የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • CO-pgm20 ገጽ 7-8
  • ለተሰብሳቢዎች የቀረበ መረጃ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ለተሰብሳቢዎች የቀረበ መረጃ
  • የ2020 የክልል ስብሰባ ፕሮግራም
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ለየት ያለ ስብሰባ
  • ለተሰብሳቢዎች የቀረበ መረጃ
    የ2024 የክልል ስብሰባ ፕሮግራም
  • ለተሰብሳቢዎች የቀረበ መረጃ
    የ2023 የክልል ስብሰባ ፕሮግራም
  • ለተሰብሳቢዎች የቀረበ መረጃ
    የ2019 የክልል ስብሰባ ፕሮግራም
  • ለተሰብሳቢዎች የቀረበ መረጃ
    የ2025 የክልል ስብሰባ ፕሮግራም
ለተጨማሪ መረጃ
የ2020 የክልል ስብሰባ ፕሮግራም
CO-pgm20 ገጽ 7-8

ለተሰብሳቢዎች የቀረበ መረጃ

መዋጮዎች ስብሰባው አስደሳች ብሎም ይበልጥ ወደ ይሖዋ እንድንቀርብ የሚረዳን እንዲሆን ለማድረግ ሲባል ከፍተኛ ወጪ ወጥቶ በቂ ወንበሮች እንዲሁም የድምፅ መሣሪያዎችና ሌሎች በርካታ አገልግሎቶች እንዲኖሩ ዝግጅት ተደርጓል። በፈቃደኝነት የምታደርጉት መዋጮ እነዚህን ወጪዎች ለመሸፈን እንዲሁም በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚከናወነውን ሥራ ለመደገፍ አስተዋጽኦ ያበረክታል። “የመዋጮ ሣጥን” የሚል ምልክት በግልጽ የተጻፈባቸው ሣጥኖች በስብሰባው ቦታ አመቺ በሆኑ ስፍራዎች ላይ ተቀምጠዋል። donate.jw.org ወደተባለው ድረ ገጽ በመሄድ በኢንተርኔት አማካኝነት መዋጮ ማድረግም ትችላላችሁ። የምታደርጉትን መዋጮ ሁሉ ከልብ እናደንቃለን። የበላይ አካሉ የአምላክን መንግሥት ዓላማ ለማራመድ በልግስና ለምታደርጉት ድጋፍ ሁሉ በዚህ አጋጣሚ ምስጋናውን ይገልጻል።

አስተናጋጆች አስተናጋጆች የተመደቡት እናንተን ለመርዳት ነው። ስለዚህ መኪና ማቆምን፣ በመተላለፊያዎች ላይ መቆምን፣ ወንበር መያዝንና ሌሎች ነገሮችን በተመለከተ የሚሰጧችሁን መመሪያ በመከተል እባካችሁ ሙሉ በሙሉ ተባበሯቸው።

ወንበር እባካችሁ ለሌሎች አሳቢነት አሳዩ። ወንበር መያዝ የሚቻለው ለቤተሰባችሁ አባላት፣ ከእናንተ ጋር በመኪና ለሚመጡ፣ አብረዋችሁ ለሚኖሩ ወይም በአሁኑ ጊዜ መጽሐፍ ቅዱስ ለምታስጠኗቸው ሰዎች ብቻ መሆኑን አስታውሱ። እባካችሁ በአጠገባችሁ ባሉት ወንበሮች ላይ ዕቃዎቻችሁን አታስቀምጡ።

የመጀመሪያ ደረጃ የሕክምና እርዳታ ይህ ዝግጅት የተደረገው ድንገት ለሚያጋጥም የጤና ችግር ብቻ እንደሆነ እባካችሁ አስታውሱ።

የፈቃደኛ አገልግሎት ከክልል ስብሰባው ጋር በተያያዘ በሚከናወኑ የተለያዩ ሥራዎች መካፈል ከፈለጋችሁ እባካችሁ ለፈቃደኛ አገልግሎት ክፍል አመልክቱ።

ጠፍተው የተገኙ ዕቃዎች የሚቀመጡበት ቦታ ጠፍተው የተገኙ ዕቃዎች ሁሉ ወደዚህ ክፍል መምጣት አለባቸው። ዕቃ ከጠፋባችሁ ወደዚህ ክፍል በመሄድ ንብረታችሁን ጠይቃችሁ መውሰድ ትችላላችሁ። ከወላጆቻቸው የጠፉ ልጆች ወደዚህ ክፍል መወሰድ አለባቸው። ሆኖም በማንም ላይ አላስፈላጊ ጫና እንዳይፈጠር እባካችሁ ልጆቻችሁን በቅርብ ተከታተሏቸው እንዲሁም ከአጠገባችሁ እንዳይርቁ ጠብቋቸው።

ጥምቀት የተለየ ዝግጅት ካልተደረገ በቀር ተጠማቂዎቹ የሚቀመጡት ከመድረኩ ፊት ለፊት ባለው ቦታ ላይ ይሆናል። የጥምቀት እጩዎች ቅዳሜ ጠዋት የሚቀርበው የጥምቀት ንግግር ከመጀመሩ በፊት በተዘጋጀላቸው ቦታ ላይ መገኘት አለባቸው። እያንዳንዱ ተጠማቂ ለጥምቀት ተስማሚ የሆነ ልብስና ፎጣ ይዞ መምጣት አለበት።

ለየት ያለ ስብሰባ

አንዲት የይሖዋ ምሥክር ለአንዲት ሴት ስትመሠክር።

የመንግሥቱ ወንጌላውያን ትምህርት ቤት አገልግሎታቸውን የማስፋት ፍላጎት ያላቸው ከ23 እስከ 65 ዓመት ባለው የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ አቅኚዎች፣ ለመንግሥቱ ወንጌላውያን በተዘጋጀው ትምህርት ቤት መካፈል ከሚፈልጉ አመልካቾች ጋር እሁድ ከሰዓት በኋላ በሚደረገው ስብሰባ ላይ እንዲገኙ ተጋብዘዋል። ይህ ስብሰባ የሚደረግበት ሰዓትና ቦታ አስቀድሞ በማስታወቂያ ይገለጻል።

በይሖዋ ምሥክሮች የበላይ አካል የተዘጋጀ

© 2020 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ