የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • lfb ትምህርት 86 ገጽ 200-ገጽ 201 አን. 1
  • ኢየሱስ አልዓዛርን ከሞት አስነሳው

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ኢየሱስ አልዓዛርን ከሞት አስነሳው
  • ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ምን ትማራለህ?
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ኢየሱስ ቶሎ ያልሄደው ለምን ነበር?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2010
  • ስንሞት ምን እንሆናለን?
    ከታላቁ አስተማሪ ተማር
  • “አምናለሁ”
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2011
  • “ትንሣኤና ሕይወት”
    ኢየሱስ—መንገድ፣ እውነት፣ ሕይወት
ለተጨማሪ መረጃ
ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ምን ትማራለህ?
lfb ትምህርት 86 ገጽ 200-ገጽ 201 አን. 1
ከሞት የተነሳው አልዓዛር ከእህቶቹ ከማርያምና ከማርታ ጋር

ትምህርት 86

ኢየሱስ አልዓዛርን ከሞት አስነሳው

ኢየሱስ በቢታንያ የሚኖሩ ሦስት የቅርብ ጓደኞች ነበሩት። እነሱም አልዓዛር፣ ማርያምና ማርታ ነበሩ። አንድ ቀን አልዓዛር በጣም ታመመ፤ በወቅቱ ኢየሱስ በፔሪያ አውራጃ ስለነበረ የአልዓዛር እህቶች የሆኑት ማርያምና ማርታ ‘የምትወደው ሰው በጣም ታሟል። እባክህ ቶሎ ና!’ የሚል መልእክት ላኩበት። ኢየሱስ ግን ወዲያውኑ አልሄደም። ከዚህ ይልቅ ለሁለት ቀን እዚያው ቆየ፤ በዚህ መሃል አልዓዛር ሞተ። ከዚያም ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ አላቸው፦ ‘ወደ ቢታንያ እንሂድ። አልዓዛር ተኝቷል፤ እኔም ከእንቅልፉ ልቀሰቅሰው እሄዳለሁ።’ ሐዋርያቱም ‘አልዓዛር ተኝቶ ከሆነ ሕመሙ ቶሎ ይሻለዋል’ አሉ። ስለዚህ ኢየሱስ በግልጽ ‘አልዓዛር ሞቷል’ አላቸው።

ኢየሱስ ቢታንያ በደረሰበት ወቅት አልዓዛር ከተቀበረ አራት ቀን ሆኖት ነበር። ማርታንና ማርያምን ለማጽናናት ብዙ ሰዎች መጥተው ነበር። ማርታ፣ ኢየሱስ መምጣቱን ስትሰማ እሱን ለማግኘት ፈጥና ወጣች። ከዚያም ኢየሱስን “ጌታ ሆይ፣ አንተ እዚህ ብትሆን ኖሮ ወንድሜ ባልሞተ ነበር” አለችው። ኢየሱስም ‘ወንድምሽ ይነሳል። ይህን ታምኛለሽ?’ አላት። እሷም ‘በትንሣኤ ወቅት እንደሚነሳ አምናለሁ’ አለችው። ከዚያም ኢየሱስ “ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ” አላት።

ማርታም ወደ ማርያም ሄዳ ‘ኢየሱስ መጥቷል’ አለቻት። ማርያም በፍጥነት ወደ ኢየሱስ ሄደች፤ ሊያጽናኗቸው የመጡት ሰዎችም ተከተሏት። ከዚያም ማርያም በኢየሱስ እግር ላይ ወድቃ ስቅስቅ ብላ አለቀሰች። ኢየሱስን ‘ጌታ ሆይ፣ አንተ እዚህ ሆነህ ቢሆን ኖሮ ወንድማችን አይሞትም ነበር!’ አለችው። ኢየሱስ፣ ማርያም ምን ያህል እንዳዘነች ሲያይ እሱም ማልቀስ ጀመረ። ሰዎቹም ኢየሱስ ሲያለቅስ ሲያዩ ‘አልዓዛርን ምን ያህል ይወደው እንደነበር እዩ’ አሉ። አንዳንድ ሰዎች ግን ‘ይህን ያህል ይወደው ከነበረ ያላዳነው ለምንድን ነው?’ ብለው አሰቡ። ታዲያ ኢየሱስ ምን ያደርግ ይሆን?

ኢየሱስ ወደ መቃብሩ ሄደ፤ መቃብሩ በትልቅ ድንጋይ ተዘግቶ ነበር። በመሆኑም ‘ድንጋዩን አንሱት’ አለ። ማርታ ግን ‘አራት ቀን ስለሆነው አሁን ይሸታል’ አለችው። ይሁንና ኢየሱስ እንዳለው ሰዎቹ ድንጋዩን አነሱት፤ ከዚያም ኢየሱስ እንዲህ በማለት ጸለየ፦ ‘አባት ሆይ፣ ስለሰማኸኝ አመሰግንሃለሁ። ሁልጊዜም እንደምትሰማኝ አውቃለሁ፤ ይህን ያልኩት ግን እነዚህ ሰዎች አንተ እንደላክኸኝ እንዲያምኑ ነው።’ ከዚያም ጮክ ብሎ “አልዓዛር፣ ና ውጣ!” አለ። በዚህ ጊዜ አንድ አስደናቂ ነገር ተፈጸመ፤ አልዓዛር በጨርቅ እንደተጠቀለለ ከመቃብር ወጣ። ኢየሱስም “ፍቱትና ይሂድ” አላቸው።

ይህ ተአምር ሲፈጸም ያዩ ብዙ ሰዎች በኢየሱስ አመኑ። አንዳንድ ሰዎች ግን ሄደው ኢየሱስ ያደረገውን ነገር ለፈሪሳውያን ነገሯቸው። ከዚያ ጊዜ አንስቶ ፈሪሳውያን አልዓዛርንና ኢየሱስን መግደል የሚችሉበትን መንገድ ይፈልጉ ጀመር። ከአሥራ ሁለቱ ሐዋርያት አንዱ የሆነው የአስቆሮቱ ይሁዳ በድብቅ ወደ ፈሪሳውያን ሄዶ ‘ኢየሱስን እንድትይዙ ብረዳችሁ ምን ያህል ገንዘብ ትሰጡኛላችሁ?’ አላቸው። እነሱም 30 የብር ሳንቲሞች ሊከፍሉት ተስማሙ፤ ከዚያም ይሁዳ ኢየሱስን ለፈሪሳውያን አሳልፎ የሚሰጥበትን አጋጣሚ መፈለግ ጀመረ።

“እውነተኛው አምላክ፣ አዳኝ አምላካችን ነው፤ ደግሞም ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ከሞት ይታደጋል።”—መዝሙር 68:20

ጥያቄ፦ ስለ አልዓዛር ትንሣኤ የሚገልጸውን ታሪክ ተናገር። ፈሪሳውያን ስለ አልዓዛር ሲሰሙ ምን ለማድረግ አሰቡ?

ማቴዎስ 26:14-16፤ ዮሐንስ 11:1-53፤ 12:10

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ