መዝሙር 144
ስብከታችን ሰው ያድናል
በወረቀት የሚታተመው
ባምላክ የበጎ ፈቃድ ዓመት
ነው ’ምንኖረው፤
ሰዎች ይወቁ፣ ያምላክ ቁጣ
ቀን ቅርብ ነው።
(አዝማች)
ስብከታችን ሰው ያድናል፤
ለኛም መዳን ያስገኛል።
ከታዘዙ ይድናሉ፤
ስለዚህ ’ንስበክ ለሁሉ፤
ለሁሉ።
በመላው ዓለም የምንሰብከው
መል’ክት አለን፤
ሰዎችን ካምላክ ጋር
ታረቁ እንላለን።
(አዝማች)
ስብከታችን ሰው ያድናል፤
ለኛም መዳን ያስገኛል።
ከታዘዙ ይድናሉ፤
ስለዚህ ’ንስበክ ለሁሉ፤
ለሁሉ።
(መሸጋገሪያ)
አፋጣኝ፣ አስቸኳይ ነው፤
ሰምተው፣ ታዘው፣ መትረፋቸው።
በነፃ ’ናስተምራቸው፤
የሕይወት ውኃ ’ንስጣቸው።
(አዝማች)
ስብከታችን ሰው ያድናል፤
ለኛም መዳን ያስገኛል።
ከታዘዙ ይድናሉ፤
ስለዚህ ’ንስበክ ለሁሉ፤
ለሁሉ።
(በተጨማሪም 2 ዜና 36:15ን፣ ኢሳ. 61:2ን፣ ሕዝ. 33:6ን እና 2 ተሰ. 1:8ን ተመልከት።)