ክፍል አንድ
‘ሰማያት ተከፈቱ’
ፍሬ ሐሳብ፦ የይሖዋ ዙፋን የሚገኝበትን መንፈሳዊ ዓለም በጨረፍታ የሚያሳይ ራእይ
የትኛውም ሰብዓዊ ፍጡር ሁሉን ቻይ አምላክ የሆነውን ይሖዋን አይቶ በሕይወት ሊኖር አይችልም። (ዘፀ. 33:20) ይሁን እንጂ ይሖዋ ለሕዝቅኤል የድርጅቱ ሰማያዊ ክፍል ምን እንደሚመስል በራእይ አሳይቶታል፤ ይህ ራእይ በከፍተኛ አድናቆት እንድንሞላ ከማድረግ ባሻገር እሱ ብቻ እውነተኛ አምላክ የሆነውን ይሖዋን የማምለክ ውድ መብታችንን ይበልጥ ከፍ አድርገን እንድንመለከት ያነሳሳናል።