መዝሙር 65
ወደፊት ግፋ!
በወረቀት የሚታተመው
1. ወደፊት ግፋ፣ ወደ ጉልምስና!
የእውነት ብርሃን ባለም ዙሪያ ደምቆ ይብራ።
ተጣጣር ባገልግሎት ለመሻሻል፤
አምላክ ይባርክሃል።
ሁላችን እንስበክ በጋራ፤
ኢየሱስ ሠርቷል ይህን ሥራ።
አምላክ ይረዳሃል ከ’ውነት እንዳትርቅ፤
ሁሌም ተጋደል ለጽድቅ።
2. ወደፊት ግፋ፣ በድፍረት ተናገር!
የዘላለም ምሥራች ለሰው ሁሉ አብስር።
ከቤት ወደ ቤት አዘውትረህ መሥክር፤
ይሖዋ እንዲከበር።
ተቃዋሚዎች ቢያስፈራሩም፣
አትፍራ ተናገር ለሁሉም።
መንግሥቱ መቅረቡ የምሥራች ነው፤
አስተምር በየቦታው።
3. ወደፊት ግፋ፣ እርዳ ተመላልሰህ፤
ብዙ ሥራ ስላለ ይሻሻል ችሎታህ።
የአምላክም መንፈስ ሁልጊዜ ይምራህ፤
ደስተኛ ትሆናለህ።
ለሰዎች ፍቅር አሳያቸው፤
ደጋግመህ በመሄድ ቤታቸው።
እርዳቸው ፈጣን እድገት እንዲያደርጉ፤
እውነት ይታይ ድምቀቱ።
(በተጨማሪም ፊልጵ. 1:27፤ 3:16ን እና ዕብ. 10:39ን ተመልከት።)