መዝሙር 22
‘ይሖዋ እረኛዬ ነው’
በወረቀት የሚታተመው
(መዝሙር 23)
1. ይሖዋ እረኛዬ ነው፤
ለምን ብዬ ’ፈራለሁ?
ለበጎቹ ከልብ ያስባል፤
መንጋውን ይጠብቃል።
ወደ ’ረፍት ወንዝ ይወስደኛል፤
ነፍሴንም ያድሳታል።
በጽድቅም መንገድ ይመራኛል፣
ስለ ታላቅ ስሙ ሲል።
በጽድቅም መንገድ ይመራኛል፣
ስለ ታላቅ ስሙ ሲል።
2. አልፈራም፣ አልሸበርም፤
በጨለማ ብጓዝም።
እረኛዬ አይለየኝም፤
ያነቃኛል በትሩም።
ራሴን በዘይት ያብሳል፤
ጽዋዬንም ይሞላል።
ታማኝ ፍቅሩ ይከተለኛል፤
በቤቱም ያኖረኛል።
ታማኝ ፍቅሩ ይከተለኛል፤
በቤቱም ያኖረኛል።
3. እረኛዬ አፍቃሪ ነው፤
በደስታ ላወድሰው።
የሱን ደግነት፣ አሳቢነት፣
አውጃለሁ በቅንዓት።
ታማኝ በመሆን ለቃሉ፣
አልወጣም ከመንገዱ።
እሱን ማገልገሌ ክብር ነው፤
ዕድሜ ልኬን ’ማልረሳው።
እሱን ማገልገሌ ክብር ነው፤
ዕድሜ ልኬን ’ማልረሳው።