የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • my ታሪክ 105
  • በኢየሩሳሌም ሆኖ መጠባበቅ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • በኢየሩሳሌም ሆኖ መጠባበቅ
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች መማሪያ መጽሐፌ
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት መንፈስ ቅዱስ ተቀበሉ
    ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ምን ትማራለህ?
  • ከጴንጤቆስጤ በፊት በርካቶች አዩት
    ኢየሱስ—መንገድ፣ እውነት፣ ሕይወት
  • ለመጨረሻ ጊዜ ለደቀ መዛሙርቱ የታየባቸው ጊዜያትና የ33 እዘአ የጴንጤቆስጤ ዕለት
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1991
  • በመጨረሻ የተገለጠባቸው ጊዜያትና በ33 እንደ ዘመናችን አቆጣጠር የዋለው ጰንጠቆስጤ
    እስከ ዛሬ ከኖሩት ሁሉ የሚበልጠው ታላቅ ሰው
ለተጨማሪ መረጃ
የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች መማሪያ መጽሐፌ
my ታሪክ 105

ምዕራፍ 105

በኢየሩሳሌም ሆኖ መጠባበቅ

እነዚህ ሰዎች የኢየሱስ ተከታዮች ናቸው። ኢየሱስን በመታዘዝ በኢየሩሳሌም ቆዩ። ሁሉም አንድ ላይ ተሰብስበው ሲጠባበቁ አንድ ኃይለኛ ድምፅ ቤቱን ሞላው። ኃይለኛ ዐውሎ ነፋስ የመጣ ይመስል ነበር። ከዚያም በእያንዳንዱ ደቀ መዝሙር ራስ ላይ የእሳት ነበልባል መታየት ጀመረ። በእያንዳንዳቸው ራስ ላይ ያለውን የእሳት ነበልባል አየኸው? ይህ ምን ያመለክታል?

ይህ ተአምር ነው! ኢየሱስ ወደ ሰማይ ተመልሶ ከአባቱ ጋር ነው፤ እንዲሁም የአምላክን ቅዱስ መንፈስ በተከታዮቹ ላይ እያወረደ ነው። ይህ መንፈስ ምን እንዲያደርጉ እንደገፋፋቸው ታውቃለህ? ሁሉም በተለያዩ ቋንቋዎች መናገር ጀመሩ።

በኢየሩሳሌም የነበሩ ብዙ ሰዎች ኃይለኛ ዐውሎ ነፋስ የሚያሰማውን ዓይነት ድምፅ ሰምተው ምን እየተከናወነ እንዳለ ለማየት መጡ። አንዳንዶቹ ጰንጠቆስጤ በሚባለው የእስራኤላውያን በዓል ላይ ለመገኘት ከሌሎች አገሮች የመጡ ነበሩ። እነዚህ ጎብኚዎች ምንኛ ተደንቀው ይሆን! ደቀ መዛሙርቱ አምላክ ስላከናወናቸው አስደናቂ ነገሮች በእነርሱ ቋንቋዎች ሲናገሩ ሰሙ።

ጎብኚዎቹ ‘እነዚህ በሙሉ የገሊላ ሰዎች ናቸው፤ እኛ በምንኖርበት አካባቢ የሚነገሩትን የተለያዩ ቋንቋዎች እንዴት ሊናገሩ ቻሉ?’ ሲሉ ተናገሩ።

በዚህ ጊዜ ጴጥሮስ ስለ ሁኔታው ሊያብራራላቸው ተነሳ። ኢየሱስ እንዴት እንደ ተገደለና ይሖዋ እንዴት ከሞት እንዳስነሳው ድምፁን ከፍ አድርጎ ለሰዎቹ ነገራቸው። ጴጥሮስ ‘አሁን ኢየሱስ በሰማይ በአምላክ ቀኝ ተቀምጧል፤ ቃል በገባውም መሠረት መንፈስ ቅዱስን አፍስሷል። እነዚህን ተአምራት ያያችሁትና የሰማችሁት በዚህ ምክንያት ነው’ አለ።

ጴጥሮስ እነዚህን ነገሮች ሲናገር ብዙዎቹ ሰዎች በኢየሱስ ላይ በተፈጸመው ነገር በጣም አዘኑ። ‘ማድረግ ያለብን ነገር ምንድን ነው?’ ብለው ጠየቁ። ጴጥሮስ ‘አኗኗራችሁን መለወጥና መጠመቅ አለባችሁ’ አላቸው። ስለዚህ በዚያው ቀን ወደ 3, 000 የሚጠጉ ሰዎች ተጠመቁና የኢየሱስ ተከታዮች ሆኑ።

ሥራ 2:​1-47

የአንቀጾቹ ጥያቄዎች

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ