የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w14 12/1 ገጽ 7
  • ከዚህ የሚበልጥ አስደሳች ሕይወት የለም

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ከዚህ የሚበልጥ አስደሳች ሕይወት የለም
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2014
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • አምላክን እንደምትቀርበው ይሰማሃል?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2014
  • እውቀት መቅሰምህን መቀጠል ያለብህ ለምንድን ነው?
    ከአምላክ የተላከ ምሥራች!
  • ወደ አምላክ መቅረብ ትችላለህ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2019
  • ከይሖዋ ጋር ያለህ ወዳጅነት ምን ያህል ጠንካራ ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2015
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2014
w14 12/1 ገጽ 7
መጽሐፍ ቅዱስን የሚያነብብ ሰው
መጽሐፍ ቅዱስን የሚያነብብ ሰው

የሽፋኑ ርዕሰ ጉዳይ | ወደ አምላክ መቅረብ ትችላለህ

ከዚህ የሚበልጥ አስደሳች ሕይወት የለም

ወደ አምላክ ለመቅረብ ምን ማድረግ ትችላለህ? ልታደርጋቸው የሚገቡ አንዳንድ ነገሮችን ከዚህ በፊት ባሉት ርዕሶች ላይ ተመልክተናል፤ እነሱም የሚከተሉት ናቸው፦

  1. ይሖዋ የተባለውን የአምላክ ስም ማወቅና በዚህ ስም መጠቀም

  2. በመጸለይና መጽሐፍ ቅዱስን በማጥናት ከአምላክ ጋር አዘውትረህ መነጋገር

  3. ምንጊዜም ይሖዋን የሚያስደስተውን ነገር ማድረግ

እየጸለየ ያለ ሰው

የአምላክን ስም በመጠቀም፣ ወደ እሱ በመጸለይ፣ ቃሉን በማጥናትና እሱን የሚያስደስተውን ነገር በማድረግ ወደ አምላክ ቅረብ

እየጸለየ ያለ ሰው

የአምላክን ስም በመጠቀም፣ ወደ እሱ በመጸለይ፣ ቃሉን በማጥናትና እሱን የሚያስደስተውን ነገር በማድረግ ወደ አምላክ ቅረብ

ከእነዚህ መሥፈርቶች አንጻር ራስህን ስትመለከተው ወደ አምላክ ለመቅረብ የሚያስፈልገውን ነገር እያደረግህ እንደሆነ ይሰማሃል? ማሻሻል እንዳለብህ የሚሰማህ ነገር አለ? ይህን ማድረግ ጥረት እንደሚጠይቅ ግልጽ ነው፤ ይሁን እንጂ የሚያስገኘውን ውጤት ተመልከት።

በዩናይትድ ስቴትስ የምትኖረው ጄኒፈር እንዲህ ብላለች፦ “ከአምላክ ጋር የጠበቀ ዝምድና ለመመሥረት ምንም ዓይነት ጥረት ቢደረግ አያስቆጭም። ይህ ዝምድና ብዙ በረከቶችን ያስገኛል፤ ይኸውም በአምላክ ይበልጥ እንድትተማመኑና ስለ ማንነቱ የበለጠ እንድታውቁ ያስችላችኋል፤ ከሁሉ በላይ ግን ለአምላክ ያላችሁ ፍቅር ያድጋል። ከዚህ የሚበልጥ አስደሳች ሕይወት የለም!”

የአምላክ ወዳጅ መሆን የምትፈልግ ከሆነ የይሖዋ ምሥክሮች በዚህ ረገድ ሊረዱህ ፈቃደኞች ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስን ያለክፍያ መማር የምትችልበትን ዝግጅት ሊያደርጉልህ ይችላሉ። በተጨማሪም በአካባቢህ በሚገኝ የይሖዋ ምሥክሮች የመንግሥት አዳራሽ ውስጥ በሚካሄደው በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረተ ስብሰባ ላይ እንድትገኝ እንጋብዝሃለን፤ በስብሰባው ላይ ከአምላክ ጋር ያላቸውን ዝምድና ከፍ አድርገው ከሚመለከቱ ሰዎች ጋር መቀራረብ የምትችልበት አጋጣሚ ታገኛለህ።a እንዲህ ካደረግህ አንተም “ለእኔ ግን ወደ እግዚአብሔር መቅረብ ይሻለኛል” በማለት የተናገረው መዝሙራዊ ዓይነት ስሜት ይኖርሃል።—መዝሙር 73:28

a የይሖዋ ምሥክሮች ስለ መጽሐፍ ቅዱስ እንዲያስተምሩህ ወይም በአቅራቢያህ የመሰብሰቢያ አዳራሻቸው የት እንደሚገኝ ማወቅ ከፈለግህ ይህን መጽሔት ያመጣልህን የይሖዋ ምሥክር አነጋግር፤ አሊያም www.jw.org/am የተሰኘውን ድረ ገጻችንን ተመልከት፤ በድረ ገጹ መጨረሻ ላይ የሚገኘውን ከእኛ ጋር ለመገናኘት የሚለውን ተመልከት።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ