የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • lfb ትምህርት 94 ገጽ 220-ገጽ 221 አን. 1
  • የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት መንፈስ ቅዱስ ተቀበሉ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት መንፈስ ቅዱስ ተቀበሉ
  • ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ምን ትማራለህ?
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • በኢየሩሳሌም ሆኖ መጠባበቅ
    የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች መማሪያ መጽሐፌ
  • “በመንፈስ ቅዱስ ስም”
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1992
  • ከጴንጤቆስጤ በፊት በርካቶች አዩት
    ኢየሱስ—መንገድ፣ እውነት፣ ሕይወት
  • መጠመቅ ያለብን በማንና በምን ስም ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2010
ለተጨማሪ መረጃ
ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ምን ትማራለህ?
lfb ትምህርት 94 ገጽ 220-ገጽ 221 አን. 1
በኢየሩሳሌም የሚገኙ ሰዎች የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት በየራሳቸው ቋንቋ ሲያነጋግሯቸው ሰምተው ተደነቁ

ትምህርት 94

የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት መንፈስ ቅዱስ ተቀበሉ

ኢየሱስ ወደ ሰማይ ከተመለሰ ከአሥር ቀን በኋላ ደቀ መዛሙርቱ መንፈስ ቅዱስ ተቀበሉ። በ33 ዓ.ም. በተከበረው የጴንጤቆስጤ ዕለት ብዙ ሰዎች በዓሉን ለማክበር ከተለያዩ ቦታዎች ወደ ኢየሩሳሌም መጥተው ነበር። በዚያ ቀን 120 ገደማ የሚሆኑ የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት ሰገነት ላይ በሚገኝ ክፍል ውስጥ ተሰብስበው ነበር። ድንገት አንድ አስደናቂ ነገር ተፈጸመ። እሳት የሚመስል ነገር በእያንዳንዱ ደቀ መዝሙር ራስ ላይ ታየ፤ ከዚያም ሁሉም በተለያዩ ቋንቋዎች መናገር ጀመሩ። እንደ ኃይለኛ ነፋስ ያለ ድምፅ ተሰብስበውበት የነበረውን ቤት ሞላው።

ከተለያዩ አገሮች ወደ ኢየሩሳሌም የመጡ ሰዎች ይህን ድምፅ ሲሰሙ ምን እንደተፈጠረ ለማየት ደቀ መዛሙርቱ ወደተሰበሰቡበት ቤት ሄዱ። እነሱም ደቀ መዛሙርቱ በተለያዩ ቋንቋዎች ሲናገሩ ሲሰሙ በጣም ተደነቁ። እርስ በርሳቸው እንዲህ ተባባሉ፦ ‘እነዚህ ሰዎች የገሊላ ሰዎች አይደሉም እንዴ? ታዲያ በእኛ ቋንቋ መናገር የቻሉት እንዴት ነው?’

ከዚያም ጴጥሮስና ሌሎቹ ሐዋርያት በተሰበሰበው ሕዝብ ፊት ቆሙ። ጴጥሮስም ኢየሱስ የተገደለውና ይሖዋ ከሞት ያስነሳው እንዴት እንደሆነ ለሕዝቡ ተናገረ። እንዲህ አለ፦ ‘አሁን ኢየሱስ በሰማይ ላይ በአምላክ ቀኝ ተቀምጦ ይገኛል፤ እሱም ቃል በገባው መሠረት መንፈስ ቅዱስን አፈሰሰ። እናንተ ያያችሁትና የሰማችሁት ተአምር የተፈጸመው ለዚህ ነው።’

ሰዎቹም ጴጥሮስ የተናገረውን ሲሰሙ ልባቸው ተነክቶ “ታዲያ ምን ብናደርግ ይሻላል?” በማለት ጠየቁ። ጴጥሮስም ‘ከኃጢአታችሁ ንስሐ ግቡ፤ እንዲሁም በኢየሱስ ስም ተጠመቁ። የመንፈስ ቅዱስን ስጦታ ትቀበላላችሁ’ አላቸው። በዚያ ቀን 3,000 ገደማ የሚሆኑ ሰዎች ተጠመቁ። ከዚያ ጊዜ ጀምሮ በኢየሩሳሌም የሚገኙት ደቀ መዛሙርት ቁጥር በከፍተኛ ፍጥነት ማደግ ጀመረ። ሐዋርያቱም ኢየሱስ ያዘዛቸውን ነገር በሙሉ ለደቀ መዛሙርቱ ለማስተማር ሲሉ በመንፈስ ቅዱስ እርዳታ ተጨማሪ ጉባኤዎችን አቋቋሙ።

“ኢየሱስ ጌታ እንደሆነ በአፍህ በይፋ ብትናገር እንዲሁም አምላክ ከሞት እንዳስነሳው በልብህ ብታምን ትድናለህ።”—ሮም 10:9

ጥያቄ፦ በ33 ዓ.ም. በተከበረው የጴንጤቆስጤ ዕለት ምን ተፈጸመ? ብዙ ሰዎች የተጠመቁት ለምንድን ነው?

የሐዋርያት ሥራ 1:15፤ 2:1-42፤ 4:4፤ ዮሐንስ 15:26

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ