መዝሙር 119
ጠንካራ እምነት ሊኖረን ይገባል
በወረቀት የሚታተመው
1. ይሖዋ ብዙ ጊዜ ተናግሯል፤
በጥንት ነቢያቱ በኩል።
ዛሬም ‘ንስሐ ግቡ’ ይለናል፤
በገዛ ልጁ በኩል።
(አዝማች)
ጽኑ ነው ወይ እምነታችን?
ሊያበቃን ’ሚችል ለመዳን?
ይታያል ወይ በሥራችን?
ይህ ዓይነት እምነት ነው የሚያድነን።
2. የክርስቶስን ት’ዛዝ በማክበር፤
እውነትን እናስፋፋለን።
ቃሉን በድፍረት እናውጃለን፤
አንሸሽግም መል’ክቱን።
(አዝማች)
ጽኑ ነው ወይ እምነታችን?
ሊያበቃን ’ሚችል ለመዳን?
ይታያል ወይ በሥራችን?
ይህ ዓይነት እምነት ነው የሚያድነን።
3. የማይናወጥ ነው እምነታችን፤
ፍርሃትም አያሸንፈን።
አምላካችን ነው መታመኛችን፤
ይታየን መዳናችን።
(አዝማች)
ጽኑ ነው ወይ እምነታችን?
ሊያበቃን ’ሚችል ለመዳን?
ይታያል ወይ በሥራችን?
ይህ ዓይነት እምነት ነው የሚያድነን።