የክፍል 3 ማስተዋወቂያ
መጽሐፍ ቅዱስ ከጥፋት ውኃው በኋላ ባሉት ዓመታት ውስጥ ይሖዋን ያገለግሉ የነበሩ ጥቂት ሰዎችን ይጠቅሳል። ከእነዚህ ሰዎች መካከል የይሖዋ ወዳጅ ተብሎ የተጠራው አብርሃም ይገኝበታል። አብርሃም የይሖዋ ወዳጅ የተባለው ለምንድን ነው? ወላጅ ከሆንክ ልጅህን ይሖዋ በግለሰብ ደረጃ እንደሚያስብለትና ሊረዳው እንደሚፈልግ እንዲገነዘብ እርዳው። ልክ እንደ አብርሃም፣ እንደ ሎጥና እንደ ያዕቆብ ሁሉ እኛም ይሖዋ እንዲረዳን በነፃነት ልንጠይቀው እንችላለን። ይሖዋ ቃል የገባውን ነገር በሙሉ እንደሚፈጽም እርግጠኛ መሆን እንችላለን።