የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • lfb ትምህርት 50 ገጽ 120-ገጽ 121 አን. 5
  • ይሖዋ ኢዮሳፍጥን ከጠላቶቹ አዳነው

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ይሖዋ ኢዮሳፍጥን ከጠላቶቹ አዳነው
  • ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ምን ትማራለህ?
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ኢዮሣፍጥ በይሖዋ ተማመነ
    የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች መማሪያ መጽሐፌ
  • ለይሖዋ ቤት የምትቀኑ ሁኑ!
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2009
  • በፍርድ ሸለቆ የተወሰደ የቅጣት እርምጃ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1998
  • 2 ዜና መዋዕል የመጽሐፉ ይዘት
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ለተጨማሪ መረጃ
ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ምን ትማራለህ?
lfb ትምህርት 50 ገጽ 120-ገጽ 121 አን. 5
ንጉሥ ኢዮሳፍጥና ሌዋውያኑ ዘማሪዎች ሠራዊቱን እየመሩ ከኢየሩሳሌም ሲወጡ

ትምህርት 50

ይሖዋ ኢዮሳፍጥን ከጠላቶቹ አዳነው

የይሁዳ ንጉሥ የሆነው ኢዮሳፍጥ የባአልን መሠዊያዎችና ጣዖታት በሙሉ አስወገደ። ሕዝቡ የይሖዋን ሕግ እንዲያውቁ ይፈልግ ነበር። ስለዚህ የይሖዋን ሕግ በመላው ይሁዳ ለሕዝቡ እንዲያስተምሩ መኳንንቱንና ሌዋውያኑን ላከ።

በአቅራቢያው የነበሩ አገሮች ይሖዋ ሕዝቡን እንደሚረዳ ስላወቁ በይሁዳ ላይ ጥቃት መሰንዘር ይፈሩ ነበር። እንዲያውም ለንጉሥ ኢዮሳፍጥ ስጦታ ያመጡለት ነበር። በኋላ ግን ሞዓባውያን፣ አሞናውያንና በሴይር አካባቢ የሚኖሩ ሰዎች ከይሁዳ ጋር ለመዋጋት መጡ። ኢዮሳፍጥ የይሖዋ እርዳታ እንደሚያስፈልገው ያውቅ ነበር። ስለዚህ ሁሉንም ወንዶች፣ ሴቶችና ልጆች በኢየሩሳሌም ሰበሰበ። ከዚያም በእነሱ ፊት እንዲህ በማለት ጸለየ፦ ‘ይሖዋ፣ ያለአንተ እርዳታ ማሸነፍ አንችልም። እባክህ ምን ማድረግ እንዳለብን ንገረን።’

ይሖዋ እንዲህ በማለት ጸሎቱን መለሰለት፦ ‘አትፍሩ። እኔ እረዳችኋለሁ። ቦታ ቦታችሁን ያዙ፤ ዝም ብላችሁ ቁሙ፤ እንዴት እንደማድናችሁ ታያላችሁ።’ ታዲያ ይሖዋ ያዳናቸው እንዴት ነው?

በቀጣዩ ቀን ጠዋት፣ ኢዮሳፍጥ ዘማሪዎችን መረጠና ከሠራዊቱ ፊት ፊት እንዲሄዱ ነገራቸው። እነሱም ከኢየሩሳሌም ተነስተው ተቆአ በሚባል ቦታ እስከሚገኘው የጦር ሜዳ ድረስ ሄዱ።

ዘማሪዎቹ ከፍ ባለ ድምፅ ይሖዋን እያወደሱ ሳሉ ይሖዋ ለሕዝቡ ተዋጋላቸው። አሞናውያኑና ሞዓባውያኑ ግራ ተጋብተው እርስ በርስ እንዲዋጉ አደረገ፤ ከመካከላቸው አንድም ሰው አልተረፈም። የይሁዳን ሕዝብ፣ ወታደሮቹንና ካህናቱን ግን ከጠላቶቻቸው አዳናቸው። በይሁዳ ዙሪያ በሚገኙት አገሮች ያሉ ሰዎች በሙሉ ይሖዋ ያደረገውን ነገር ሲሰሙ አሁንም ሕዝቡን እንደሚጠብቅ ተገነዘቡ። አዎ፣ ይሖዋ ሕዝቡን በተለያዩ መንገዶች ያድናል። ደግሞም ሕዝቡን ለማዳን የሰዎች እርዳታ አያስፈልገውም።

“እናንተ ይህን ጦርነት መዋጋት አያስፈልጋችሁም። ቦታ ቦታችሁን ይዛችሁ ዝም ብላችሁ ቁሙ፤ ይሖዋ ለእናንተ ሲል የሚወስደውን የማዳን እርምጃ ተመልከቱ።”—2 ዜና መዋዕል 20:17

ጥያቄ፦ ኢዮሳፍጥ ምን ዓይነት ንጉሥ ነበር? ይሖዋ ይሁዳን የጠበቀው እንዴት ነው?

2 ዜና መዋዕል 17:1-19፤ 20:1-30

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ