መዝሙር 58
ራሴን ለአምላክ ለመወሰን ያቀረብኩት ጸሎት
በወረቀት የሚታተመው
1. ሰጠሁ ለአንተ ልቤን፤
ይማር ጥበብ፣ እውነትን።
ሰጠሁህ አ’ምሮዬን፤
እንዲያገለግል አንተን።
2. ሰጠሁ እጅና እግሬን፤
ይፈጽሙ ሕግህን።
ሰጠሁህ አንደበቴን፤
ያሰማ ውዳሴህን።
3. ሰጠሁ ላንተ ሕይወቴን፤
ላስቀድም ፈቃድህን።
ሁለመናዬን ሰጠሁ፤
ምንጊዜም ላስደስትህ።
(በተጨማሪም መዝ. 40:8ን፣ ዮሐ. 8:29ን እና 2 ቆሮ. 10:5ን ተመልከት።)