የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • lfb ትምህርት 88 ገጽ 206
  • ኢየሱስ ታሰረ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ኢየሱስ ታሰረ
  • ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ምን ትማራለህ?
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ክርስቶስ አልፎ ተሰጠ እንዲሁም ተያዘ
    ኢየሱስ—መንገድ፣ እውነት፣ ሕይወት
  • በይሁዳ ጠቋሚነት መያዝ
    እስከ ዛሬ ከኖሩት ሁሉ የሚበልጠው ታላቅ ሰው
  • ኢየሱስ በአንድ የአትክልት ቦታ
    የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች መማሪያ መጽሐፌ
  • የኢየሱስ ሰብዓዊ ሕይወት የመጨረሻ ዕለት
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1999
ለተጨማሪ መረጃ
ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ምን ትማራለህ?
lfb ትምህርት 88 ገጽ 206
ይሁዳ በጌትሴማኒ የአትክልት ስፍራ ኢየሱስን አሳልፎ ሲሰጠው

ትምህርት 88

ኢየሱስ ታሰረ

ኢየሱስና ሐዋርያቱ የቄድሮንን ሸለቆ ተሻግረው ወደ ደብረ ዘይት ተራራ እየተጓዙ ነው። እኩለ ሌሊት አልፏል፤ ጨረቃዋ ሙሉ ሆና ትታያለች። ወደ ጌትሴማኒ የአትክልት ስፍራ እንደደረሱ ኢየሱስ ሐዋርያቱን “እዚህ ሁኑና ነቅታችሁ ጠብቁ” አላቸው። ከዚያም ኢየሱስ ትንሽ ራቅ ብሎ በመንበርከክ መጸለይ ጀመረ። በታላቅ ጭንቀት ተውጦ “የአንተ ፈቃድ ይፈጸም” በማለት ይሖዋን ለመነ። ከዚያም ይሖዋ ኢየሱስን እንዲያበረታታው አንድ መልአክ ላከለት። ኢየሱስ ወደ ሐዋርያቱ ሲመለስ ተኝተው አገኛቸው። ከዚያም ‘ተነሱ! ይህ የእንቅልፍ ሰዓት አይደለም! ጠላቶቼ እኔን የሚይዙበት ሰዓት ደርሷል’ አላቸው።

ይሁዳ በከረጢት ገንዘብ ሲሰጠው

ወዲያውኑም ይሁዳ ሰይፍና ዱላ ከያዙ ሰዎች ጋር መጣ። ይሁዳ ከኢየሱስ ጋር ብዙ ጊዜ ወደዚህ የአትክልት ስፍራ ይመጣ ስለነበር ኢየሱስን እዚህ ሊያገኘው እንደሚችል አውቆ ነበር። ይሁዳ ለወታደሮቹ ኢየሱስ የትኛው እንደሆነ በምልክት እንደሚያሳያቸው ነግሯቸው ነበር። ስለዚህ ወደ ኢየሱስ ሄዶ ‘መምህር፣ ሰላም ለአንተ ይሁን’ አለውና ሳመው። ኢየሱስም ‘ይሁዳ፣ እኔን በመሳም አሳልፈህ ልትሰጠኝ ነው?’ አለው።

ኢየሱስ ወደ ፊት ራመድ ብሎ ሰዎቹን “ማንን ነው የምትፈልጉት?” አላቸው። እነሱም “የናዝሬቱን ኢየሱስ” ብለው መለሱለት። እሱም “እኔ ነኝ” አላቸው፤ ከዚያም ሰዎቹ ወደ ኋላ በመሸሽ መሬት ላይ ወደቁ። ኢየሱስም ሰዎቹን በድጋሚ “ማንን ነው የምትፈልጉት?” ብሎ ጠየቃቸው። እነሱም ደግመው “የናዝሬቱን ኢየሱስ” አሉት። ኢየሱስም ‘እኔ ነኝ አልኳችሁ እኮ። ስለዚህ እነሱን ተዉአቸው’ አላቸው።

ጴጥሮስ ሰዎቹ ኢየሱስን ሊይዙት መሆኑን ሲያይ ሰይፉን በመምዘዝ የሊቀ ካህናቱን ባሪያ የማልኮስን ጆሮ ቆረጠው። ኢየሱስ ግን የማልኮስን ጆሮ በመዳሰስ ፈወሰው። ከዚያም ጴጥሮስን እንዲህ አለው፦ ‘ሰይፍህን መልስ። በሰይፍ ከተዋጋህ በሰይፍ ትሞታለህ።’ ወታደሮቹ ኢየሱስን ይዘው እጁን አሰሩት፤ በዚህ ጊዜ ሐዋርያቱ ጥለውት ሸሹ። ከዚያም ሰዎቹ ኢየሱስን የካህናት አለቃ ወደሆነው ወደ ሐና ወሰዱት። ሐናም ኢየሱስን የተለያዩ ጥያቄዎችን ከጠየቀው በኋላ ወደ ሊቀ ካህናቱ ወደ ቀያፋ ቤት ላከው። ታዲያ ሐዋርያቱ ምን አጋጥሟቸው ይሆን?

“በዓለም ሳላችሁ መከራ ይደርስባችኋል፤ ነገር ግን አይዟችሁ! እኔ ዓለምን አሸንፌዋለሁ።”—ዮሐንስ 16:33

ጥያቄ፦ በጌትሴማኒ የአትክልት ስፍራ ምን ነገር ተፈጸመ? ኢየሱስ በዚያ ምሽት ካደረገው ነገር ምን ትማራለህ?

ማቴዎስ 26:36-57፤ ማርቆስ 14:32-50፤ ሉቃስ 22:39-54፤ ዮሐንስ 18:1-14, 19-24

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ