የክፍል 4 ማስተዋወቂያ
በዚህ ክፍል ላይ የዮሴፍን፣ የኢዮብን፣ የሙሴንና የእስራኤላውያንን ታሪክ እንመለከታለን። ዲያብሎስ በእነዚህ ሰዎች ላይ ብዙ መከራ አድርሶባቸዋል። አንዳንዶቹ የፍትሕ መጓደል ደርሶባቸዋል፣ ታስረዋል፣ ባሪያ ሆነዋል እንዲሁም የሚወዱትን ሰው በሞት አጥተዋል። ሆኖም ይሖዋ በተለያየ መንገድ ጠብቋቸዋል። ወላጅ ከሆንክ፣ ልጅህ እነዚህ የይሖዋ አገልጋዮች ያጋጠማቸውን መከራ በመቋቋም እምነታቸውን ጠብቀው መኖር የቻሉት እንዴት እንደሆነ እንዲገነዘብ እርዳው።
ይሖዋ አሥሩን መቅሰፍቶች በመጠቀም ከግብፅ አማልክት ይበልጥ ኃያል መሆኑን አሳይቷል። በጥንት ዘመን ይሖዋ ሕዝቦቹን የጠበቀው እንዴት እንደሆነና አሁንም ሕዝቦቹን የሚጠብቀው እንዴት እንደሆነ ጎላ አድርገህ ግለጽ።