የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w10 8/1 ገጽ 14-15
  • ኢየሱስ ቶሎ ያልሄደው ለምን ነበር?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ኢየሱስ ቶሎ ያልሄደው ለምን ነበር?
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2010
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ኢየሱስ አልዓዛርን ከሞት አስነሳው
    ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ምን ትማራለህ?
  • ስንሞት ምን እንሆናለን?
    ከታላቁ አስተማሪ ተማር
  • የአንባቢያን ጥያቄዎች
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2013
  • የሞቱ ሰዎች ይነሳሉ!
    መጽሐፍ ቅዱስ ምን ያስተምረናል?
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2010
w10 8/1 ገጽ 14-15

ልጆቻችሁን አስተምሩ

ኢየሱስ ቶሎ ያልሄደው ለምን ነበር?

ኢየሱስ የቅርብ ወዳጁ አልዓዛር በጣም እንደታመመ ሰምቷል። ወሬውን የነገረው የአልዓዛር እህቶች የሆኑት ማርያምና ማርታ የላኩት አንድ መልእክተኛ ነው። መልእክተኛው የመጣው አልዓዛርና እህቶቹ ከሚኖሩበት ከቢታንያ ነው። እህትማማቾቹ የሚኖሩት ኢየሱስ በወቅቱ ከነበረበት ስፍራ ርቆ በሚገኝ ቦታ ይኸውም ከዮርዳኖስ ማዶ ቢሆንም ኢየሱስ ወንድማቸውን ሊፈውሰው እንደሚችል ያምናሉ። ከዚያ በፊት ኢየሱስ ባለበት ቦታ ሆኖ በሩቅ የሚገኙ ሰዎችን እንደፈወሰ ያውቃሉ።—ማቴዎስ 8:5-13፤ ዮሐንስ 11:1-3

[በገጽ 14 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

መልእክተኛው ኢየሱስ ወዳለበት ሄዶ አሳዛኙን ዜና ሲነግረው ኢየሱስ ምንም አላደረገም። መጽሐፍ ቅዱስ “በዚያው በነበረበት ቦታ ሁለት ቀን ቆየ” በማለት ይናገራል። (ዮሐንስ 11:6) ኢየሱስ አልዓዛርን ለመርዳት ፈጥኖ ያልሄደው ለምን እንደሆነ ታውቃለህ?—a እስቲ ይህን ጉዳይ እንመርምር።

ኢየሱስ፣ አልዓዛር ታሞ እንደሞተ አውቋል። ስለዚህ ለሐዋርያቱ “ተመልሰን ወደ ይሁዳ እንሂድ” አላቸው። እነሱም “አሁን በቅርብ እኮ የይሁዳ ሰዎች ሊወግሩህ ፈልገው ነበር፤ ታዲያ ወደዚያ ተመልሰህ ልትሄድ ነው?” በማለት ሐሳቡን ተቃወሙ። ኢየሱስ “ወዳጃችን አልዓዛር ተኝቷል፤ እኔም ከእንቅልፍ ልቀሰቅሰው ወደዚያ እሄዳለሁ” አላቸው።

ሐዋርያቱም መልሰው “ጌታ ሆይ፣ ተኝቶ ከሆነ ይሻለዋል” አሉት። በዚህ ጊዜ ኢየሱስ “አልዓዛር ሞቷል” በማለት በግልጽ ነገራቸው። ቀጥሎም “በዚያ ባለመኖሬ ስለ እናንተ ደስ ይለኛል። ያም ሆነ ይህ ወደ እሱ እንሂድ” በማለት መናገሩ ሐዋርያቱን ሳያስገርማቸው አልቀረም።

ቶማስ በድፍረት ‘ከኢየሱስ ጋር እንድንሞት አብረነው እንሂድ’ አለ። ቶማስ፣ ጠላቶች ኢየሱስን እንደገና ሊገድሉት እንደሚሞክሩ ያውቅ ነበር፤ ሐዋርያቱም ጭምር ሊገደሉ ይችላሉ። ይሁን እንጂ ሁሉም አብረው ሄዱ። ከሁለት ቀን ገደማ በኋላ የአልዓዛር የትውልድ ከተማ ወደሆነችው ወደ ቢታንያ ደረሱ። ቢታንያ የምትገኘው ከኢየሩሳሌም ሦስት ኪሎ ሜትር ገደማ ርቀት ላይ ነው።—ዮሐንስ 11:7-18

ኢየሱስ ቀደም ብሎ ቢታንያ ባለመድረሱ የተደሰተው ለምን እንደሆነ ታውቃለህ?— እርግጥ ነው፣ ኢየሱስ ከዚያ በፊት ሌሎች ሰዎችን ከሞት አስነስቷል፤ ይሁን እንጂ እነዚያ ሰዎች ኢየሱስ እስኪያስነሳቸው ድረስ ሞተው የቆዩት ለጥቂት ሰዓታት ብቻ ነበር። (ሉቃስ 7:11-17, 22፤ 8:49-56) የአልዓዛር አስከሬን ግን ከተቀበረ የተወሰኑ ቀናት አልፈዋል። በዚህ ጊዜ አልዓዛር በእርግጥ ስለመሞቱ ማንም ሰው ሊጠራጠር አይችልም!

የአልዓዛር እህት ማርታ ኢየሱስ ወደ ቢታንያ እንደተቃረበ ስትሰማ ልትቀበለው ሮጣ ወጣች። “ጌታ ሆይ፣ አንተ እዚህ ኖረህ ቢሆን ኖሮ ወንድሜ ባልሞተ ነበር” አለችው። ኢየሱስም “ወንድምሽ ይነሳል” በማለት አጽናናት። ማርታ ሮጣ ተመለሰችና እህቷን ማርያምን በሚስጥር ጠርታ “መምህሩ እዚህ ተገኝቷል፤ ሊያገኝሽ ይፈልጋል” አለቻት።

[በገጽ 15 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

ማርያምም ወደ ኢየሱስ ለመሄድ ወዲያውኑ ተነስታ ወጣች። ሕዝቡ ግን ወደ መቃብሩ ልትሄድ መስሏቸው ተከተሏት። ኢየሱስም ማርያምና አብሯት ያለው ሕዝብ ሲያለቅሱ ሲመለከት እሱም “እንባውን አፈሰሰ።” ወዲያውኑም ሁሉም በትልቅ ድንጋይ ወደተዘጋው መቃብር ደረሱ። ኢየሱስ “ድንጋዩን አንሱት” በማለት አዘዘ። ማርታ ግን “ጌታ ሆይ፣ አራት ቀን ስለሆነው አሁን ይሸታል” አለች።

ሕዝቡም ኢየሱስን በመታዘዝ ድንጋዩን አነሱት። ከዚያም ኢየሱስ፣ አልዓዛርን ከሞት ለማስነሳት የሚያስችል ኃይል አምላክ እንደሚሰጠው በመገንዘብ በቅድሚያ በጸሎት ምስጋናውን አቀረበ። ቀጥሎም “አልዓዛር፣ ና ውጣ” በማለት በታላቅ ድምፅ ጮኸ። አልዓዛርም ‘በመግነዝ እንደተገነዘ’ ወጣ። ስለዚህ ኢየሱስ “ፍቱትና ይሂድ” በማለት አዘዛቸው።—ዮሐንስ 11:19-44

[በገጽ 15 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

ኢየሱስ ቶሎ ወደ ቢታንያ ያልሄደው ለምን እንደሆነ አሁን ገባህ?— መቆየቱ ስለ አባቱ ስለ ይሖዋ የበለጠ ምሥክርነት ለመስጠት እንደሚያስችለው ያውቅ ስለነበረ ነው። ደግሞም የተሻለውን ጊዜ በመምረጡ ብዙዎች አማኞች ሊሆኑ ችለዋል። (ዮሐንስ 11:45) ከኢየሱስ ምሳሌ ምን ልንማር እንደምንችል አስተዋልክ?—

አንተም አምላክ ስላደረጋቸውና ወደፊትም ስለሚያደርጋቸው አስደናቂ ነገሮች ምሥክርነት ለመስጠት የሚያስችል ምቹ ጊዜ መምረጥ ትችላለህ። ምናልባትም አብረውህ ለሚማሩ ልጆች ወይም ለአስተማሪዎችህ ስለ አምላክ ድንቅ ሥራዎች መናገር ትችል ይሆናል። በክፍል ውስጥም እንኳን አንዳንድ ልጆች ባገኙት አጋጣሚ ተጠቅመው የአምላክ መንግሥት ለሰው ዘር ስለሚያመጣቸው ታላላቅ በረከቶች ተናግረዋል። እርግጥ ነው፣ አንተ ሙታንን ማስነሳት አትችልም፤ ይሁን እንጂ የምንወዳቸውን በሞት ያንቀላፉ ሰዎች ወደ ሕይወት ለመመለስ ችሎታውም ፈቃደኝነቱም ያለውን አምላክ እንዲያውቁት ሌሎችን መርዳት ትችላለህ።

a ይህን ርዕስ የምታነበው ከትንሽ ልጅ ጋር ከሆነ፣ ይህ ሰረዝ ቆም ብለህ ልጁ ሐሳቡን እንዲገልጽ እንድታበረታታው ለማስታወስ ተብሎ የተደረገ ነው።

ጥያቄዎች፦

  • ኢየሱስ አልዓዛርን ለመርዳት ቶሎ ያልሄደው ለምን ነበር?

  • ቶማስ ‘ከኢየሱስ ጋር እንድንሞት አብረነው እንሂድ’ ያለው ለምን ነበር?

  • ኢየሱስ አልዓዛርን ማስነሳት የቻለው እንዴት ነበር?

  • አንተም ኢየሱስ ከተወው ምሳሌ ትምህርት እንዳገኘህ ለማሳየት ምን ልታደርግ ትችላለህ?

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ