የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • lfb ትምህርት 82 ገጽ 192-ገጽ 193 አን. 3
  • ኢየሱስ ስለ ጸሎት አስተማረ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ኢየሱስ ስለ ጸሎት አስተማረ
  • ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ምን ትማራለህ?
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • አምላክ ስለሚሰማቸው ጸሎቶች
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2009
  • ወደ አምላክ የመጸለይ ውድ መብት
    መጽሐፍ ቅዱስ ምን ያስተምረናል?
  • መጸለይ ያለብን ወደ ኢየሱስ ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2015
  • በጸሎት አማካኝነት ወደ አምላክ ቅረብ
    ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
ለተጨማሪ መረጃ
ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ምን ትማራለህ?
lfb ትምህርት 82 ገጽ 192-ገጽ 193 አን. 3
አንድ ፈሪሳዊ ሰዎች ቆመው እያዩት በመንገድ ላይ ሲጸልይ

ትምህርት 82

ኢየሱስ ስለ ጸሎት አስተማረ

ፈሪሳውያን ማንኛውንም ነገር የሚያደርጉት የሰዎችን ትኩረት ለመሳብ ነበር። ለሰዎች ጥሩ ነገር የሚያደርጉት ሌሎች እንዲያዩዋቸው ብለው ነው። ሰው እንዲያያቸው ሲሉ ሕዝብ በብዛት በሚገኝባቸው ቦታዎች ይጸልዩ ነበር። ፈሪሳውያን ረጅም ጸሎቶችን ሸምድደው በምኩራብና በመንገድ ላይ ሰዎች እየሰሟቸው ይጸልዩ ነበር። ስለዚህ ኢየሱስ እንዲህ ብሎ ሲናገር የሚሰሙት ሰዎች ተገርመው ነበር፦ ‘እንደ ፈሪሳውያን አትጸልዩ። እነሱ ረጅም ጸሎት ስላቀረቡ ብቻ አምላክ የሚደሰት ይመስላቸዋል፤ አምላክ ግን በዚህ አይደሰትም። የምትጸልዩት ሌሎች እንዲያዩዋችሁ ብላችሁ ሳይሆን አባታችሁን ይሖዋን በግል ለማነጋገር መሆን አለበት። ጸሎታችሁ እንዲሁ ድግግሞሽ መሆን የለበትም። ይሖዋ በውስጣችሁ የሚሰማችሁን ነገር በግልጽ እንድትነግሩት ይፈልጋል።

A boy kneels and prays

‘እንዲህ ብላችሁ ጸልዩ፦ “በሰማያት የምትኖር አባታችን ሆይ፣ ስምህ ይቀደስ። መንግሥትህ ይምጣ። ፈቃድህ በሰማይ እየተፈጸመ እንዳለ ሁሉ በምድርም ላይ ይፈጸም።”’ በተጨማሪም ኢየሱስ፣ ይሖዋ የዕለት ምግባቸውን እንዲሰጣቸው፣ ኃጢአታቸውን ይቅር እንዲላቸው እንዲሁም ስለ ሌሎች የግል ጉዳዮቻቸው እንዲጸልዩ ነግሯቸዋል።

ኢየሱስ እንዲህ ብሏል፦ ‘መጸለያችሁን አታቋርጡ። አባታችሁን ይሖዋን ጥሩ ነገር እንዲያደርግላችሁ ጠይቁት። ሁሉም ወላጅ ለልጁ ጥሩ ነገር መስጠት ይፈልጋል። ልጃችሁ ዳቦ እንድትሰጡት ቢጠይቃችሁ ድንጋይ ትሰጡታላችሁ? ወይስ ዓሣ እንድትሰጡት ቢጠይቃችሁ እባብ ትሰጡታላችሁ?’

ከዚያም ኢየሱስ የምሳሌውን ትርጉም አብራራ፦ ‘እናንተ ለልጆቻችሁ ጥሩ ስጦታ መስጠት የምትችሉ ከሆነ አባታችሁ ይሖዋ እንዴት መንፈስ ቅዱስን አይሰጣችሁም? ከእናንተ የሚጠበቀው መጠየቅ ብቻ ነው።’ አንተስ የኢየሱስን ምክር ትከተላለህ? ስለ ምን ጉዳይ ትጸልያለህ?

“ደጋግማችሁ ለምኑ፣ ይሰጣችኋል፤ ሳታቋርጡ ፈልጉ፣ ታገኛላችሁ፤ ደጋግማችሁ አንኳኩ፣ ይከፈትላችኋል።”—ማቴዎስ 7:7

ጥያቄ፦ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ምን ብለው እንዲጸልዩ አስተምሯቸዋል? በጸሎትህ ውስጥ የምትጠቅሳቸው በጣም የሚያሳስቡህ ነገሮች ምንድን ናቸው?

ማቴዎስ 6:2-18፤ 7:7-11፤ ሉቃስ 11:13

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ