የክፍል 11 ማስተዋወቂያ
ይህ ክፍል ከክርስቲያን ግሪክኛ ቅዱሳን መጻሕፍት ጋር ያስተዋውቀናል። ኢየሱስ በአንዲት ትንሽ ከተማ ውስጥ ይኖር በነበረ ድሃ ቤተሰብ ውስጥ ተወለደ። ኢየሱስ አናጺ ከሆነው አባቱ ጋር ይሠራ ነበር። የሰውን ዘር የሚያድነው እሱ ነው። ይሖዋ ኢየሱስን የአምላክ መንግሥት ንጉሥ እንዲሆን መርጦታል። ወላጅ ከሆንክ፣ ይሖዋ ኢየሱስ የሚወለድበትን ቤተሰብ በጥንቃቄ የመረጠው እንዴት እንደሆነ ልጅህ እንዲያስተውል እርዳው፤ ይህን ያደረገው ኢየሱስ በጥሩ ሁኔታ እንዲያድግ አስቦ ነው። ከዚህም ሌላ ሄሮድስ ኢየሱስን እንዳይገድለው ይሖዋ የጠበቀው እንዴት እንደሆነና የይሖዋን ዓላማ ሊያከሽፍ የሚችል ምንም ነገር እንደሌለ አስረዳው። ይሖዋ ለኢየሱስ መንገድ እንዲጠርግለት ዮሐንስን ልኮታል። ኢየሱስ ከትንሽነቱ ጀምሮ ጥበብ የተንጸባረቀባቸውን የይሖዋን መመሪያዎች እንደሚወድ ያሳየው እንዴት እንደሆነም ጎላ አድርገህ ግለጽ።