንዝቤያለሁ። ስለዚህ እባክህ ይህን ስጦታ ተቀበለኝ’ አለው። ኤልሳዕ ግን ‘በፍጹም፣ አልቀበልም’ አለ። ንዕማንን የፈወሰው ይሖዋ ስለሆነ ስጦታውን መውሰዱ ትክክል እንደማይሆን ኤልሳዕ ያውቅ ነበር። ይሁን እንጂ የኤልሳዕ አገልጋይ የሆነው ግያዝ ስጦታውን ለራሱ መውሰድ ፈልጎ ነበር።

ስለዚህ ግያዝ የሚከተለውን ነገር አደረገ። ንዕማን ከሄደ በኋላ ግያዝ እሱ ላይ ለመድረስ ሮጠ። ‘ኤልሳዕ አሁን እኔን ለመጠየቅ ለመጡት ጓደኞቼ የሚሆን ጥቂት ስጦታ ላክልኝ ብሎሃል’ ብሎ ግያዝ ለንዕማን ነገረው። ሆኖም ይህ ውሸት ነበር። ይሁን እንጂ ንዕማን ይህ ውሸት መሆኑን አያውቅም ነበር፤ ስለዚህ ከያዘው ነገር ላይ የተወሰነውን ለግያዝ ሰጠው።

ግያዝ ወደ ቤት ሲመለስ ኤልሳዕ ግያዝ ያደረገውን ነገር አውቆ ነበር። ይሖዋ ነግሮታል። ስለዚህ ‘ይህን መጥፎ ነገር በመሥራትህ የንዕማን የሥጋ ደዌ ወደ አንተ ይተላለፋል’ አለው። እንዳለውም ወዲያውኑ በሽታው ያዘው!

ከዚህ ሁሉ ምን ልንማር እንችላለን? በመጀመሪያ ደረጃ፣ ትንሿ ልጅ እንዳደረገችው ስለ ይሖዋ መናገር አለብን። እንዲህ ማድረጋችን ብዙ ጥቅም ሊያስገኝ ይችላል። ሁለተኛ፣ ንዕማን መጀመሪያ እንደነበረው ኩሩዎች መሆን የለብንም፤ ከዚህ ይልቅ የአምላክ አገልጋዮችን መታዘዝ አለብን። በሦስተኛ ደረጃ ደግሞ ግያዝ እንዳደረገው መዋሸት የለብንም። መጽሐፍ ቅዱስን በማንበባችን ብዙ ትምህርት ማግኘት አልቻልንምን?

2 ነገሥት 5:​1-27

የአንቀጾቹ ጥያቄዎች

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ