የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • fg ትምህርት 15 ጥያቄ 1-4
  • እውቀት መቅሰምህን መቀጠል ያለብህ ለምንድን ነው?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • እውቀት መቅሰምህን መቀጠል ያለብህ ለምንድን ነው?
  • ከአምላክ የተላከ ምሥራች!
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ወደ አምላክ መቅረብ የምትችለው እንዴት ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2011
  • ከዚህ የሚበልጥ አስደሳች ሕይወት የለም
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2014
  • ወደ አምላክ መቅረብ የምትችለው እንዴት ነው?
    ከአምላክ የተላከ ምሥራች!
  • ‘ወደ አምላክ መቅረብ ይበጀናል!’
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2025
ለተጨማሪ መረጃ
ከአምላክ የተላከ ምሥራች!
fg ትምህርት 15 ጥያቄ 1-4

ትምህርት 15

እውቀት መቅሰምህን መቀጠል ያለብህ ለምንድን ነው?

1. መጽሐፍ ቅዱስን ማጥናትህን መቀጠልህ የሚጠቅምህ እንዴት ነው?

ሁለት ሴቶች በሥራ ቦታቸው ላይ በእረፍት ሰዓት መጽሐፍ ቅዱስ ሲያጠኑ

መሠረታዊ የሆኑ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቶችን በዚህ ብሮሹር አማካኝነት ጠቅለል ባለ መልኩ መመልከትህ ለይሖዋ ያለህን ፍቅር እንዳጠናከረልህ ጥርጥር የለውም። ይህ ፍቅር እያደገ እንዲሄድ ያላሰለሰ ጥረት ማድረግ ያስፈልጋል። (1 ጴጥሮስ 2:2) የዘላለም ሕይወት የማግኘት ተስፋህ የተመካው የአምላክን ቃል እያጠናህ ወደ እሱ በመቅረብህ ላይ ነው።​—ዮሐንስ 17:3ን እና ይሁዳ 21ን አንብብ።

ስለ አምላክ ያለህ እውቀት እያደገ ሲሄድ እምነትህ ይበልጥ ይጠናከራል። እምነት ደግሞ አምላክን ለማስደሰት ያስችልሃል። (ዕብራውያን 11:1, 6) እምነት፣ ንስሐ እንድትገባና በሕይወትህ ውስጥ ጠቃሚ የሆኑ ለውጦችን እንድታደርግ ያነሳሳሃል።​—የሐዋርያት ሥራ 3:19ን አንብብ።

2. ስለ አምላክ ያገኘኸው እውቀት ሌሎችን የሚጠቅመው እንዴት ነው?

አንዲት ሴት ወደ አምላክ ስትጸልይ

ከይሖዋ ጋር ልዩ ዝምድና መመሥረት ትችላለህ

የተማርከውን ነገር ለሌሎች ለመናገር እንደምትፈልግ ግልጽ ነው፤ ሁላችንም ብንሆን ምሥራች ማብሰር ያስደስተናል። መጽሐፍ ቅዱስን ማጥናትህን ስትቀጥል በይሖዋ ላይ ስላለህ እምነትና ስለ ምሥራቹ በመጽሐፍ ቅዱስ ተጠቅመህ ለሰዎች እንዴት እንደምታስረዳ ትማራለህ።​—ሮም 10:13-15ን አንብብ።

አብዛኞቹ ሰዎች ምሥራቹን መጀመሪያ የሚነግሩት ለጓደኞቻቸው ወይም ለዘመዶቻቸው ነው። አንተም ይህንን ስታደርግ ዘዴኛ ሁን። ሃይማኖታቸው ስህተት እንደሆነ ከመግለጽ ይልቅ አምላክ ስለሰጠን ተስፋዎች ንገራቸው። በተጨማሪም አብዛኛውን ጊዜ ሰዎችን የሚማርካቸው የምትናገረው ነገር ሳይሆን የምታሳያቸው ደግነት እንደሆነ አስታውስ።​—2 ጢሞቴዎስ 2:24, 25ን አንብብ።

3. ከአምላክ ጋር ምን ዓይነት ዝምድና መመሥረት ትችላለህ?

የአምላክን ቃል ማጥናትህ በመንፈሳዊ እንድታድግ ይረዳሃል። ውሎ አድሮ ከይሖዋ ጋር በጣም ልዩ ዝምድና መመሥረት ትችላለህ። እንዲያውም የእሱ ቤተሰብ አባል መሆን ትችላለህ።​—2 ቆሮንቶስ 6:18ን አንብብ።

4. እድገት ማድረግህን መቀጠል የምትችለው እንዴት ነው?

የአምላክን ቃል ማጥናትህን በመቀጠል በመንፈሳዊ እድገት ማድረግ ትችላለህ። (ዕብራውያን 5:13, 14) የይሖዋ ምሥክሮች መጽሐፍ ቅዱስ ምን ያስተምረናል? በተባለው መጽሐፍ አማካኝነት መጽሐፍ ቅዱስን እንዲያስጠኑህ ልትጠይቃቸው ትችላለህ። የአምላክን ቃል ይበልጥ በተማርክ መጠን ሕይወትህ ይበልጥ ስኬታማ ይሆናል።​—መዝሙር 1:1-3ን እና 73:27, 28ን አንብብ።

የይሖዋ ምሥክሮች መጽሐፍ ቅዲስ እንዲያጠና ሲጋብዙ

ምሥራቹ የመጣው ደስተኛ አምላክ ከሆነው ከይሖዋ ነው። እሱን ከሚያመልኩ ሰዎች ጋር በመቀራረብ ወደ እሱ ይበልጥ መቅረብ ትችላለህ። (ዕብራውያን 10:24, 25) ይሖዋን ለማስደሰት ጥረት ማድረግህን የምትቀጥል ከሆነ እውነተኛውን ሕይወት ይኸውም የዘላለም ሕይወት ማግኘት ትችላለህ። በእርግጥም በሕይወትህ ልታደርጋቸው ከምትችላቸው ነገሮች በሙሉ የላቀው ወደ አምላክ መቅረብ ነው።​—1 ጢሞቴዎስ 1:11ን እና 6:19ን አንብብ።

ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት መጽሐፍ ቅዱስ ምን ያስተምረናል? የተባለውን መጽሐፍ ምዕራፍ 18 ተመልከት።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ