የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • fg ትምህርት 6 ጥያቄ 1-5
  • የሞቱ ሰዎች ምን ተስፋ አላቸው?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የሞቱ ሰዎች ምን ተስፋ አላቸው?
  • ከአምላክ የተላከ ምሥራች!
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የሞቱ ሰዎች ተስፋ አላቸው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2011
  • በሞት የተለዩን የምንወዳቸው ሰዎች ምን ይሆናሉ?
    ወደ ዘላለም ሕይወት የሚመራ እውቀት
  • ስንሞት ምን እንሆናለን?
    ከታላቁ አስተማሪ ተማር
  • ሰው ሲሞት ምን ይሆናል?
    በምድር ላይ በገነት ለዘላለም መኖር ትችላለህ
ለተጨማሪ መረጃ
ከአምላክ የተላከ ምሥራች!
fg ትምህርት 6 ጥያቄ 1-5

ትምህርት 6

የሞቱ ሰዎች ምን ተስፋ አላቸው?

1. ሙታን ምን ተስፋ አላቸው?

አልዓዛር ከሞት ከተነሳ በኋላ ከእህቶቹ ከማርታ እና ከማርያም ጋር በደስታ ተቃቅፈው

ኢየሱስ በኢየሩሳሌም አቅራቢያ ወደምትገኘው የቢታንያ መንደር ሲደርስ ወዳጁ አልዓዛር ከሞተ አራት ቀን አልፎት ነበር። ኢየሱስ ከሟቹ እህቶች ከማርታና ከማርያም ጋር ወደ መቃብሩ ስፍራ ሄደ። ወዲያው በርካታ ሰዎች ተሰበሰቡ። ኢየሱስ፣ አልዓዛርን ከሞት ሲያስነሳው ማርታና ማርያም ምን ያህል ተደስተው እንደሚሆን መገመት ትችላለህ?​—ዮሐንስ 11:21-24, 38-44ን አንብብ።

ማርታ፣ መጽሐፍ ቅዱስ የሞቱ ሰዎችን አስመልክቶ የሚናገረውን ምሥራች ታውቅ ነበር። ይሖዋ ሙታንን እንደሚያስነሳቸውና እንደገና በምድር ላይ መኖር እንደሚችሉ ተገንዝባ ነበር።​—ኢዮብ 14:14, 15ን አንብብ።

2. ሙታን የሚገኙት በምን ዓይነት ሁኔታ ነው?

አዳም ሲፈጠር፤ እንዲሁም ከጊዜ በኋላ ሲሞት

አምላክ አዳምን “አፈር ስለሆንክ ወደ አፈር ትመለሳለህ” ብሎታል።—ዘፍጥረት 3:19

የሰው ልጆች የተሠራነው ከአፈር ነው። (ዘፍጥረት 2:7፤ 3:19) የሰው ልጆች ሥጋዊ አካል የለበስን መንፈሳዊ ፍጥረታት አይደለንም። ሥጋዊ ፍጥረታት ስለሆንን ስንሞት ከእኛ ወጥቶ በሕይወት የሚቀጥል ነገር የለም። ስንሞት አንጎላችን ሥራውን ስለሚያቆም የማሰብ ችሎታችን ይጠፋል። ሙታን ምንም የሚያውቁት ነገር የለም፤ አልዓዛር ከሞት ከተነሳ በኋላ ሞቶ እያለ ስለተመለከተው ሁኔታ ምንም የተናገረው ነገር አልነበረም።​—መዝሙር 146:4ን እና መክብብ 9:5, 6, 10ን አንብብ።

አምላክ የሞቱ ሰዎችን በእሳት ያቃጥላቸዋል? መጽሐፍ ቅዱስ የሞቱ ሰዎች ምንም እንደማያውቁ ስለሚናገር ስለ ገሃነም እሳት የሚገልጸው ትምህርት አምላክን የሚያስነቅፍ የሐሰት ትምህርት እንደሆነ ግልጽ ነው። አምላክ፣ ሰዎችን በእሳት ሊያቃጥል ቀርቶ ሐሳቡ እንኳ ይዘገንነዋል።​—ኤርምያስ 7:31ን አንብብ።

ስንሞት ምን እንሆናለን? የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት

3. ከሙታን ጋር መነጋገር እንችላለን?

የሞቱ ሰዎች መናገርም ሆነ መስማት አይችሉም። (መዝሙር 115:17) ይሁንና ክፉ መላእክት የሞተውን ሰው መስለው በመቅረብ ከሰዎች ጋር ሊነጋገሩ ይችላሉ። (2 ጴጥሮስ 2:4) ይሖዋ ከሞቱ ሰዎች ጋር ለመነጋገር መሞከር እንደሌለብን አስጠንቅቋል።​—ዘዳግም 18:10, 11ን አንብብ።

4. ትንሣኤ የሚያገኙት እነማን ናቸው?

በገነት ውስጥ ከሞት የተነሳ ሰው ስለ አምላክ ይማራል። ከዚያም እሱ ራሱ ከሞት የሚነሱትን ያስተምራል።

በመቃብር ያሉ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ከሞት ተነስተው በምድር ላይ ይኖራሉ። አምላክን ሳያውቁ መጥፎ ድርጊቶችን ሲፈጽሙ የነበሩ ሰዎች እንኳ ይነሳሉ።​—ሉቃስ 23:43ን እና የሐዋርያት ሥራ 24:15ን አንብብ።

ከሞት የተነሱ ሰዎች ስለ አምላክ እውነቱን መማር እንዲሁም ኢየሱስን በመታዘዝ በእሱ ላይ እምነት እንዳላቸው ማሳየት ይችላሉ። (ራእይ 20:11-13) ከሞት ተነስተው መልካም ሥራዎችን የሚሠሩ ሰዎች በምድር ላይ ለዘላለም ይኖራሉ።​—ዮሐንስ 5:28, 29ን አንብብ።

5. ትንሣኤ ስለ ይሖዋ ምን ያስተምረናል?

አምላክ ልጁን ለእኛ ሲል እንዲሞት በመላክ ሙታን ተስፋ እንዲኖራቸው አድርጓል። በመሆኑም ትንሣኤ የይሖዋ ፍቅርና ጸጋ መገለጫ ነው። ሙታን በሚነሱበት ወቅት በተለይ ማግኘት የምትፈልገው ማንን ነው?​—ዮሐንስ 3:16ን እና ሮም 6:23ን አንብብ።

ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት መጽሐፍ ቅዱስ ምን ያስተምረናል? የተባለውን መጽሐፍ ምዕራፍ 6, 7 እና 10 ተመልከት።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ