የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • gf ትምህርት 9 ገጽ 15
  • የአምላክ ወዳጆች እነማን ናቸው?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የአምላክ ወዳጆች እነማን ናቸው?
  • የአምላክ ወዳጅ መሆን ትችላለህ!
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • በሚሊዮን የሚቆጠሩ መንፈሳዊ ፍጡራን
    የሙታን መናፍስት—ሊረዱህ ወይም ሊጎዱህ ይችላሉን? ደግሞስ በእርግጥ አሉን?
  • መላእክት—“የሕዝብ አገልጋዮች የሆኑ መናፍስት”
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2009
  • መጽሐፍ ቅዱስ ሰዎች ሲሞቱ መላእክት ይሆናሉ ብሎ ያስተምራል?
    ንቁ!—2006
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2014
ለተጨማሪ መረጃ
የአምላክ ወዳጅ መሆን ትችላለህ!
gf ትምህርት 9 ገጽ 15

ትምህርት 9

የአምላክ ወዳጆች እነማን ናቸው?

ኢየሱስ ክርስቶስ የአምላክ መንግሥት ንጉሥ ሆኖ፤ መላእክት የስብከቱን ሥራ ሲመሩ

ኢየሱስ ክርስቶስ የይሖዋ ልጅ፣ እንዲሁም የቅርብ ወዳጁ ነው። ኢየሱስ ሰው ሆኖ ምድር ላይ ከመኖሩ በፊት ኃያል መንፈሳዊ ፍጡር ሆኖ በሰማይ ይኖር ነበር። (ዮሐንስ 17:5) ከዚያም ስለ አምላክ እውነትን ለሰዎች ለማስተማር ወደ ምድር መጣ። (ዮሐንስ 18:37) በተጨማሪም ታዛዥ ሰዎችን ከኃጢአትና ከሞት ለማዳን ሰብዓዊ ሕይወቱን ሰጥቷል። (ሮሜ 6:23) ኢየሱስ አሁን የአምላክ መንግሥት ንጉሥ ሲሆን በዚህ ሰማያዊ መስተዳድር አማካኝነት ምድርን ገነት ያደርጋል።—ራእይ 19:16

መላእክትም የአምላክ ወዳጆች ናቸው። መላእክት ሕልውናቸውን ያገኙት እንደ ሰው በምድር ላይ አይደለም። አምላክ ምድርን ከመፍጠሩ በፊት እነሱ በሰማይ ተፈጥረው ነበር። (ኢዮብ 38:4-7) መላእክት በሚልዮን የሚቆጠሩ ናቸው። (ዳንኤል 7:10) እነዚህ በሰማይ የሚኖሩ የአምላክ ወዳጆች ሰዎች ስለ ይሖዋ እውነቱን እንዲማሩ ይፈልጋሉ።—ራእይ 14:6, 7

የይሖዋ ምሥክሮች ለአንዲት ሴት ሲሰብኩ

በተጨማሪም አምላክ በምድር ላይ ወዳጆች አሉት፤ ምሥክሮቼ በማለት ይጠራቸዋል። በፍርድ ቤት የሚቀርብ አንድ ምሥክር ስለ አንድ ሰው ወይም ነገር የሚያውቀውን ይናገራል። የይሖዋ ምሥክሮች ስለ ይሖዋና ስለ ዓላማው የሚያውቁትን ሁሉ ለሰዎች ይናገራሉ። (ኢሳይያስ 43:10) እንደ መላእክት ሁሉ ምሥክሮቹም ስለ ይሖዋ እውነቱን እንድታውቅ ሊረዱህ ይፈልጋሉ። አንተም የአምላክ ወዳጅ እንድትሆን ይፈልጋሉ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ