የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • lfb ትምህርት 75 ገጽ 178-ገጽ 179 አን. 4
  • ዲያብሎስ ኢየሱስን ፈተነው

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ዲያብሎስ ኢየሱስን ፈተነው
  • ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ምን ትማራለህ?
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የሚያጋጥሙንን ፈተናዎች መቋቋም ያስፈልገናል
    ከታላቁ አስተማሪ ተማር
  • ኢየሱስ እንዳደረገው “ዲያብሎስን ተቃወሙት”
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2008
  • ኢየሱስ ፈተናዎችን ከተቋቋመበት መንገድ መማር
    ኢየሱስ—መንገድ፣ እውነት፣ ሕይወት
  • ኢየሱስ ከቀረቡለት ፈተናዎች መማር
    እስከ ዛሬ ከኖሩት ሁሉ የሚበልጠው ታላቅ ሰው
ለተጨማሪ መረጃ
ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ምን ትማራለህ?
lfb ትምህርት 75 ገጽ 178-ገጽ 179 አን. 4
ኢየሱስ ከቤተ መቅደሱ አናት ለመዝለል ፈቃደኛ አልሆነም

ትምህርት 75

ዲያብሎስ ኢየሱስን ፈተነው

ኢየሱስን ድንጋዮቹን ወደ ዳቦ ለመቀየር ፈቃደኛ አልሆነም

ኢየሱስ ከተጠመቀ በኋላ መንፈስ ቅዱስ ወደ ምድረ በዳ ወሰደው። ለ40 ቀን ያህል ምንም አልበላም፤ ስለዚህ በጣም ራበው። ከዚያም ዲያብሎስ ሊፈትነው መጣና እንዲህ አለው፦ ‘እስቲ የአምላክ ልጅ ከሆንክ እነዚህን ድንጋዮች ዳቦ እንዲሆኑ እዘዛቸው።’ ኢየሱስ ግን ከቅዱሳን መጻሕፍት በመጥቀስ እንዲህ አለው፦ ‘“ሰው በምግብ ብቻ አይኖርም” ተብሎ ተጽፏል። ይሖዋ የሚናገረውን ቃል መስማትም አስፈላጊ ነው።’

ቀጥሎ ደግሞ ዲያብሎስ እንዲህ በማለት ኢየሱስን ፈተነው፦ ‘እስቲ የአምላክ ልጅ ከሆንክ ከቤተ መቅደሱ አናት ዝለል። “አምላክ መላእክቱን ልኮ ጉዳት እንዳይደርስብህ ይጠብቅሃል” ተብሎ ተጽፏል።’ ኢየሱስ ግን በድጋሚ ቅዱሳን መጻሕፍትን በመጥቀስ ‘“ይሖዋን አትፈታተነው” ተብሎ ተጽፏል’ አለው።

ሰይጣን የዓለምን መንግሥታት በሙሉ እንደሚሰጠው ቃል ቢገባለትም ኢየሱስ ግብዣውን አልተቀበለም

ከዚያም ሰይጣን የዓለምን መንግሥታት በሙሉ እንዲሁም ሀብታቸውንና ክብራቸውን ለኢየሱስ አሳየውና ‘አንድ ጊዜ ብቻ ብታመልከኝ እነዚህን ሁሉ መንግሥታትና ክብራቸውን በሙሉ እሰጥሃለሁ’ አለው። ኢየሱስ ግን ‘ሂድ፣ አንተ ሰይጣን! “ይሖዋን ብቻ አምልክ” ተብሎ ተጽፏል’ አለው።

ከዚያም ዲያብሎስ ሄደ፤ መላእክትም መጥተው ለኢየሱስ የሚበላው ምግብ ሰጡት። ከዚያ ጊዜ አንስቶ ኢየሱስ የአምላክን መንግሥት ምሥራች መስበክ ጀመረ። ወደ ምድር የተላከው ይህን ሥራ እንዲሠራ ነው። ሕዝቡ ኢየሱስ የሚያስተምራቸውን ትምህርት ይወዱት ነበር፤ እንዲሁም በሚሄድበት ቦታ ሁሉ ይከተሉት ነበር።

“[ዲያብሎስ] ውሸታምና የውሸት አባት ስለሆነ ውሸት ሲናገር ከራሱ አመንጭቶ ይናገራል።”—ዮሐንስ 8:44

ጥያቄ፦ ሰይጣን ለኢየሱስ ያቀረባቸው ሦስት ፈተናዎች የትኞቹ ናቸው? ኢየሱስ ለዲያብሎስ ምን መልስ ሰጠ?

ማቴዎስ 4:1-11፤ ማርቆስ 1:12, 13፤ ሉቃስ 4:1-15፤ ዘዳግም 6:13, 16፤ 8:3፤ ያዕቆብ 4:7

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ