የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • jy ምዕ. 34 ገጽ 82-ገጽ 83 አን. 6
  • ኢየሱስ አሥራ ሁለት ሐዋርያት መረጠ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ኢየሱስ አሥራ ሁለት ሐዋርያት መረጠ
  • ኢየሱስ—መንገድ፣ እውነት፣ ሕይወት
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ሐዋርያቱን መምረጥ
    እስከ ዛሬ ከኖሩት ሁሉ የሚበልጠው ታላቅ ሰው
  • የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት
    ከታላቁ አስተማሪ ተማር
  • ኢየሱስ በአንድ ተራራ ላይ ሲያስተምር
    የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች መማሪያ መጽሐፌ
  • ኢየሱስ አሥራ ሁለት ሐዋርያትን መረጠ
    ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ምን ትማራለህ?
ለተጨማሪ መረጃ
ኢየሱስ—መንገድ፣ እውነት፣ ሕይወት
jy ምዕ. 34 ገጽ 82-ገጽ 83 አን. 6
ኢየሱስ ወደ ተራራ ሲወጣ

ምዕራፍ 34

ኢየሱስ አሥራ ሁለት ሐዋርያት መረጠ

ማርቆስ 3:13-19 ሉቃስ 6:12-16

  • የኢየሱስ 12 ሐዋርያት

መጥምቁ ዮሐንስ፣ ኢየሱስ የአምላክ በግ መሆኑን ከተናገረ አንድ ዓመት ተኩል ገደማ ሆኗል። ኢየሱስ አገልግሎቱን ሲጀምር ቅን ልብ ያላቸው በርካታ ሰዎች ደቀ መዛሙርቱ ሆኑ፤ ከእነዚህም መካከል እንድርያስ፣ ስምዖን ጴጥሮስ፣ ዮሐንስ ምናልባትም ያዕቆብ (የዮሐንስ ወንድም)፣ ፊልጶስና በርቶሎሜዎስ (ናትናኤል ተብሎም ይጠራል) ይገኙበታል። ከጊዜ በኋላ ሌሎች ብዙዎችም የክርስቶስ ተከታዮች ሆኑ።—ዮሐንስ 1:45-47

አሁን ኢየሱስ ሐዋርያቱን ለመምረጥ ተዘጋጅቷል። እነዚህ ሰዎች የቅርብ ወዳጆቹ ይሆናሉ፤ እንዲሁም ኢየሱስ ልዩ ሥልጠና ይሰጣቸዋል። ሆኖም ኢየሱስ እነሱን ከመምረጡ በፊት ወደ አንድ ተራራ ወጣ፤ የሄደው ከቅፍርናሆም ሳይርቅ በገሊላ ባሕር አቅራቢያ ወደሚገኝ ቦታ ሊሆን ይችላል። ጥበብና የአምላክን በረከት ለማግኘት ሳይሆን አይቀርም ሌሊቱን ሙሉ ሲጸልይ አደረ። በማግስቱ ደቀ መዛሙርቱን ጠራና ሐዋርያቱ እንዲሆኑ ከመካከላቸው 12ቱን መረጠ።

ኢየሱስ በመግቢያው ላይ የተጠቀሱትን ስድስት ደቀ መዛሙርት እና ከቀረጥ መሰብሰቢያ ቦታ የጠራውን ማቴዎስን መረጠ። ሌሎቹ አምስቱ ደግሞ ይሁዳ (ታዴዎስ እና “የያዕቆብ ልጅ” ተብሎም ይጠራል)፣ ቀነናዊው ስምዖን፣ ቶማስ፣ የእልፍዮስ ልጅ ያዕቆብና የአስቆሮቱ ይሁዳ ናቸው።—ማቴዎስ 10:2-4፤ ሉቃስ 6:16

ኢየሱስ አሥራ ሁለት ሐዋርያቱን ከመምረጡ በፊት ሲጸልይ

ኢየሱስ ከእነዚህ 12 ሰዎች ጋር ሲጓዝ ስለቆየ በደንብ ያውቃቸዋል። እንዲያውም አንዳንዶቹ ዘመዶቹ ናቸው። ወንድማማቾቹ ያዕቆብና ዮሐንስ የኢየሱስ አክስት ልጆች እንደሆኑ ከሁኔታው መረዳት ይቻላል። አንዳንዶች እንደሚገምቱት እልፍዮስ የኢየሱስ አሳዳጊ አባት የሆነው የዮሴፍ ወንድም ነው፤ ይህ ከሆነ ደግሞ የእልፍዮስ ልጅ የሆነው ሐዋርያው ያዕቆብ ለኢየሱስ የአጎቱ ልጅ ይሆናል ማለት ነው።

ኢየሱስ የሐዋርያቱን ስም ለማስታወስ እንደማይቸገር ጥያቄ የለውም። አንተስ ስማቸውን ማስታወስ ትችላለህ? ስሞቹን እንዳንረሳ ከሚረዱን መንገዶች አንዱ የሚከተለው ነው፦ ሁለት ስምዖኖች፣ ሁለት ያዕቆቦች፣ ሁለት ይሁዳዎች እንዳሉ አስታውስ። ስምዖን (ጴጥሮስ) እንድርያስ የሚባል ወንድም አለው፤ ያዕቆብ (የዘብዴዎስ ልጅ) ደግሞ ዮሐንስ የሚባል ወንድም አለው። ይህ የስምንቱን ሐዋርያት ስም ለማስታወስ የሚያስችል ዘዴ ነው። የተቀሩት አራቱ ደግሞ ቀረጥ ሰብሳቢ የነበረው ማቴዎስ፣ በኋላ ላይ የተጠራጠረው ቶማስ፣ ዛፍ ሥር ሳለ የተጠራው ናትናኤል እና ጓደኛው ፊልጶስ ናቸው።

አሥራ አንዱ ሐዋርያት የመጡት ኢየሱስ ካደገባት ከገሊላ ነው። ናትናኤል የቃና ሰው ነው። ፊልጶስ፣ ጴጥሮስና እንድርያስ ደግሞ የቤተሳይዳ ሰዎች ናቸው። ከጊዜ በኋላ ጴጥሮስና እንድርያስ በቅፍርናሆም መኖር ጀመሩ፤ ማቴዎስም የሚኖረው እዚያው ሳይሆን አይቀርም። ያዕቆብና ዮሐንስም የሚኖሩት ቅፍርናሆም ውስጥ ወይም በአቅራቢያዋ ሲሆን በዚያው አካባቢ ዓሣ በማጥመድ ሥራ ላይ ተሰማርተው ነበር። ከይሁዳ የመጣው ሐዋርያ፣ ከጊዜ በኋላ ኢየሱስን አሳልፎ የሰጠው የአስቆሮቱ ይሁዳ ብቻ ይመስላል።

  • ኢየሱስ ሌሊቱን ሙሉ ሲጸልይ ካደረ በኋላ ምን ከባድ ውሳኔ አደረገ?

  • የኢየሱስ ሐዋርያት እነማን ናቸው? ስማቸውንስ እንዴት ማስታወስ ትችላለህ?

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ