ክፍል አምስት
“በመካከላቸው . . . እኖራለሁ”—የይሖዋ ንጹሕ አምልኮ መልሶ ተቋቋመ
ፍሬ ሐሳብ፦ ሕዝቅኤል ስለ ቤተ መቅደሱ ያየው ራእይ ያሉት አንዳንድ ገጽታዎች እና ንጹሕ አምልኮን በተመለከተ የምናገኘው ትምህርት
ይሖዋ ለነቢዩ ሕዝቅኤልና ለሐዋርያው ዮሐንስ በጣም ተመሳሳይ የሆኑ ራእዮችን አሳይቷቸዋል። እነዚህ ራእዮች ያሏቸው አንዳንድ ገጽታዎች በዛሬው ጊዜ ይሖዋን ተቀባይነት ባለው መንገድ ማምለክ እንድንችል የሚረዱ ጠቃሚ ትምህርቶችን ይዘዋል፤ በተጨማሪም ወደፊት በአምላክ መንግሥት ሥር በገነት ውስጥ የሚኖረው ሁኔታ ምን እንደሚመስል እንድናውቅ ይረዱናል።