የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • rk ክፍል 4 ገጽ 10-11
  • አምላክ ማን ነው?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • አምላክ ማን ነው?
  • እውነተኛ እምነት ደስታ ያስገኝልሃል
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • መላእክት ሊረዱህ የሚችሉት እንዴት ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1998
  • መላእክት—“የሕዝብ አገልጋዮች የሆኑ መናፍስት”
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2009
  • መላእክት በሕይወታችን ውስጥ ምን ሚና ይጫወታሉ?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2006
  • መላእክትን በተመለከተ እውነታው ምንድን ነው?
    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
ለተጨማሪ መረጃ
እውነተኛ እምነት ደስታ ያስገኝልሃል
rk ክፍል 4 ገጽ 10-11

ክፍል 4

አምላክ ማን ነው?

ሰዎች ብዙ አማልክት ያመልካሉ። ይሁን እንጂ ቅዱሳን መጻሕፍት እውነተኛው አምላክ አንድ ብቻ እንደሆነ ያስተምራሉ። እውነተኛው አምላክ አቻ የሌለው፣ የሁሉ የበላይና ዘላለማዊ ነው። በሰማይና በምድር ላይ ያሉ ነገሮችን በሙሉ የፈጠረውም ሆነ ለእኛ ሕይወት የሰጠን እሱ ነው። በመሆኑም ልናመልከው የሚገባው እሱን ብቻ ነው።

ሙሴ አሥርቱን ትእዛዛት የሰፈሩበትን የድንጋይ ጽላት ይዞ

‘በመላእክት አማካኝነት እንደተነገረ’ የተገለጸው ሕግ በነቢዩ ሙሴ (ሙሳ) በኩል ተሰጥቷል

አምላክ ስም አለው፤ ስሙም ይሖዋ ይባላል። አምላክ ለሙሴ (ለሙሳ) እንዲህ ብሏቸዋል፦ “እስራኤላውያንን እንዲህ በላቸው፦ ‘የአባቶቻችሁ አምላክ፣ የአብርሃም አምላክ፣ የይስሐቅ አምላክና የያዕቆብ አምላክ የሆነው ይሖዋ ወደ እናንተ ልኮኛል።’ ይህ ለዘላለም ስሜ ነው፤ ከትውልድ እስከ ትውልድ የምታወሰውም በዚህ ነው።” (ዘፀአት 3:​15) ይሖዋ የሚለው ስም በቅዱሳን መጻሕፍት ውስጥ 7,000 ያህል ጊዜ ይገኛል። መዝሙር 83:​18 ስለ አምላክ ሲናገር “ስምህ ይሖዋ የሆነው አንተ፣ አዎ፣ አንተ ብቻ በመላው ምድር ላይ ልዑል [ነህ]” ይላል።

የአምላክን ስም የያዘ የሙት ባሕር ጥቅልል

በሙት ባሕር አካባቢ የተገኘ የአምላክን ስም የያዘ ጥንታዊ የቅዱሳን መጻሕፍት ጥቅልል

ማንም ሰው አምላክን አይቶት አያውቅም። አምላክ ለሙሴ “ማንም ሰው አይቶኝ በሕይወት መኖር ስለማይችል ፊቴን ማየት አትችልም” ብሏቸዋል። (ዘፀአት 33:​20) አምላክ የሚኖረው በሰማይ ስለሆነ ሰው ሊያየው አይችልም። በመሆኑም በጣዖት፣ በሥዕል ወይም አምላክን እንደሚወክል በሚታሰብ ምስል ፊት መጸለይ ስህተት ነው። ይሖዋ አምላክ በነቢዩ ሙሴ አማካኝነት የሚ​ከተለውን ትእዛዝ ሰጥቷል፦ “በላይ በሰማያት ወይም በታች በምድር አሊያም ከምድር በታች በውኃ ውስጥ ባለ በማንኛውም ነገር አምሳል የተቀረጸን ቅርጽ ወይም የተሠራን ምስል ለራስህ አታድርግ። አትስገድላቸው፤ ተታለህም እነሱን አታገልግል፤ ምክንያቱም እኔ አምላክህ ይሖዋ እኔ ብቻ እንድመለክ የምፈልግ . . . አምላክ ነኝ።” (ዘፀአት 20:​2-5) በኋላም አምላክ በነቢዩ ኢሳይያስ በኩል “እኔ ይሖዋ ነኝ። ስሜ ይህ ነው፤ ክብሬን ለሌላ፣ ምስጋናዬንም ለተቀረጹ ምስሎች አልሰጥም” ብሏል።​—⁠ኢሳይያስ 42:8

አንዳንድ ሰዎች በአምላክ ቢያምኑም እሱን ማወቅም ሆነ ከእሱ ጋር መቀራረብ እንዲሁም እሱን መፍራት እንጂ መውደድ ከባድ እንደሆነ ይሰማቸዋል። አንተስ ምን ይመስልሃል? አምላክ ለአንተ በግለሰብ ደረጃ ትኩረት እንደሚሰጥ ይሰማሃል? እሱን ማወቅ አልፎ ተርፎም ከእሱ ጋር መቀራረብ የምትችል ይመስልሃል? እስቲ ቅዱሳን መጻሕፍት ስለ አምላክ ባሕርያት ምን እንደሚሉ እንመልከት።

ምን ብለህ ትመልሳለህ?

  •  አምላክን ማምለክ ያለብን ለምንድን ነው?

  •  የአምላክ ስም ማን ነው?

  •  አምላክን ለማምለክ በጣዖት ወይም በምስል መጠቀም የሌለብን ለምንድን ነው?

  •  አምላክ ፈቃዱን ለመፈጸም ቅዱስ መንፈሱንና መላእክቱን የሚጠቀመው እንዴት ነው?

የአምላክ ቅዱስ መንፈስና መላእክቱ

አምላክ ፈቃዱን የሚፈጽመው እንዴት ነው? አንዱ መንገድ ቅዱስ መንፈሱን በመላክ ነው። የአምላክ መንፈስ፣ ማሰብ የሚችል አካል ወይም መልአክ አይደለም፤ ከዚህ ይልቅ በዓይን የማይታይ የአምላክ ኃይል ነው፤ አምላክ የሚፈልገውን ሁሉ ለማከናወን ገደብ የለሽ በሆነው በዚህ ኃይሉ ይጠቀማል። አምላክ ሰማይንና ምድርን ለመፍጠር ይህን ኃይል ተጠቅሞበታል። “ሰማያት በይሖዋ ቃል፣ በውስጣቸው ያሉትም ሁሉ ከአፉ በሚወጣው መንፈስ ተሠሩ” በማለት የአምላክ ቃል ይናገራል። (መዝሙር 33:⁠6) ምድር ገና በውኃ ተሸፍናና አምላክ ለሰው ልጆች ምቹ መኖሪያ እንድትሆን እያዘጋጃት በነበረበት ወቅት ‘የአምላክ ኃይል በውኃው ላይ ይንቀሳቀስ’ እንደነበር ዘፍጥረት 1:2 ይገልጻል። ከዚያም አምላክ በምድር ላይ ሕይወት ያላቸውን ነገሮች በሙሉ ለመፍጠር በቅዱስ መንፈሱ ተጠቅሟል።

በተጨማሪም አምላክ ፈቃዱን ለመፈጸም መላእክቱን ይጠቀማል። አምላክ መላእክትን የፈጠራቸው ከእሱ ጋር በሰማይ እንዲኖሩ ነው። መላእክት ከፍተኛ ኃይል አላቸው። የአምላክን መልእክት የሚያደርሱ ከመሆኑም በተጨማሪ ሌሎች አስፈላጊ ተግባሮችን ያከናውናሉ። ለምሳሌ ያህል፣ በነቢዩ ሙሴ (ሙሳ) በኩል የተሰጠው ሕግ ‘በመላእክት አማካኝነት የተነገረ ቃል’ እንደሆነ ቅዱሳን መጻሕፍት ገልጸዋል። በተጨማሪም የአምላክ መላእክት በምድር ላይ ያሉትን የአምላክ አገልጋዮች ይረዳሉ። እንዲያውም የአምላክ ቃል፣ መላእክት “መዳን የሚወርሱትን እንዲያገለግሉ የሚላኩ ቅዱስ አገልግሎት የሚያከናውኑ መናፍስት” እንደሆኑ ይናገራል።​—⁠ዕብራውያን 1:​14፤ 2:2

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ