የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • sjj መዝ. 152
  • ለስምህ ክብር የሚያመጣ ቤት

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ለስምህ ክብር የሚያመጣ ቤት
  • ለይሖዋ ‘በደስታ ዘምሩ’
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ይሖዋ አምላካችንን አወድሱ!
    ለይሖዋ ዘምሩ
  • ይሖዋ አምላካችንን አወድሱ!
    ለይሖዋ ‘በደስታ ዘምሩ’
  • የመንግሥቱን መዝሙር ዘምሩ!
    ለይሖዋ ‘በደስታ ዘምሩ’
  • የመንግሥቱን መዝሙር ዘምሩ!
    ለይሖዋ ዘምሩ
ለተጨማሪ መረጃ
ለይሖዋ ‘በደስታ ዘምሩ’
sjj መዝ. 152

መዝሙር 152

ለስምህ ክብር የሚያመጣ ቤት

በወረቀት የሚታተመው

(1 ነገሥት 8:27፤ 1 ዜና መዋዕል 29:14)

  1. 1. ሰማይን የፈጠርክ ይሖዋ፣

    ታላቅ አምላክ ነህ ገናና፤

    እንኳን ይህ ቤት፣ እንኳን ይህ ሕንፃ፣

    ሰማይ መች ይበቃህና።

    እናመልክሃለን በዚህ ቤት፤

    መንፈስህ ይደር፣ ይሙላበት።

    ባምልኳችን ልብህ ይደሰት፤

    ለቤትህ ጌጥ ይሁን ውበት።

    (መሸጋገሪያ)

    ያለን ነገር ሁሉ

    ከ’ጅህ ነው የተገኘው፤

    መልሰን የምንሰጥህ

    ያንተው ስጦታ ነው።

    (አዝማች)

    አዎ፣ ይገባሃል ምስጋና፤

    ምኞታችን ሰምሯልና።

    ለስምህ ቤት ለመሥራት በቃን፤

    እንዘምርልህ በደስታ።

  2. 2. አባት ሆይ፣ ላንተ ቤት ለመሥራት

    ብዙ ስንመኝ ኖረናል፤

    ቅኖች ስምህን እንዲጠሩ፣

    እንዲያመልኩህ በዚህ ስፍራ።

    ይህን ቤት ላንተ ሰጥተነዋል፤

    ሁሌም ለፈቃድህ ይዋል፤

    ድጋፍ ሆኖ ይኑር ለሥራህ፣

    ልጅህ ለሰጠን ባደራ።

    (መሸጋገሪያ)

    አሁን የሰጠነው፣

    ካለን ምርጣችንን ነው።

    ምን ይሰሰታል ላንተ፣

    ለጋሱ ይሖዋ!

    (አዝማች)

    አዎ፣ ይገባሃል ምስጋና፤

    ምኞታችን ሰምሯልና።

    ለስምህ ቤት ለመሥራት በቃን፤

    እንዘምርልህ በደስታ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ