የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • lfb ትምህርት 80 ገጽ 188-ገጽ 189 አን. 1
  • ኢየሱስ አሥራ ሁለት ሐዋርያትን መረጠ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ኢየሱስ አሥራ ሁለት ሐዋርያትን መረጠ
  • ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ምን ትማራለህ?
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ኢየሱስ አሥራ ሁለት ሐዋርያት መረጠ
    ኢየሱስ—መንገድ፣ እውነት፣ ሕይወት
  • ሐዋርያቱን መምረጥ
    እስከ ዛሬ ከኖሩት ሁሉ የሚበልጠው ታላቅ ሰው
  • ኢየሱስ በአንድ ተራራ ላይ ሲያስተምር
    የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች መማሪያ መጽሐፌ
  • የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት
    ከታላቁ አስተማሪ ተማር
ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ምን ትማራለህ?
lfb ትምህርት 80 ገጽ 188-ገጽ 189 አን. 1
ኢየሱስና 12 ሐዋርያቱ

ትምህርት 80

ኢየሱስ አሥራ ሁለት ሐዋርያትን መረጠ

ኢየሱስ ለአንድ ዓመት ተኩል ያህል ከሰበከ በኋላ ትልቅ ውሳኔ ማድረግ የሚጠይቅ ሁኔታ አጋጠመው። የቅርብ ረዳቶቹ ሆነው ከእሱ ጋር እንዲሠሩ የሚመርጠው እነማንን ይሆን? በክርስቲያን ጉባኤ ውስጥ አመራር እንዲሰጡ የሚያሠለጥነውስ እነማንን ነው? ኢየሱስ እነዚህን ውሳኔዎች ለማድረግ የይሖዋ እርዳታ እንደሚያስፈልገው ተሰማው። ስለዚህ ብቻውን ወደ አንድ ተራራ ሄደና ሌሊቱን ሙሉ ሲጸልይ አደረ። ከዚያም ጠዋት ላይ ከደቀ መዛሙርቱ መካከል የተወሰኑትን ጠራና 12 ሐዋርያቱን መረጠ። ከሐዋርያቱ መካከል የእነማንን ስም ታስታውሳለህ? የኢየሱስ 12 ሐዋርያት ጴጥሮስ፣ እንድርያስ፣ ያዕቆብ፣ ዮሐንስ፣ ፊልጶስ፣ በርቶሎሜዎስ፣ ቶማስ፣ ማቴዎስ፣ የእልፍዮስ ልጅ ያዕቆብ፣ ታዴዎስ፣ ስምዖንና የአስቆሮቱ ይሁዳ ነበሩ።

እንድርያስ፣ ጴጥሮስ፣ ፊልጶስ፣ ያዕቆብ

እንድርያስ፣ ጴጥሮስ፣ ፊልጶስ፣ ያዕቆብ

አሥራ ሁለቱ ሐዋርያት ከኢየሱስ ጋር አብረው ይጓዙ ነበር። ኢየሱስ ካሠለጠናቸው በኋላ ደግሞ ብቻቸውን እንዲሰብኩ ላካቸው። ይሖዋም አጋንንትን ለማስወጣትና የታመሙ ሰዎችን ለመፈወስ የሚያስችል ኃይል ሰጣቸው።

ዮሐንስ፣ ማቴዎስ፣ በርቶሎሜዎስ፣ ቶማስ

ዮሐንስ፣ ማቴዎስ፣ በርቶሎሜዎስ፣ ቶማስ

ኢየሱስ አሥራ ሁለቱን ሐዋርያት ‘ወዳጆቼ’ ብሎ ይጠራቸው ነበር፤ እንዲሁም ያምናቸው ነበር። ፈሪሳውያን የኢየሱስን ሐዋርያት ያልተማሩና ተራ ሰዎች አድርገው ይመለከቷቸው ነበር። ኢየሱስ ግን ለሐዋርያቱ የሚያስፈልጋቸውን ሥልጠና ሰጥቷቸዋል። በተጨማሪም በኢየሱስ ሕይወት ውስጥ ወሳኝ በሆኑ ጊዜያት ከጎኑ አልተለዩም፤ ለምሳሌ ከመሞቱ በፊትና ከሞት ከተነሳ በኋላ አብረውት ነበሩ። ከአሥራ ሁለቱ ሐዋርያት መካከል አብዛኞቹ ልክ እንደ ኢየሱስ የገሊላ ሰዎች ነበሩ። ከዚህም ሌላ አንዳንዶቹ ሐዋርያት አግብተው ነበር።

የእልፍዮስ ልጅ ያዕቆብ፣ የአስቆሮቱ ይሁዳ፣ ታዴዎስ፣ ስምዖን

የእልፍዮስ ልጅ ያዕቆብ፣ የአስቆሮቱ ይሁዳ፣ ታዴዎስ፣ ስምዖን

ሐዋርያቱ ፍጹም ሰዎች አልነበሩም፤ በመሆኑም ስህተት የሠሩባቸው ጊዜያት አሉ። አልፎ አልፎ ሳያስቡ ይናገሩ እንዲሁም የተሳሳቱ ውሳኔዎችን ያደርጉ ነበር። አንዳንድ ጊዜ ደግሞ የችኩልነት ባሕርይ ይታይባቸው ነበር። ‘ከመካከላችን የሚበልጠው ማን ነው?’ ብለው የተከራከሩበት ጊዜም ነበር። ሆኖም ሐዋርያቱ ይሖዋን የሚወዱ ጥሩ ሰዎች ነበሩ። የክርስቲያን ጉባኤ የመጀመሪያ አባላት ከመሆናቸውም ሌላ ኢየሱስ ከሞተ በኋላ በጉባኤው ውስጥ ትልቅ ሚና ተጫውተዋል።

“ከአባቴ የሰማሁትን ነገር ሁሉ ስላሳወቅኳችሁ ወዳጆች ብዬ ጠርቻችኋለሁ።”—ዮሐንስ 15:15

ጥያቄ፦ ኢየሱስ የመረጣቸው 12 ሐዋርያት እነማን ናቸው? ኢየሱስ ሐዋርያቱን ምን እንዲያደርጉ ላካቸው?

ማቴዎስ 10:1-10፤ ማርቆስ 3:13-19፤ 10:35-40፤ ሉቃስ 6:12-16፤ ዮሐንስ 15:15፤ 20:24, 25፤ የሐዋርያት ሥራ 2:7፤ 4:13፤ 1 ቆሮንቶስ 9:5፤ ኤፌሶን 2:20-22

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ