መዝሙር 139
ጸንተው እንዲቆሙ አስተምሯቸው
በወረቀት የሚታተመው
ደስ ይላል፣ ማስተማር ቅኖችን
ማየት እድገታቸውን፤
እውነትም ሲሆን የራሳቸው፣
ይሖዋ ሲመራቸው።
(አዝማች)
ይሖዋ ሆይ፣ ስማን ’ባክህ፤
አይለያቸው ጥበቃህ።
በ’የሱስ ስም ተለመነን፤ ምኞታችን
በርትተው ማየት ነው፣ ጸንተው።
ስንጸልይ ነበር በየ’ለቱ፤
ፈተናን እንዲወጡ።
አስተማርን፣ ረዳን ጊዜ ሰጥተን፤
እነሱም በረቱልን።
(አዝማች)
ይሖዋ ሆይ፣ ስማን ’ባክህ፤
አይለያቸው ጥበቃህ።
በ’የሱስ ስም ተለመነን፤ ምኞታችን
በርትተው ማየት ነው፣ ጸንተው።
ይመኩ ባምላክና ልጁ፤
ይሁኑ ልበ ሙሉ።
ታዛዦች ከሆኑ፣ ከጸኑ፤
ለሕይወት ይበቃሉ።
(አዝማች)
ይሖዋ ሆይ፣ ስማን ’ባክህ፤
አይለያቸው ጥበቃህ።
በ’የሱስ ስም ተለመነን፤ ምኞታችን
በርትተው ማየት ነው፣ ጸንተው።