የክፍል 13 ማስተዋወቂያ
ኢየሱስ ወደ ምድር የመጣው ኃጢአተኛ ለሆኑ የሰው ልጆች ሕይወቱን ለመስጠት ነው። እስከ ሞት ድረስ ለይሖዋ ታማኝ በመሆን ዓለምን አሸንፏል። ይሖዋም ለልጁ ታማኝ በመሆን ከሞት አስነስቶታል። ኢየሱስ እስከ ዕለተ ሞቱ በትሕትና ሌሎችን አገልግሏል፤ እንዲሁም ስህተት ሲሠሩ ይቅር ብሏቸዋል። ኢየሱስ ከሞት ከተነሳ በኋላ ለደቀ መዛሙርቱ ታየ። ከዚያም የሰጣቸውን አስፈላጊ ሥራ እንዴት መሥራት እንዳለባቸው ገለጸላቸው። ወላጅ ከሆንክ፣ ልጅህ በዚህ ሥራ የመካፈል መብት እንዳለን እንዲገነዘብ እርዳው።