መከራ የማይኖርበት ጊዜ ይመጣል?
መልስህ ምንድን ነው?
ይመጣል?
አይመጣም?
ወይስ ምናልባት?
መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?
“እሱም እንባን ሁሉ ከዓይናቸው ያብሳል፤ ከእንግዲህ ወዲህ ሞት አይኖርም፤ ሐዘንም ሆነ ጩኸት እንዲሁም ሥቃይ ከእንግዲህ ወዲህ አይኖርም።” —ራእይ 21:3, 4 አዲስ ዓለም ትርጉም
ይህን ማወቅህ ለአንተ ምን ጥቅም አለው?
በሰው ልጆች ላይ ለሚደርሱት ችግሮች መንስኤው አምላክ እንዳልሆነ ማረጋገጫ ይሰጥሃል።—ያዕቆብ 1:13
መከራ ሲደርስብህ አምላክ እንደሚያዝንልህ ስለምታውቅ ትጽናናለህ።—ዘካርያስ 2:8
ሁሉም ዓይነት መከራ እንደሚወገድ ተስፋ እንድታደርግ ይረዳሃል።—መዝሙር 37:9-11
መጽሐፍ ቅዱስ በሚናገረው ነገር ላይ እምነት መጣል እንችላለን?
አዎ፣ ቢያንስ ሁለት ምክንያቶችን መጥቀስ ይቻላል፦
አምላክ መከራንና ኢፍትሐዊነትን ይጠላል። በመጽሐፍ ቅዱስ ዘመን፣ ይሖዋ አምላክ በሕዝቦቹ ላይ ግፍ ሲፈጸም ምን እንደተሰማው እስቲ እንመልከት። ሕዝቡ “በሚጨቁኗቸውና በሚያንገላቷቸው ሰዎች የተነሳ ሲቃትቱ” አምላክ እንዳዘነ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል።—መሳፍንት 2:18
አምላክ በሌሎች ላይ ጉዳት የሚያደርሱ ሰዎችን ይጠላል። ለምሳሌ ያህል፣ “ንጹሕ ደም የሚያፈሱ እጆች” በአምላክ ዘንድ የተጠሉ እንደሆኑ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል።—ምሳሌ 6:16, 17
አምላክ በግለሰብ ደረጃ ያስብልናል። አንድ ሰው መከራ አጋጥሞት ‘ጭንቀትና ሥቃይ’ ሲሰማው ይሖዋም የዚህ ሰው ‘ጭንቀትና ሥቃይ’ ይሰማዋል።—2 ዜና መዋዕል 6:29, 30
ይሖዋ በመንግሥቱ አማካኝነት የእያንዳንዱን ሰው መከራ በቅርቡ ያስወግዳል። (ማቴዎስ 6:9, 10) እስከዚያው ግን እሱን ከልብ የሚፈልጉ ሰዎችን በደግነት ያጽናናቸዋል።—የሐዋርያት ሥራ 17:27፤ 2 ቆሮንቶስ 1:3, 4