ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | ዘፀአት 15–16
ይሖዋን በመዝሙር አወድሱት
ሙዚቃ በአእምሯችንና በአካላችን ላይ ትልቅ ተጽዕኖ ሊያሳድር ይችላል። መዝሙር መዘመር በይሖዋ አምልኮ ውስጥ ትልቅ ቦታ አለው።
ሙሴና አስራኤላውያን በቀይ ባሕር ላይ ያዳናቸውን ይሖዋን በመዝሙር አወድሰውታል
ንጉሥ ዳዊት 4,000 ወንዶችን በቤተ መቅደስ ውስጥ ሙዚቀኞችና ዘማሪዎች ሆነው እንዲያገለግሉ መድቦ ነበር
ኢየሱስ ከመሞቱ በፊት በነበረው ሌሊት እሱና ታማኝ ሐዋርያቱ ይሖዋን በመዝሙር አወድሰውታል
ይሖዋን በመዝሙር ማወደስ የምችልባቸው አንዳንድ አጋጣሚዎች የትኞቹ ናቸው?