የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • lfb ትምህርት 51 ገጽ 124-ገጽ 125 አን. 2
  • የሠራዊቱ አለቃና ትንሿ ልጅ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የሠራዊቱ አለቃና ትንሿ ልጅ
  • ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ምን ትማራለህ?
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የመርዳት ፍላጎት ነበራት
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2008
  • እምቢተኛ የነበረ ቢሆንም በኋላ ላይ ታዛዥ ሆኗል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2012
  • አንዲት ልጅ አንድ ኃያል ሰው ረዳች
    የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች መማሪያ መጽሐፌ
  • በድፍረት የተናገረች አንዲት ትንሽ ልጅ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1996
ለተጨማሪ መረጃ
ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ምን ትማራለህ?
lfb ትምህርት 51 ገጽ 124-ገጽ 125 አን. 2
ንዕማን ከሕመሙ እንዲያድነው ወደ ኤልሳዕ በሄደበት ወቅት

ትምህርት 51

የሠራዊቱ አለቃና ትንሿ ልጅ

ከትውልድ አገሯ ርቃ በሶርያ የምትኖር አንዲት እስራኤላዊት ልጅ ነበረች። ይህችን ልጅ የሶርያ ሠራዊት ከቤተሰቧ ለይቶ ወስዷት ነበር። በዚያም ንዕማን የተባለ አንድ የሠራዊት አለቃ ነበር፤ እስራኤላዊቷ ልጅ የንዕማን ሚስት አገልጋይ ሆነች። አብረዋት ያሉት ሰዎች ይሖዋን ባያመልኩም እንኳ ይህች ትንሽ ልጅ ይሖዋን ታመልክ ነበር።

ንዕማን ከባድ የቆዳ በሽታ ነበረበት፤ በዚህ የተነሳ ሁልጊዜ ይሠቃይ ነበር። ትንሿ ልጅ ንዕማንን መርዳት ፈለገች። ስለዚህ የንዕማንን ሚስት እንዲህ አለቻት፦ ‘ባልሽን ሊረዳው የሚችል ሰው አውቃለሁ። እስራኤል ውስጥ ኤልሳዕ የሚባል የይሖዋ ነቢይ አለ። እሱ ባልሽን ከሕመሙ ሊያድነው ይችላል።’

የንዕማን ሚስት ትንሿ ልጅ ያለቻትን ነገር ለባሏ ነገረችው። ንዕማንም ከሕመሙ ለመዳን ጓጉቶ ስለነበር በእስራኤል ወደሚገኘው የኤልሳዕ ቤት ሄደ። ንዕማን፣ ኤልሳዕ ትልቅ አቀባበል ያደርግልኛል ብሎ ጠብቆ ነበር። ኤልሳዕ ግን ራሱ ወጥቶ ንዕማንን ከማነጋገር ይልቅ አገልጋዩን ልኮ ንዕማንን እንዲቀበለውና እንዲህ ብሎ እንዲነግረው አዘዘው፦ ‘ሂድና ዮርዳኖስ ወንዝ ውስጥ ሰባት ጊዜ ታጠብ። ከዚያ ትድናለህ።’

በዚህ ጊዜ ንዕማን በጣም ተቆጣ። እንዲህ አለ፦ ‘እኔ እኮ ይህ ነቢይ የአምላኩን ስም እየጠራ ለየት ያለ ነገር አድርጎ የሚያድነኝ መስሎኝ ነበር። እሱ ግን እስራኤል ውስጥ በሚገኘው በዚህ ወንዝ ውስጥ ታጠብ ይለኛል። ሶርያ ውስጥ ከዚህ የተሻሉ ወንዞች አሉን። እዚያው አልታጠብም ነበር?’ ንዕማን በጣም ተናዶ አካባቢውን ለቆ ሄደ።

ንዕማን በዮርዳኖስ ወንዝ ውስጥ ታጥቦ ሲድን

በኋላ ግን የንዕማን አገልጋዮች አስተሳሰቡን እንዲያስተካክል ረዱት። እንዲህ አሉት፦ ‘ለመዳን ስትል ማንኛውንም ነገር ታደርግ የለ? ይህ ነቢይ እንድታደርግ የነገረህ ነገር ደግሞ በጣም ቀላል ነው። ታዲያ ለምን እሱ ያለህን አታደርግም?’ ንዕማን አገልጋዮቹ እንዳሉት አደረገ። ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ ሄዶ ሰባት ጊዜ ውኃው ውስጥ ብቅ ጥልቅ አለ። ንዕማን ለሰባተኛ ጊዜ ውኃው ውስጥ ገብቶ ሲወጣ ከሕመሙ ሙሉ በሙሉ ዳነ። በጣም ደስ ስላለው ኤልሳዕን ለማመስገን ተመልሶ ሄደ። ኤልሳዕንም ‘እውነተኛው አምላክ ይሖዋ እንደሆነ አሁን አወቅኩ’ አለው። ትንሿ እስራኤላዊት ልጅ ንዕማን ድኖ ወደ ቤት ሲመለስ ስታይ ምን የተሰማት ይመስልሃል?

“ከልጆችና ከሕፃናት አፍ ምስጋና አዘጋጀህ።”—ማቴዎስ 21:16

ጥያቄ፦ ትንሿ እስራኤላዊት ልጅ የንዕማንን ሚስት ለማናገር ስታስብ ምን ተሰምቷት ሊሆን ይችላል? በድፍረት እንድትናገር የረዳት ምን ይመስልሃል?

2 ነገሥት 5:1-19፤ ሉቃስ 4:27

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ