የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • od ገጽ 4-5
  • ከበላይ አካሉ የተላከ ደብዳቤ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ከበላይ አካሉ የተላከ ደብዳቤ
  • የይሖዋን ፈቃድ ለማድረግ የተደራጀ ሕዝብ
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ወንድሞች፣ ለመንፈስ ብላችሁ በመዝራት ለኃላፊነት ለመብቃት ተጣጣሩ!
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2010
  • ከአምላክ መጽሐፍ ጋር በሚስማማ መልኩ መደራጀት
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2016
  • የይሖዋ በጎች በርኅራኄ መያዝ ያስፈልጋቸዋል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1996
  • ወጣት ወንድሞች፣ የኃላፊነት ቦታ ላይ ለመድረስ እየተጣጣራችሁ ነው?
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2013
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን ፈቃድ ለማድረግ የተደራጀ ሕዝብ
od ገጽ 4-5

ከበላይ አካሉ የተላከ ደብዳቤ

የሥራ ባልደረባችን የሆንከው ውድ የምሥራቹ አስፋፊ፦

እሱ ብቻ እውነተኛ አምላክ የሆነውን ይሖዋን በኅብረት ማምለክ መቻላችን እንዴት ያለ አስደናቂ መብት ነው! ‘ከአምላክ ጋር አብረን የመሥራት’ መብት ያለን ሲሆን በሰማይ ስለተቋቋመው መንግሥቱ የሚገልጸውን ምሥራች የመስበክና የማስተማር ሥራ በአደራ ተሰጥቶናል፤ ይህም ቅዱስና ሕይወት አድን ሥራ ነው። (1 ቆሮ. 3:9፤ ማቴ. 28:19, 20) ይህን ዓለም አቀፋዊ ይዘት ያለው ሥራ እርስ በርስ ተስማምተን በአንድነት ማከናወን እንድንችል በሚገባ የተደራጀን መሆን ይኖርብናል።—1 ቆሮ. 14:40

ይህ መጽሐፍ በዛሬው ጊዜ የክርስቲያን ጉባኤ እንዴት እንደተደራጀ እንድትገነዘብ ይረዳሃል። በተጨማሪም የይሖዋ ምሥክር እንደመሆንህ መጠን ምን መብቶች እንዳሉህና ምን ኃላፊነቶች እንደተጣሉብህ ያብራራል። መብቶችህን የምታደንቅና ኃላፊነቶችህን በአግባቡ የምትወጣ ከሆነ ‘በእምነት ጠንካራ’ ትሆናለህ።—ሥራ 16:4, 5፤ ገላ. 6:5

በመሆኑም ይህን መጽሐፍ በደንብ እንድታጠና እናበረታታሃለን። እንዲሁም በውስጡ የያዘውን ትምህርት በሕይወትህ ተግባራዊ ማድረግ የምትችልባቸውን መንገዶች ለማስተዋል ጥረት አድርግ። ለምሳሌ ያህል፣ ያልተጠመቀ አስፋፊ የሆንከው በቅርቡ ከሆነ ተጠምቀህ የይሖዋ ምሥክር ለመሆን ምን እርምጃዎች መውሰድ ይኖርብሃል? በሌላ በኩል ደግሞ ተጠምቀህ ይሖዋን በማገልገል ላይ የምትገኝ ክርስቲያን ከሆንክ በመንፈሳዊ ለማደግና ለይሖዋ የምታቀርበውን አገልግሎት ለማስፋት ምን ማድረግ ትችላለህ? (1 ጢሞ. 4:15) ለጉባኤው ሰላም የበኩልህን አስተዋጽኦ ማበርከት የምትችለው እንዴት ነው? (2 ቆሮ. 13:11) ይህ መጽሐፍ ለእነዚህ ጥያቄዎች መልስ ይሰጣል።

የተጠመቅክ ወንድም ከሆንክ ብቃቱን አሟልተህ የጉባኤ አገልጋይ ለመሆን ከዚያም የጉባኤ ሽማግሌ ሆነህ ለማገልገል ምን ማድረግ ትችላለህ? በሺዎች የሚቆጠሩ አዳዲስ ክርስቲያኖች ወደ አምላክ ድርጅት እየጎረፉ ስለሆነ አመራር የሚሰጡ ብቃት ያላቸው ወንድሞች ማግኘት ጊዜ የማይሰጥ ጉዳይ ሆኗል። ይህ መጽሐፍ እነዚህ መንፈሳዊ ግቦች ላይ ለመድረስ ‘መጣጣር’ የምትችለው እንዴት እንደሆነ እንድትገነዘብ ይረዳሃል።—1 ጢሞ. 3:1

ይህ መጽሐፍ በይሖዋ ዝግጅት ውስጥ የበኩልህን ድርሻ ማበርከት የምትችለው እንዴት እንደሆነ እንድትገነዘብና ይህን መብትህን በአድናቆት እንድትመለከት ይረዳህ ዘንድ ከልብ እንጸልያለን። ሁላችሁንም ከልብ እንወዳችኋለን፤ እንዲሁም በሰማይ የሚኖረውን አባታችንን ይሖዋን ለዘላለም በደስታ ከሚያመልኩት ሰዎች መካከል እንድትሆኑ ምንጊዜም ጸሎታችን ነው።—መዝ. 37:10, 11፤ ኢሳ. 65:21-25

ወንድሞችህ፣

የይሖዋ ምሥክሮች የበላይ አካል

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ