የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • CO-pgm23 ገጽ 7-8
  • ለተሰብሳቢዎች የቀረበ መረጃ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ለተሰብሳቢዎች የቀረበ መረጃ
  • የ2023 የክልል ስብሰባ ፕሮግራም
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ለተሰብሳቢዎች የቀረበ መረጃ
    የ2024 የክልል ስብሰባ ፕሮግራም
  • ለተሰብሳቢዎች የቀረበ መረጃ
    የ2020 የክልል ስብሰባ ፕሮግራም
  • ለተሰብሳቢዎች የቀረበ መረጃ
    የ2025 የክልል ስብሰባ ፕሮግራም
  • ለተሰብሳቢዎች የቀረበ መረጃ
    የ2019 የክልል ስብሰባ ፕሮግራም
ለተጨማሪ መረጃ
የ2023 የክልል ስብሰባ ፕሮግራም
CO-pgm23 ገጽ 7-8

ለተሰብሳቢዎች የቀረበ መረጃ

አስተናጋጆች አስተናጋጆች የተመደቡት እናንተን ለመርዳት ነው። ስለዚህ መኪና ማቆምን፣ በመተላለፊያዎች ላይ መቆምን፣ ወንበር መያዝንና ሌሎች ነገሮችን በተመለከተ የሚሰጧችሁን መመሪያ በመከተል እባካችሁ ሙሉ በሙሉ ተባበሯቸው።

ጥምቀት የተለየ ዝግጅት ካልተደረገ በቀር ተጠማቂዎቹ የሚቀመጡት ከመድረኩ ፊት ለፊት ባለው ቦታ ላይ ይሆናል። የጥምቀት ዕጩዎች ቅዳሜ ጠዋት የሚቀርበው የጥምቀት ንግግር ከመጀመሩ በፊት በተዘጋጀላቸው ቦታ ላይ መገኘት አለባቸው። እያንዳንዱ ተጠማቂ ለጥምቀት ተስማሚ የሆነ ልብስና ፎጣ ይዞ መምጣት አለበት።

መዋጮዎች ስብሰባው አስደሳች ብሎም ይበልጥ ወደ ይሖዋ እንድንቀርብ የሚረዳን እንዲሆን ለማድረግ ሲባል ከፍተኛ ወጪ ወጥቶ በቂ ወንበሮች እንዲሁም የድምፅ መሣሪያዎችና ሌሎች በርካታ አገልግሎቶች እንዲኖሩ ዝግጅት ተደርጓል። በፈቃደኝነት የምታደርጉት መዋጮ እነዚህን ወጪዎች ለመሸፈን እንዲሁም ዓለም አቀፉን ሥራ ለመደገፍ አስተዋጽኦ ያበረክታል። “የመዋጮ ሣጥን” የሚል ምልክት በግልጽ የተጻፈባቸው ሣጥኖች በስብሰባው ቦታ አመቺ በሆኑ ስፍራዎች ላይ ተቀምጠዋል። donate.jw.org ወደተባለው ድረ ገጽ በመሄድ በኢንተርኔት አማካኝነት መዋጮ ማድረግም ትችላላችሁ። የምታደርጉትን መዋጮ ሁሉ ከልብ እናደንቃለን። የበላይ አካሉ የአምላክን መንግሥት ዓላማ ለማራመድ በልግስና ለምታደርጉት ድጋፍ ሁሉ በዚህ አጋጣሚ ምስጋናውን ይገልጻል።

የመጀመሪያ ደረጃ የሕክምና እርዳታ ይህ ዝግጅት የተደረገው ድንገት ለሚያጋጥም የጤና ችግር ብቻ እንደሆነ እባካችሁ አስታውሱ።

ጠፍተው የተገኙ ዕቃዎች የሚቀመጡበት ቦታ ጠፍተው የተገኙ ዕቃዎች ሁሉ ወደዚህ ክፍል መምጣት አለባቸው። ዕቃ ከጠፋባችሁ ወደዚህ ክፍል በመሄድ ንብረታችሁን ጠይቃችሁ መውሰድ ትችላላችሁ። ከወላጆቻቸው የጠፉ ልጆች ወደዚህ ክፍል መወሰድ አለባቸው። ሆኖም በማንም ላይ አላስፈላጊ ጫና እንዳይፈጠር እባካችሁ ልጆቻችሁን በቅርብ ተከታተሏቸው እንዲሁም ከአጠገባችሁ እንዳይርቁ ጠብቋቸው።

ወንበር እባካችሁ ለሌሎች አሳቢነት አሳዩ። ወንበር መያዝ የሚቻለው ለቤተሰባችሁ አባላት፣ ከእናንተ ጋር በመኪና ለሚመጡ፣ አብረዋችሁ ለሚኖሩ ወይም በአሁኑ ጊዜ መጽሐፍ ቅዱስ ለምታስጠኗቸው ሰዎች ብቻ መሆኑን አስታውሱ። እባካችሁ ከያዛችሁት ቦታ ውጭ በሌሎች ወንበሮች ላይ ዕቃዎቻችሁን አታስቀምጡ።

የፈቃደኛ አገልግሎት ከክልል ስብሰባው ጋር በተያያዘ በሚከናወኑ የተለያዩ ሥራዎች መካፈል ከፈለጋችሁ እባካችሁ ለፈቃደኛ አገልግሎት ክፍል አመልክቱ።

ለየት ያለ ስብሰባ

ወንድሞችና እህቶች ክፍል ውስጥ በጥሞና እያዳመጡ ማስታወሻ ሲይዙ።

የመንግሥቱ ወንጌላውያን ትምህርት ቤት

አገልግሎታቸውን ለማስፋት አቅምና ሁኔታቸው የሚፈቅድላቸው ሁሉ፣ ለመንግሥቱ ወንጌላውያን በተዘጋጀው ትምህርት ቤት መካፈል ከሚፈልጉ አመልካቾች ጋር እሁድ ከሰዓት በኋላ በሚደረገው ስብሰባ ላይ እንዲገኙ ተጋብዘዋል። ይህ ስብሰባ የሚደረግበት ሰዓትና ቦታ አስቀድሞ በማስታወቂያ ይገለጻል።

በይሖዋ ምሥክሮች የበላይ አካል የተዘጋጀ

© 2023 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ