መዝሙር 79
ደግነት ያለው ኃይል
በወረቀት የሚታተመው
1. እጅግ ደስ ይላል ማወቅ ይሖዋን፤
ከቃሉ ተረዳን፦
ኃይሉ፣ ጥበቡ ታላቅ ቢሆንም
ደግና ፍቅር መሆኑን።
2. ሸክማችንን እንድናሳርፍ
ኢየሱስ ጋብዞናል።
ቀንበሩ ልዝብ፣ ሸክሙ ቀላል፤
እሱ እረፍት ይሰጠናል።
3. አምላክንና ’የሱስን መምሰል፣
ምንጊዜም አለብን።
አዛኞችና ደጎች እንሁን፣
ከልባችን ተነሳስተን።
(በተጨማሪም ሚክ. 6:8ን፣ ማቴ. 11:28-30ን፣ ቆላ. 3:12ን እና 1 ጴጥ. 2:3ን ተመልከት።)