የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w11 6/1 ገጽ 16-17
  • የሞቱ ሰዎች ተስፋ አላቸው?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የሞቱ ሰዎች ተስፋ አላቸው?
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2011
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የሞቱ ሰዎች ምን ተስፋ አላቸው?
    ከአምላክ የተላከ ምሥራች!
  • በሞት የተለዩን የምንወዳቸው ሰዎች ምን ይሆናሉ?
    ወደ ዘላለም ሕይወት የሚመራ እውቀት
  • በሞት የተለዩህ የምትወዳቸው ሰዎች ያላቸው እውነተኛ ተስፋ
    ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው?
  • ብቸኛው መፍትሔ!
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2006
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2011
w11 6/1 ገጽ 16-17

ከአምላክ ቃል ተማር

የሞቱ ሰዎች ተስፋ አላቸው?

ይህ ርዕሰ ትምህርት በአእምሮህ ሊመላለሱ የሚችሉ ጥያቄዎችን የሚያነሳ ሲሆን መልሶቹን ከመጽሐፍ ቅዱስህ ውስጥ የት ቦታ ላይ ማግኘት እንደምትችልም ይጠቁምሃል። የይሖዋ ምሥክሮች ለጥያቄዎቹ በተሰጡት መልሶች ላይ ከአንተ ጋር ቢወያዩ ደስ ይላቸዋል።

1. ሙታን ምን ተስፋ አላቸው?

ኢየሱስ በኢየሩሳሌም አቅራቢያ ወደምትገኘው የቢታንያ መንደር ሲደርስ ወዳጁ አልዓዛር ከሞተ አራት ቀን አልፎት ነበር። ኢየሱስ ከሟቹ እህቶች ከማርታና ከማርያም ጋር ወደ መቃብሩ ስፍራ ሄደ። ወዲያው በርካታ ሰዎች ተሰበሰቡ። ኢየሱስ አልዓዛርን ከሞት ሲያስነሳው ማርታና ማርያም ምን ያህል ተደስተው እንደሚሆን መገመት ትችላለህ?​—ዮሐንስ 11:20-24, 38-44⁠ን አንብብ።

ማርታ ሙታን እንደሚነሱ እምነት ነበራት። ታማኝ የነበሩት የይሖዋ አገልጋዮች አምላክ እንደገና በምድር ላይ መኖር እንዲችሉ ሲል ወደፊት የሞቱ ሰዎችን እንደሚያስነሳ ከድሮ ጀምሮ ያውቁ ነበር።​—ኢዮብ 14:14, 15⁠ን አንብብ።

2. ሙታን የሚገኙት በምን ዓይነት ሁኔታ ውስጥ ነው?

የሕይወት ኃይል ወይም “መንፈስ” ሰዎችንም ሆነ እንስሳትን ሕያው አድርጎ የሚያቆም ቢሆንም እኛ የሰው ልጆች ሥጋዊ አካል የለበስን መንፈሳዊ ፍጥረታት አይደለንም። (መክብብ 3:19፤ ዘፍጥረት 7:21, 22) እኛ ከአፈር የተሠራን ፍጥረታት ነን። (ዘፍጥረት 2:7፤ 3:19) አንጎላችን ሥራውን ሲያቆም የማሰብ ችሎታችን ይጠፋል። ሙታን ምንም ስለማያውቁ አልዓዛር ከሞት ከተነሳ በኋላ ሞቶ እያለ ስለነበረው ሁኔታ ምንም የተናገረው ነገር አልነበረም።​—መዝሙር 146:4ን እና መክብብ 9:5, 10⁠ን አንብብ።

ከዚህ በግልጽ መመልከት እንደሚቻለው የሞቱ ሰዎች አይሠቃዩም። በመሆኑም አምላክ የሞቱ ሰዎችን ያሠቃያል የሚለው ትምህርት ሐሰት ነው። ይህ አምላክን እንደ መሳደብ ነው። አምላክ፣ ሰዎችን በእሳት የማቃጠልን ሐሳብ እንኳ ይጸየፋል።​—ኤርምያስ 7:31⁠ን አንብብ።

3. ከሙታን ጋር መነጋገር እንችላለን?

የሞቱ ሰዎች መናገር አይችሉም። (መዝሙር 115:17) ይሁንና ክፉ መላእክት የሞተው ሰው መንፈስ መስለው በመቅረብ ከሰዎች ጋር ሊነጋገሩ ይችላሉ። (2 ጴጥሮስ 2:4) ይሖዋ ከሞቱ ሰዎች ጋር ለመነጋገር መሞከር እንደሌለብን አስጠንቅቋል።​—ዘዳግም 18:10, 11⁠ን አንብብ።

4. ትንሣኤ የሚያገኙት እነማን ናቸው?

በሚመጣው አዲስ ዓለም በመቃብር ያሉ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ከሞት ይነሳሉ። ይሖዋን ሳያውቁ መጥፎ ድርጊቶችን ሲፈጽሙ የነበሩ ሰዎች እንኳ ይነሳሉ።​—ሉቃስ 23:43⁠ን እና የሐዋርያት ሥራ 24:15⁠ን አንብብ።

ከሞት የተነሱ ሰዎች አምላክን በተመለከተ እውነቱ ምን እንደሆነና ኢየሱስን በመታዘዝ በእሱ ላይ እምነት እንዳላቸው ማሳየት የሚችሉት እንዴት እንደሆነ ይማራሉ። (ራእይ 20:11-13) ከሞት ተነስተው መልካም ሥራዎችን መሥራታቸውን የቀጠሉ ሰዎች በምድር ላይ ለዘላለም ይኖራሉ። ይሁንና ትንሣኤ ካገኙት መካከል አንዳንዶቹ መጥፎ ድርጊት መፈጸማቸውን ይቀጥላሉ። ይህም ያገኙት ትንሣኤ ‘የፍርድ ትንሣኤ’ እንዲሆንባቸው ያደርጋል።​—ዮሐንስ 5:28, 29⁠ን አንብብ።

5. ትንሣኤ ስለ ይሖዋ ምን ያስተምረናል?

የትንሣኤ ተስፋ እውን ሊሆን የቻለው አምላክ ልጁን ለእኛ ሲል እንዲሞት በመላኩ ነው። በመሆኑም ትንሣኤ የይሖዋ ፍቅርና ጸጋ መገለጫ ነው።​—ዮሐንስ 3:16⁠ን እና ሮም 6:23⁠ን አንብብ።

ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት በይሖዋ ምሥክሮች የተዘጋጀውን ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው? የተባለውን መጽሐፍ ምዕራፍ 6 እና 7ን ተመልከት።

[በገጽ 16 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

አዳም የተፈጠረው ከአፈር ነው

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ